ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤ “እየተቃጠለንና እየተገደልን አንሰበሰብም ፥ ልጆቻችን ያሉበት ሔደን አብረን እንቃጠላለን፤ እንሞታለን”
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 24, 2019
-
+ በኦሮሚያ ልዩ ልዩ ከተሞች በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው አስከፊ ጥቃት እና ግድያ ሳቢያ ቅዱስ ሲኖዶስ የምልአተ ጉባኤውን ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤
-
+ የተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለብዙኀን መገናኛዎች እና ለዓለም ኅብረተሰብ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያሰማውን መግለጫ እያረቀቁ ነው፤
-
+ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለመከላከያ ሚኒስትሩ እና ለሰላም ሚኒስትሯ ለመጨረሻ ጊዜ የሚደርስ ደብዳቤም እያዘጋጁ ነው፤
-
+ በባሌ፣ በአርሲ፣ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በድሬዳዋ እና በአዳማ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን፣ የአክራሪዎች እና ነውጠኞች ሰለባ እየኾኑ ነው፤ ቤታቸው እና ንብረታቸው እየተጠቃ ነው፤ አስከፊ እልቂት ማንዣበቡ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ሐራ ዘተዋሕዶ
መምህር ዘመድኩን እንዳቀበለን፦
“• በምዕራብ አሩሲ የኮፈሌ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ አባል የነበሩትን አረጋዊ አቶ ተምራት ፀጋዬ ገደሉ፣ ቀጥሎ አባትየው አስከሬን አጠገብ ልጃቸውን አቢቲ ታምራትን ገደሉ ቀጥለው እንደ ልጃቸው ያሳደጉትን የሱቃቸውን ሠራተኛ በሁለቱ አስከሬን አጠገብ አርደው ገደሉ። መኪናዎቻቸውን፣ ንብረታቸውን በእሳት አቃጠሉ።
• በመጨረሻም የሟቹን አረጋዊና የልጆቻቸውን አስከሬን ከተማው ላይ እየጎተቱ ሲጨፍሩ ዋሉ። ይሄ ሁሉ ሲሆን የኦሮሚያ ፖሊስና መከላከያ ቆሞ ከማየት ውጪ ምንም አያደርግም ነበር። በተጠና መልኩ በከተማዋ የሚገኙ የክርስቲያኖቹ ንንረትና ቤት በሙሉ በእሳት እንዲወድም ተደረገ።
• ይሄ የተዘጋጁበት የዘር ማጥፋት ድርጊት ነው። የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ይገመታል። ኦርቶዶክስ ኦሮሚያን ይልቀቅ ነው ፉከራቸው።”
ይህን እያየ እንዳለየ የሚሆንና ከዚህ በኋላ ከግራኝ አብዮት አህመድ ጎን የሚሰለፍ ኢትዮጵያዊ፡ ኢትዮጵያዊ ሊሆን አይችልምና እግሩ ይሰበር!!!
Leave a Reply