Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 24th, 2019

ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤ “እየተቃጠለንና እየተገደልን አንሰበሰብም ፥ ልጆቻችን ያሉበት ሔደን አብረን እንቃጠላለን፤ እንሞታለን”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 24, 2019

  • + በኦሮሚያ ልዩ ልዩ ከተሞች በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው አስከፊ ጥቃት እና ግድያ ሳቢያ ቅዱስ ሲኖዶስ የምልአተ ጉባኤውን ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤

  • + የተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለብዙኀን መገናኛዎች እና ለዓለም ኅብረተሰብ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያሰማውን መግለጫ እያረቀቁ ነው፤

  • + ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለመከላከያ ሚኒስትሩ እና ለሰላም ሚኒስትሯ ለመጨረሻ ጊዜ የሚደርስ ደብዳቤም እያዘጋጁ ነው፤

  • + በባሌ፣ በአርሲ፣ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በድሬዳዋ እና በአዳማ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን፣ የአክራሪዎች እና ነውጠኞች ሰለባ እየኾኑ ነው፤ ቤታቸው እና ንብረታቸው እየተጠቃ ነው፤ አስከፊ እልቂት ማንዣበቡ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሐራ ዘተዋሕዶ

መምህር ዘመድኩን እንዳቀበለን፦

“• በምዕራብ አሩሲ የኮፈሌ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ አባል የነበሩትን አረጋዊ አቶ ተምራት ፀጋዬ ገደሉ፣ ቀጥሎ አባትየው አስከሬን አጠገብ ልጃቸውን አቢቲ ታምራትን ገደሉ ቀጥለው እንደ ልጃቸው ያሳደጉትን የሱቃቸውን ሠራተኛ በሁለቱ አስከሬን አጠገብ አርደው ገደሉ። መኪናዎቻቸውን፣ ንብረታቸውን በእሳት አቃጠሉ።

በመጨረሻም የሟቹን አረጋዊና የልጆቻቸውን አስከሬን ከተማው ላይ እየጎተቱ ሲጨፍሩ ዋሉ። ይሄ ሁሉ ሲሆን የኦሮሚያ ፖሊስና መከላከያ ቆሞ ከማየት ውጪ ምንም አያደርግም ነበር። በተጠና መልኩ በከተማዋ የሚገኙ የክርስቲያኖቹ ንንረትና ቤት በሙሉ በእሳት እንዲወድም ተደረገ።

ይሄ የተዘጋጁበት የዘር ማጥፋት ድርጊት ነው። የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ይገመታል። ኦርቶዶክስ ኦሮሚያን ይልቀቅ ነው ፉከራቸው።”

ይህን እያየ እንዳለየ የሚሆንና ከዚህ በኋላ ከግራኝ አብዮት አህመድ ጎን የሚሰለፍ ኢትዮጵያዊ፡ ኢትዮጵያዊ ሊሆን አይችልምና እግሩ ይሰበር!!!

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የክርስቶስ ልጆች በናዝሬት ተወለዱ | የግብጽ ቡችሎች የኦሮሚያ ቄሮ ፖሊሶች ድል ተነሱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 24, 2019

የኢትዮጵያ ልጆች እንዲህ ናቸው፤ ተው! ኢትዮጵያን አትንኳት!’ ብለዋል። ኢትዮጵያውያን እንዲህ በርቱ፣ ቀጥሉበት ፥ ጠላቶቻችን ገና ምን አይተው! እነዚህ ምስጋናቢስ ከሃዲዎች፡ ኢትዮጵያውያንን እትብታቸው ከተቀቀበረበት ምድር ሊያባርሩ ይሻሉ፤ አይይ! ሁሉም ግን በተቃራኒው ይሆናል፤ በቅርቡ፡ ወደዱም ጠሉም፡ በሃገረ ኢትዮጵያ፡ ኢትዮጵያን ያልተቀበለ ሊኖርባት እንደማይችል ለመገንዘብ ይገደዳሉ ፥ በኬኒያ እንኳን ቦታ እንዳየገኙ ይደረጋሉ። ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ብቻ!

ሰዎች “ሂዱ! እናንት ርኵሳን!” ብለው ይጮኹባቸዋል፤ “ወግዱ! ወግዱ! አትንኩ!” ይሏቸዋል፤ ሸሽተው በሚቅበዘበዙበትም ጊዜ፣ በአሕዛብ መካከል ያሉ ሰዎች፣ “ከእንግዲህ በዚህ መቀመጥ አይገባቸውም!” ይላሉ።

[ሰቆቃወ ኤርምያስ ምዕራፍ ፬፥፫፡ ፳፪]

ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።

ጡት የሚጠባው የሕፃን ምላስ ከጥም የተነሣ ወደ ትናጋው ተጣበቀ፤ ሕፃናት እንጀራ ለመኑ፥ የሚቈርስላቸውም የለም።

የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፤ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነበሩ የፍግ ክምር አቀፉ።

የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኃጢአት በዛች።

አለቆችዋ ከበረዶ ይልቅ ጥሩ፥ ከወተት ይልቅ ነጭ ነበሩ፤ ገላቸው ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ቀይ ነበረ፥ መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበረ።

ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፤ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨት ሆኖአል።

በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፤ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።

የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፤ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው።

እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፥ ጽኑ ቍጣውን አፍስሶአል፤ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፥ መሠረትዋንም በላች።

የምድር ነገሥታት በዓለምም የሚኖሩ ሁሉ አስጨናቂና ጠላት በኢየሩሳሌም በር እንዲገባ አላመኑም።

የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ ስለ ነቢያቶችዋ ኃጢአትና ስለ ካህናቶች በደል ነው።

ታውረው በመንገድ ላይ ተቅበዘበዙ፤ ልብሳቸው እንዳይዳሰስ በደም ረክሰዋል።

እናንተ ርኩሳን፥ ራቁ፥ ርቃችሁም ሂዱ፥ አትንኩ ብለው ጮኹባቸው። በሸሹና በተቅበዘበዙ ጊዜ፥ በአሕዛብ መካከል። በዚህ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖሩም ተባለ።

የእግዚአብሔር ፊት በተናቸው እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፤ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፥ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።

ዓይናችን ወደ ከንቱ ረዳታችን ገና ሲመለከት ጠፍቶአል፤ በመቆየታችን ማዳን የማይቻለውን ሕዝብ ጠብቀናል።

በአደባባያችን እንዳንሄድ ፍለጋችንን ተከተሉ፤ ፍጻሜያችን ቀርቦአል፥ ዕድሜያችን አልቆአል፥ ፍጻሜያችን ደርሶአል።

አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስር ይልቅ ፈጣኖች ሆኑ፤ በተራሮች ላይ አሳደዱን፥ በምድረ በዳ ሸመቁብን።

ስለ እርሱ። በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት እንኖራለን ያልነው በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጕድጓዳቸው ተያዘ።

በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፤ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።

የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፤ ኃጢአትሽን ይገልጣል።

[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፳፫፥፲፩፡፲፱]

እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል፤ የዓመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል።

ከአምስት ወራት በፊት የቀረበ፦

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: