Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 22nd, 2019

ተዓምረኛው አባ ዘ-ወንጌል ተሰወሩ | አሁን የኢትዮጵያ መከራዋ ይጀምራል ፥ ትንሣኤዋም ይቀርባል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 22, 2019

እግዚአብሔር የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን አበው ነፍስ ጋር ይደምርልን!!!

አባ ዘወንጌል✦

አባታችን አባ ዘወንጌል በሰሜን ኢትዮጵያ፡ ኢሮብ በሚባል መድኃኒያለም ገዳም ላይ የሚገኙ ሲሆን የ610 አመት እድሜ ባለ ፀጋ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ በኛ ዘመን ሰው እንደ ቅጠል በሚረግፍበት፣ የደሀ እንባ እንደ ጎርፍ በሚፈስበት ወቅት እንዲህ ያሉ አባቶች በዚህ ጊዜ መገኘታቸው እጅግ በጣም የሚገርምና የሚያስደስትም ነው። እድሜ እንደ ማቱሳላ ይሉሀል ይህ ነው።

ስለ አባ ዘወንጌል ብዙ አለመስማታችንና ዓለማችንም ስለ አባታችን የእድሜ ፀጋና (በዚህ ዓለም ያልተሰማ) ሲፈጽሟቸው በነበሯቸው ተዓምራት ላይ አለመነጋገሩ እጅግ በጣም አሳዛኝ ጉዳይ ነው። እኔ እራሴ፡ “አልተፈቀደልኝም ነበርና”፡ ገና አሁን መስማቴ ነው። ሌሊቱን ሙሉ ሲያስገርመኝ ነው ያደረው!

ታታሪው ወንድማችን ዘመድኩን በቀለ የሚከተለውን አካፍሎናል

በትግራይ ክፍለ ሃገር አዲግራት አቅራቢያ በምትገኘው ኢሮብ ከተማ ውስጥ የሚገኙት አባታችን አባ ዘወንጌል በምድር ላይ ከ300 አመት በላይ የኖሩ ሲሆን እጅግ በጣም የሚያስደንቁ ተአምራትን እንደሚፈጽሙ ይነገራል።

አባ ዘወንጌል የአሲምባ መስቀለ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከተመረቀ በኋላ ወደ አምላኬ እሄዳለሁ ብለው አስቀድመው በተናገሩት መሠረት እንደ ቃላቸው ወደ አምላካቸው ተጠርተዋል።

አሁን እንደተነገረው የኢትዮጵያ መከራዋ ይጀምራል። ትንሣኤዋም ይቀርባል። የቀረውን የበረኸኞቹን ትእዛዝ በቀጣይ ጊዜ እንነጋገራለን። [ፈጥነን ንስሐ እንግባ]

መእምዝ ሶበ ፈጸመ ሑረቶ ሠናየ ወአሥመሮ ለእግዚአብሔር ወአዕረፈ በሰላም ”

ከዚህም በኋላ መልካም ጉዞውን በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቱ ለዝንቱ አብ ወበረከቱ ተሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን።”

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር። ለዘላለሙ አሜን።

ይህ ከመፈጸሙ በፊት ቀደም ብዬ ከበረኸኞቹ በተነገረኝ መሠረት መስከረም 18/2012 ዓም የጻፍኩላችሁን ማስታወሻም እነሆ፦

*★★★* በበረኸኞቹ ሲጠበቅ የቆየው ዕለት

መስከረም 18/2012 ዓም

#ETHIOPIA | ~ ከትንሣኤ በፊት ያለው የኢትዮጵያ ኅማማት ከዛሬ ዕለት በኋላ ይጀምራል የሚሉት ቀን ዛሬ ነው። ለአጨዳ የተዘጋጀ … … …

በብዙ በረኸኞች የቅዳሴ ቤቱ ምረቃ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በትግራይ ክፍለ ሀገር በአሲምባ በረሃ የሚገኘውና በአዲስ መልክ የተሠራው የመስቀለ ኢየሱስ ህንፃ ቤተክርስቲያን ይህ ነው።

መስቀለ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከአዲግራት 80 ኪ ሜ ተጉዘው በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ አሲምባ ተራራ ላይ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው።

እንደሚታወቀው አሲምባ ማለት የዛሬዋን ኢትዮጵያ ትርምስምሷን ያወጡ የዘመኑ ወጣቶች የተሰባሰቡባት፣ የብዙዎችም ደም የፈሰሰበት አካባቢ ነው። በበረሃው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቅዱሳን መኖሪያም ነው። የመስቀለ ክርስቶስ በስፍራው የነበረ ቢሆንም ይሄኛው በአዲስ መልክ እግዚአብሔር ፈቃዱ የሆነላቸውና ያሳሰባቸው ባለ ተስፋ ምእመናን ያሠሩት ቤተ ክርስቲያንም ነው።

ዕድሜያቸው በትክክል ይህን ያህል ዘመን ነው ብሎ ለመግለጽ ያልተቻለ አባ ዘወንጌል የተባሉ ፀጋ እግዚአብሔር የበዛላቸው አባትም ያሉበት ስፍራም ነው። ይህ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት መስከረም 18/2012 ዓም በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይመረቃል።

ከዚህ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ በኋላ አረጋዊው አባ ዘወንጌል ይሰወራሉ። የኢትዮጵያም መከራ ይጀምራል። እስከ 2015 .ም ድረስ ደስ አይልም። ረሃብ፣ የእርስ በእርስ ጦርነትና ክፉ ገዳይ በሽታም ይከሰታል ይላሉ በረኸኞቹ። ታቦተ ኢየሱስ ያለበት ገዳምም ሆነ ቤተ ክርስቲያን መትረፊያ ነውም ይላሉ።

ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይጀምራል። የዓለም መከራዋም ይጀምራል። ኃያላኑ ራሳቸው በሠሩት መሣሪያ እርስ በእርሳቸው ይጫረሳሉ። በውጭ ሀገራት የተሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት የብዙ ሀበሾች መትረፊያ ይሆናሉ። ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል። በተዋሕዶ ሃይማኖት አምኖ ለመጠመቅ በባህርና በየብስ የሰው ዘር ይጎርፋል። እና ሌሎች ከበድ ከበድ ደግሞም መጨረሻው ደስ የሚል ነገር ይናገራሉ።

እንደወረደ ለመናገር ቢጨንቀኝ ጊዜ ነው ቆንጠር ቆንጠር ማድረጌ። 7 ተላላቅ ገዳማት ይቃጠላሉ፣ ይወድማሉ። በዳር ሀገር ያሉ ክርስቲያኖች በተለይ ወጣቶቹ በሰይፍ፣ በመሃል ሀገር ያሉት በጦርነትና የሚበዛው በረሃብ ይጎዳሉ። ከላይ እና ከታች እሳት ይዘንባል። የማይነቅዝ እህል እና ጨው በብዛት ወደ ገዳማት ይላክ ይቀመጥ። ከጦርነቱ ረሃቡ ይከፋል። ስለ ቅዱሳኑ ሲል ዘመኑ ያጥራልም ይላሉ።

••• አክሱም ጽዮን፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ጉንድ ተክለሃይማኖት፣ አሰቦት ሥላሴ፣ ደብረ ሊባኖስ

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: