Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

አቡነ ኤርምያስ | የቃየል ልጆች የያዙት መንግስት በቤተክርስቲያን ላይ ለሚፈጽመው ጥቃት እራሱ ተጠያቂ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 13, 2019

ከ ፫ ሚልዮን ምዕመናን በላይ በተገኙበት በግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓል ላይ የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ ትምህርት ሲሰጡ፦

ቤተ ክርስቲያን ተደፍራለች ፤ምእመናን ታርደዋል፡፡ እንደ ዘርዐ ያዕቆብ አይነት መሪ በመጥፋቱ አሁን ችግር ነው፡፡ ወንጌሉን እኛ እናስተምራለን፤ የሚያምጹትን መንግሥት መቅጣት ይገባዋል፡፡ እንግዳ ተቀብላ ወርቅ አበድራ መልሷ ግን ጠጠር ተመለሰላት፣ የኢህዴግ መንግስት ሊያስብበት ይገባል፡፡ የስም መለዋወጥ ሀገር አይለውጥም፤”እኔ የአቤል ጠባቂ ነኝ” ማለት አያዋጣም፡፡ መንግስት ስሙን እንጅ ግብሩን አልቀየረም፤ ዶክተር አቢይ ይህንን ቢያስተካክል ይሻላል የመንግስት አካል በጀት በጅቶ እቅድ አውጥቶ ፕሮግራም ነድፎ ቤተክርስቲያን እንድትቃጠል ንዋያተ ቅድስቱ እንዲነዱ ምዕመናን እንዲታረዱ ማድረግ፡ ቃየል አቤልን ገድሎ እግዚአብሔር ሲጠይቀው፤ እኔ የአቤል ጠባቂው ነኝ ማለቱ አላዳነውምና መንግስት ሊያስበት ይገባል ሲሉ እሳስበዋል። ምክርና ስብከት በቂ አይደለም፤ ስብከቱንም ማስተማሩንም ለእኛ ተውልን፤ እኛ እናከናውነዋለን። “ዛሬ እንደ ዘርዐ ያዕቆብ ያለ መሪ በማጣት ቤተክርስቲያን ችግር ላይ ናት” ካሉ በኋላም አባታችን አያይዘውም “ሶማሊያ ላይ የታረደው ገብረማርያም ማን ሊጠየቅበት ነው?” ይሉና “ካልሆነ ጠንከር ያለ ፓርቲ አዘጋጅቶ ማስረከብ ይሻላል!” ሲሉም ጠቁመዋል። “የገቢያ ግርግር ለብዙ ቀጣፊዎች ጠቅሟቸዋል፣ መንግሥት የያዘውን አካሄድ እንዲያስተካክልና ሕዝበ ክርስቲያኑ ኢትዮጵያን ደኅንነቷን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ አደራውን እንዲወጣ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃትም መንግሥት ሕግን ባለማስከበሩ የመጣ መሆኑን

በማሳወቅ ኃይለኛ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እግዚአብሔር በደመና ውስጥ ኾኖ “ቃየል ቃየል ወንድምኅ አቤል ወዴት ነው?” አለው፡፡ ቃየል ግን በትዕቢት ኾኖ “እኔ ምን አውቃለኹ፤ እኔ የወንድሜ የአቤል ጠባቂው ነኝን?” ሲል መለሰ፡፡ እግዚአብሔርም መልሶ “እንግዲኽ ጠባቂው ካልኾንኅ ስለምን ገደልከው? አኹንም ባለ ዘመን ኹሉ በምድር ኹሉ ላይ ድንጉጥና ተቅበዝባዥ ኹን” በማለት እግዚአብሔር ቃየልን ረገመው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቃየል በጣም ፈሪ፣ ሰዎችን የሚሸሽ፣ የሚጨነቅ፣ ባጠፋው ጥፋት እግዚአብሔርን የሚያፍር ኾኖ ኖረ፡፡

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]

ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።

ከማን አፍ ነው ይህን የሰማነው? አዎ! ኢትዮጵያን በቱርክ ባዛር ለመሸጥ ከተቀጠረው፣ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ፀረኢትዮጵያ ዘመቻውን በመጣጧፍ ላይ ከሚገኘውና በግብረሰዶማውያኑ ኢሉሚናቲዎች ከተሸለመው የቃየል ልጅ፤ ከገዳይ አብይ አፍ፦

አላየሁም! አልሰማሁም! እኔ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ነኝን? እኔ ቤተ ክርስቲያን አላቃጠልኩም: ካህናትን አልገደልኩም: ግፍ አልሰራሁም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ገዳይ አብይ በጣም ፈሪ፣ ሰዎችን የሚሸሽ፣ ቀጣፊ፣ የሚጨነቅ፣ ባጠፋው ጥፋት እግዚአብሔርን የሚያፍርና ብርሃኑን የሚፈራ ኾኖ ይኖራል። አቤት የእነዚህ የቃየል ልጆች መጨረሻቸው! እነርሱን አያድርገን!

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ብቻ እንጅ የሁሉም አይደለችም!

___________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: