Archive for September, 2019
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 13, 2019
እያንዳንዳችን ከጥምቀታችን ቀጥሎ በሚፈጸምልን ምሥጢረ ሜሮን አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ያድርብናል፡፡ ይህንን ተጠቅመን ሥራ ለመሥራት እኛም እንደ መጥምቁ የራሳችን በረሃ ያስፈልገናል፤ በትህርምትና ራስን በመግዛት መኖር አለብን፡፡
ይህንን ማድረግ የሚገባቸውና የሚችሉት በገዳም ያሉ ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ በዓለም የምንኖር ሰዎችም ብቻችንን የምንሆንበትና በጸሎት፣ በተመስጦ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ፣ ራሳችንን በመመርመር የምናሳልፈው ጊዜ በመመደብ መኖሪያ ቤቶቻችንን ገዳማት ማድረግ እንችላለን፡፡ ሁኔታዎችን እያመቻቸን ወደተለያዩ ገዳማት እየሄድን ጊዜ ማሳለፍም ጠቃሚ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ምግባችንን፣ መጠጣችንን እና ልብሳችንን በልክ እያደረግን መጥምቁን ባለ ብዙ ፍሬ በሆነበት ጎዳናው ልንከተለው ያገባናል፡፡
ሲሰርቁ፣ ሲያመነዝሩ፣ በዝሙት ሲወድቁ፣ ሲሰክሩ፣ ሲዘሉ፣ ሲያብዱና ሲያጨበጭቡ ከመሞት እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠብቀን!
የቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ይደርብን! አማላጅነቱ ይደረግልን!
______________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሄሮድስ, መጥምቁ ዮሐንስ, ቅዱስ ዮሐንስ, ነብዩ ኤልያስ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ዘመነ ዮሐንስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥምቀት, ፪ሺ፲፩, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, John The Baptist | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 12, 2019
የቅዱስ ዮሐንስ ክብር እና መዓርጋት
ቅዱስ ዮሐንስ ክብሩ በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ የክብሩ ምስክሮችም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል የመጥምቁን ክብር ተናግሯል፡፡
«ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጥታችኋል? ከነፋስ የተነሣ የሚወዛወዛውን ሸንበቆ ነው? ወይስ ምን ልታዩ መጥታችኋል ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን ነውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት አሉ? ምን ልታዩ መጥታችኋል ነቢይ ነውን? አዎን እርሱ ከነቢያት እጅግ ይበልጣል፤ እነሆ በፊትህ መንገድህን የሚጠርግ መልእክተኛዬን እልካለሁ ተብሎ ስለ እርሱ የተጻፈለት ይህ ነውና፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ሴቶች ከወለዷቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም» /ማቴ.11÷7-11/
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም እንዲህ ሲል ክብሩን ተናግሮለታል፡– «እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናል» /ሉቃ.1÷15/
የቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ይደርብን! አማላጅነቱ ይደረግልን!
____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሄሮድስ, መጥምቁ ዮሐንስ, ቅዱስ ዮሐንስ, ነብዩ ኤልያስ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ዘመነ ዮሐንስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥምቀት, ፪ሺ፲፩, Christmas, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, John The Baptist | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 7, 2019
ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ናትና ሃገራችንን አይተዋትም
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ
ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሲፈካ
ዝናም በሙቀት ሊተካ
ብርሃን ጨለማን ሲተካ
እንቁጣጣሽ፡ እንቁጣጣሽ!!
ደህና ጊዜን ይዘሽ ደግሞ ደግሞ ያምጣሽ።
እርቅ ነው ፍቅር ነው ለኛ አዲስ ዘመን፡
የሚታረቀውን እናቀናለን፡ አረሙን እንነቅላለን።
አዲሱ ፪ሺ፲ ዓመት
የበረከት፣ የፍቅርና የሰላም ይሁንልን
እንቁጣጣሽ
እንቁጣጣሽ በያመቱ ያምጣሽ!
እንኳን ከዘመነ ሉቃስ
ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላምና
በጤና አሸጋገረን!
መልካም አዲስ አመት!
ብሩክ አዲስ ፪ሺ፲፪ አመት – Happy Ethiopian New 2012 Year!
መጭውን ፳፻፲ ወ ፪ ዓ.ም አመት፡ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የደስታ ዘመን ያድርግልን !!!
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: አዲስ ዓመት, እንቁጣጣሽ, ዘመነ ዮሐንስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, Ethiopian New Year, Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 5, 2019
በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል /ጦቢት ፲፪፥፲፭/፡፡
ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡
የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል /ሄኖክ ፲፥፲፫/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” እንዳለ ሄኖክ /ሄኖክ ፮፥፫/፡፡
ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ለማኅፀን ችግር ኹሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት፣ በማኅፀን እያለ “ተሥዕሎተ መልክዕ” (በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡
አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል /ጦቢት ፫፥፰–፲፯/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል “ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ተብሎ እንደ ተጻፈ /ሄኖክ ፫፥፭–፯/ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው /ሄኖክ ፪፥፲፰/፡፡
የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር
የቅዱስ ሩፋኤልን ቤ/ክርስቲያን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈንድቶ የሞተው እዚህ ነበር፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይም ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት አንድ መስጊድ ተሠራ!
ከ 132 ዓመታት በፊት የዚህ ውብ ቤተክርስቲያን ህንፃ በተሠራ ማግስት አንድ ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት ይኖር የነበረ ጭራቅ/ጠንቋይ በየቀኑ እየመጣ ቤተክርስቲያኗን ካላፈረስኩ፣ ካላቃጠልኩ እያለ ለሳምንታት እያጓራ ሲዝት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እራሱ ፈንድቶ ሞተ።
ያው እንግዲህ፡ ልክ ጠንቋዩ በሞተበት ቦታ ላይ ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት (በ150 ሜትር ርቀት ላይ)መስጊዱ ተተክሎ ይታያል።
ሰይጣን ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅም!
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!
____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: 666, Addis Ababa, መላዕክት, መስጊድ, ቅዱስ ሩፋኤል, አዲስ አበባ, እስላም, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ዲያብሎስ, ጉለሌ, ጠንቋይ, ጭራቅ, ጳጉሜ ፫፥ ፪ሺ፲, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, St. Raphael Church | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 3, 2019
ቪዲዮው መጀመሪያ ክፍል ላይ የሚታየው ባለፈው ሳምንት ላይ የተቃጠለው የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን ነውን? የተሻለ መረጃ ያላችሁ፣ ጉዳዩን የምታውቁና ማረጋገጥ የምትችሉ ወንድሞች እና እህቶች ባካችሁ ጠቁሙን፤ መረጃው በጣም አስፈላጊ ነው።
ቪዲዮው የተሠራው “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ደኖችን ማዳን” „Saving Ethiopian Orthodox Church Forests“ የሚለውን ዘመቻ ለዓመታት በምታካሂደው አሜሪካዊት፡ በ ዶ/ር ማርጋሬት ሎውማን ነው (ከምስጋና ጋር)።
ነገሮች ሁሉ ተገጣጠሙብኝ፦ እንደ ዋልድባ ገዳማት በመሳሰሉት ጫካማ አካባቢ ፋብሪካዎች እንዲሠሩ ካዘዟቸው በኋላ የኢትዮጵያ ቤተከርስቲያን ደኖችን መጠበቅ አለብን የሚሉ ዘመቻዎችን ብዙ የውጭ ሰዎች በማካሄድ ላይ ናቸው። የዶ/ር ማርጋሬትን ሥራ ዝቅ ማድረጌ አይደለም፤ አስተዋፅኦ ታደርግ ይሆናል፣ ለበጎ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ደኖቿን ጠብቃ ያቆየችልን ቤተክርስቲያን እስከሆነች ድረስ ለምን ሙሉውን ኃላፊነት ለቤተክርስቲያኗ አይተውላትም?
በተለይ የ ግራኝ አብዮት አህመድ የ”ችግኝ ተከላ” ዘመቻ ተንኮል ያለበት መሆኑን ብዙዎች አሁን እየተረዱት ነው። ደን የምትንከባከበው ቤተክርስቲያን ሆና የምትቃጠለውም ቤተክርስቲያን ናት። እንደ አብዮት አህመድ ከሆነ፦
“ለዋቄዮ–አላህ መስዋዕት ከማድረጌ በፊት ለዛፉ ችግኝ መትከል አለበኝ፤ ለዚህም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩትን ኢትዮጵያውያን ማንቀሳቀስ እችላለሁ፤ ንጉስ ነኝ፣ ጁፒተር ነኝ ፥ ልጆቿ የተገደሉባትና የዕምነት ቦታዎቿ የተቃጠሉባት ቤተክርስቲያን ግን በጎቿን ማዘዝ እንኳን አትችልም፤ ዛፎቹና ደኖቹ የኛ/ኬኛ ናቸው”።
አዎ! ለዋቄዮ-አላህ ብዙ መስዋዕት በማቅረብ ላይ ስላሉ አምላካቸው ጊዜያዊ ድፍረቱን ሰጥቷቸዋል፤ ለዚህም ነው በቤተክርስቲያን ላይ ዕብደት የተሞላባቸውን ድርጊቶች በመፈጸም ላይ ያሉት።
„ኦሮሞ ነን” የምትሉ የተዋሕዶ ልጆች ከክርስቶስ ተቃዋሚው ፍዬል ጋር መደመር ካልፈለጋችሁ፡ ፈጥናችሁ “ኦሮሞነታችሁን” ካዱ!
________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መንፈሳዊ ውጊያ, ማርጋሬት ሎውማን, ስብጥር ጥናት, ችግኝ, አቡነ ተክለ ሐይማኖት, አብይ አህመድ, ኢትዮጵያ, ዛፍ, የብዝሃ ሕይወት, የአብያተክርስቲያናት ቃጠሎ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የደን ሥነ-ምሕዳር, ደቡብ ጎንደር, ደን, ጫካ, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, ፀረ-ኢትዮጵያ ሴራ, ፋርጣ ወረዳ, Ecology, Ethiopian Orthodox Tewahedo Churches, Forest Biodiversity, Margaret Lowman, Vegetation | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 1, 2019
ታሪካዊው ምስካየ ኅዙናን (የሐዘንተኞች መጠጊያ) መድኃኔ ዓለም ገዳም – ድንቅና ገነታማ የሆነ ቅጽር ግቢ። ዲያብሎስ ጠላታችንን በጣም ነው የሚያስቀናውና የሚያስቆጨው፤ ለዚህም ነው ጥቃት የሚፈጽምባቸው።
በ፲፮ ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ፤ በወቅቱ ነግሠው የነበሩት አፄ ልብነ ድንግልም ሆኑ
እሳቸውን የተኳቸው ነገሥታት፤ በጦርነቱ ምክኒያት በቅድስት ሀገር ለተቋቋሙ አብያተ ክርስትያናት ዕርዳታቸውን ስላቋረጡ፤ ካህናቱ የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ፣ ምግብ ባለማግኘታቸው፤ ገዳማቱን ግማሹን በአደራ ለአርመንና ለግሪኮች እየሰጡ፤ ሌሎቹን ደግሞ ዘግተው ወደ አውሮጳ ተሰደዱ፡፡
ከዓመታት በኋላ ተመልሰው ሲመጡ ግን ሁሉንም ለማግኘት ባይችሉም አሁን በእጃችን ያሉትን ይዘው አገልግሎታቸውን ቀጠሉ፡፡ ግራኝ ድል ሆኖ ጦርነቱ ከቆመም በኋላ፣ አንድ ወጥ መንግሥት የነበረው ቀርቶ የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ስለቀጠለና ፣ አሁንም በቂ ዕርዳታ ማግኘት ስላልቻሉ፤ ድርጎ፣ ልብስ፣ የመሳሰሉትን የሚያገኙት ከአርመንና ከግሪክ ገዳማት ነበር፡፡
በ፲፱ ኛ ክፍለ ዘመን የነገሡት ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ የወገኖቻችንን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ብለው ቋሚ ገቢ እንዲኖራቸው በማሰብ እዚያው ኢየሩሳሌም ውስጥ ሕንፃ ተሠርቶ የሚከራይበት መሬትና ተጨማሪ ሌላ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በሺ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓ.ም. በመግዛት አበርክተዋል፡፡ በዚያው ዓመት
የመድኃኔዓለምን ታቦት ዴር ሱልጣን መድኃኔዓለም በሚል ተሰይሞ መምህር ፈቃደ እግዚእ በተባሉ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳለም ልከው በዴር ሡልጣን ገዳም ለ፴፬ ዓመታት ሲቀደስበት ሲወደስበት ኖሯል፡፡
በስደት የነበረው ታቦት መድኃኔዓለም ነሐሴ ፳፫ ቀን ፲፱፴፫/1933 ዓ.ም. እቴጌ መነን ወደ አዲስ አበባ በተመለሱ ቀን፤ አባ ኃይሌ ቡሩክ ታቦቱን ይዘው ተመልሰው በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የአሁኑ የስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ጸሎት ቤት ውስጥ እያጠኑና እየጠበቁ ከቆዩ በኋላ፤ ሚያዚያ ፳፯/27 ቀን ፲፱፴፭/1935 ዓ.ም. የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተብሎ ተሰይሞ
በቀድሞ ቤተ ሳይዳ ቀዳማዊ ኃ/ሥለሴ ሆስፒታል አሁን የካቲት ፲፪ ቀን ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ተተከለ፡፡
የምስካየ ኅዙናን ትርጓሜ ለተበደሉትና ላዘኑት ማረጋጊያ ማጽናኛ ማለት ነው፡፡
አዎ! የዘመናችን ግራኝ አህመድ በለገጣፎ ያፈናቀላቸውን ወገኖቻንን መጠለያ የሰጣቸው የመድኃኔ ዓለም ቤተክስቲያን ነው፤ ለሙስሊሙ ሳይቀር። ቸሩ መድኃኔ ዓለም ሁሌም ለሁሉም በሩን ይከፍታል።
ምስካየ ኅዙናን (የሐዘንተኞች መጠጊያ) – መጠሪያ ስሙ ብቻ በጣም ይመስጣል፤ እግዚአብሔር የገዳሙን ደጅ መርገጥ ፈቅዶልኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነበር፤ ይገርማል የአዲስ አበባ ሰው ሆኜ፤ በጣም ከተደሰትኩባቸው ዕለታት መካከል አንዱ ነበር።
የምስካየ ኀዙናን መድኃኔ ዓለም አፄ ምኒልክ ታቦቱን ወደ ቅድስት ሀገር ልከው፤ ከዚያም በእንግሊዝ ሀገር በስደት ለብዙዎች መጽናኛ ሆኖ ቆይቶ ወደ ሀገራችን ተመልሶ እስከመጣበትና እስከ አሁንም ድረስ፤ ታሪካዊና፣ በሥራ ሂደቱ፣ በእንቅስቃሴው፣ ልዩ ልዩ ሥራዎችን በመጀመር ለሌሎች አብያተ ክርስቱያናት አርአያ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ገዳም ነው፡፡
ይህ ድንቅ ገዳም ወደፊትም የበለጠ ሥራ የሚሠራና፤ ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን የሚያኮራ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
መድኃኔ ዓለም ይህንን እና ሌሎቹን ገዳሞቻችንን እንዲጠብቅልን፤ ሀገራችንንም በበረከቱ እና ቸርነቱ እንዲጎበኝልን ዘወትር እንጸልያለን፡፡
ቸሩ መድኃኔ ዓለም የተበደሉትን፣ የተሰደዱትንና የሚጎሳቆሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያጽናናልን!
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መስከረም ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም, መድኃኔ ዓለም, ምስካየ ኅዙናን, ስደት, ቤተክርስቲያን, አዲስ አበባ, አፄ ምኒልክ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 1, 2019
በጣም አሳዛኝ ነው፤ መከራቸው በዛ፡ ወገኖቼ ፥ ነፍሳቸውን ይማርላቸው!
[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፬፥፲፯፡፲፰]
“የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።“
___________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሊብያ, መከራ, ሞት, ሰማእታት, ሰማዕታት, ቀብር, በረሃ, ተዋሕዶ ክርስቲያናት, ኢትዮጵያውያን, ኤርትራ, እንባ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ግድያ | Leave a Comment »