የምስራቅ ኦርቶዶክሱ ሊቅ | በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ደኖች መንፈሳዊ ቅናት ይሰማኛል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 19, 2019
ይህን የተናገሩት ካናዳዊው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዶ/ር ዴቪድ ጉዲን ናቸው።
Christology and Eco-Theology: Safeguarding Ethiopian Tewahedo Church Forests
Dr. David Goodin (Canada) presents “Christology and Eco-Theology: The Centrality of Cyril of Alexandria in Safeguarding Ethiopian Tewahedo Church Forests” at the Inaugural Conference of the International Orthodox Theological Association (IOTA), with the theme Pan-Orthodox Unity and Conciliarity, held January 9 to 12, 2019, in Iasi, Romania.
+ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አሁን ማሕበረሰባቸውን ለማበረታት ደኖቻቸውን ለማስፋፋት እየሞከሩ ነው፤ይህም አበረታች የሆነ ተግባር ነው።
+ በኢትዮጵያ ጫካማ የሆነ ቦታ ካየን፥ መሀከል ላይ በርግጥ ቤተክርስቲያን እንዳለ የማወቅ እድል ይኖረናል።
+ ደኖቹ የመጠለያ፣ ፀሎት የማድረጊያ እና የመቃብር ቦታዎች ሆነው ያገለግላሉ።
+ አብዛኛው የአገሪቱ ጫካ እያደገ የመጣውን የአገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ለመመገብ ሲባል ለግብርና መስዋእትነት ወስዷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ 100 ሚሊዮን በላይ ነው፣ ይህም በዓለም 12 ኛ ደረጃ ትልቁ ነው። በተለይ ከ 1974-1991 ዓ.ም በሀገሪቱ የኮሚኒዝም ሥርዓት፡ በ “መሬት ለአራሹ” ዘመን፡ የደን ጭፍጨፋው አሳዛኝ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፤ በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰፋፊ ቦታዎች በመውረስ ደኖቻቸውን እየመነጠሩ ለእርሻ እንዲውሉ አድርገዋቸዋል። በአሁን ዘመን በአገሪቱ 5% ብቻ በደን የተሸፈነ ሲሆን፤ በሀያኛው ክፍለ ዘመን እስከ 45 በመቶ ነበር።
+ ምን ያህል ስብጥር እንደጠፋ በውል አናውቅም ፥ ነገር ግን ከጠበቅነው በላይ በጣም ጉልህ የሆነ የስብጥር መጠን መትረፉን እናውቃለን።
+ የደን ብዝሃ–ህይወት ስብጥርን መጠበቅ ለእርሻ በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም በዓብያተ ክርስቲያናቱ ጫካዎች ውስጥ የሚኖሩት ብዙዎቹ ወፎች እና ነፍሳት ሰብሎችን ለማዳቀል እና ተባይን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉና ነው።
+ ከግማሽ በላይ ለሚሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች እናት የሆነችው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ደኖቿ የሰማይ መንግስትን በምድር ላይ የሚወክሉ ናቸው፤ እያንዳንዱ ፍጥረት የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ መኖሪያ ይፈልጋል።
+ የተፈጥሮ አካባቢዎች መንፈሳዊ ክልል አካል የሆኑት እነዚህ ደኖች በባህልና በሳይንሳዊ መልኩም በጣም አስፈላጊ ናቸው።”
Leave a Reply