እነ ሞዛርት ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በኢትዮጵያችን ተወለደ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 15, 2019
አውሮጳውያኑ የዜማ ሊቃውንት ሞዛርትና ቤትሆቨን ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ በኢትዮጵያችን የተወለደ ነው ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ። ጻድቁ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም ጽዮን አቅራቢያ ሲሆን አባቱ ይስሐቅ (አብድዩ ) እናቱም ክርስቲና (ታኡክልያ) ይባላሉ።
“ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “
ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን:
ክብራችን: ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን?
አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም): ልቡናው የቅድስና ማሕደር:
ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: እስከ አርያም
ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ!
+ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- “ቅዱስ ያሬድ
ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ
ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ: ሙሉ አካሏ ነው“
የጻድቁ ረድኤትና በረከት ከሀገራችን ከኢትዮጵያና ከህዝቧም ጋር ይሁን አሜን።
Leave a Reply