Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2019
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    30  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for September 5th, 2019

ቅዱስ ሩፋኤልን ሰይጣን አይችለውም | ሰማያት ተከፈቱ፤ የምሕረት ዓመቱ በር ተከፈተ ደስ ይበላችሁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 5, 2019

በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል /ጦቢት ፲፪፥፲፭/፡፡

ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሩፋኤልየሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡

የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነውበማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል /ሄኖክ ፲፥፲፫/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነውእንዳለ ሄኖክ /ሄኖክ ፮፥፫/፡፡

ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ለማኅፀን ችግር ኹሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት፣ በማኅፀን እያለ ተሥዕሎተ መልክዕ” (በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡

አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል /ጦቢት ፫፥፰፲፯/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለውተብሎ እንደ ተጻፈ /ሄኖክ ፫፥፭/ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው /ሄኖክ ፪፥፲፰/፡፡

የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር

የቅዱስ ሩፋኤልን ቤ/ክርስቲያን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈንድቶ የሞተው እዚህ ነበር፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይም ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት አንድ መስጊድ ተሠራ!

132 ዓመታት በፊት የዚህ ውብ ቤተክርስቲያን ህንፃ በተሠራ ማግስት አንድ ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት ይኖር የነበረ ጭራቅ/ጠንቋይ በየቀኑ እየመጣ ቤተክርስቲያኗን ካላፈረስኩ፣ ካላቃጠልኩ እያለ ለሳምንታት እያጓራ ሲዝት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እራሱ ፈንድቶ ሞተ።

ያው እንግዲህ፡ ልክ ጠንቋዩ በሞተበት ቦታ ላይ ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት (150 ሜትር ርቀት ላይ)መስጊዱ ተተክሎ ይታያል።

ሰይጣን ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅም!

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!

____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: