Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2019
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    30  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for September, 2019

የነጮች ድፍረትና ግድየለሽነት | ዳሎል ላይ በቁምጣ ሱሪ እና በባዶ እግሯ ሽርጉድ ትላለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 30, 2019

ምነው ነጮች ወደ አፋር መጓዝ አዘወተሩ? ምን አግኝተው ይሆን? ይህች የሃምስት ዓመት ኒውዚላንዳዊት በአፋር በአደገኛው ሰልፈር በተሸፈነውና ለአይን በሚማርከው ዳሎል በቁምጣ ሱሪ እና በባዶ እግሯ እየተራመደች ትታያላች። ይህ ቦት ከሩቅ ሆኖ እንኳን ቦታውን ለማየት በጣም የሚሞቅ በርሀማ ቦታ ነው። ይህች አትኩሮትፈላጊ የኢንስታግራም ባሪያ ቀደም ሲል እዚሁ አካባቢ ኩሬ ውስጥ ስትዋኝ ታይታ ነበር። ሞት እየጠራት ይሆን?

_____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos, Photos & Videos | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

ደመራ በዓል | የተዋሕዶ ልጆች የሚደመሩት ከቅድስት ማርያም እና ከክቡር ልጇ ጋር ብቻ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 25, 2019

ደመራው ተለኮሰአረንጓዴቢጫ ቀይ አበራ፤ ጨለማውም በብርሃን ተጋለጠ!

መስቀል ማለት ምን ማለት ነው?

ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ” (ማቴ. 16:24-26)

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቃል መነገሩ፣ በኅሊና መዘከሩ፣ በሰው ልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ይበልና፣ ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆቹ ፈቃዱን እያደረግን እንድንኖርና እርሱም ከመልካም ምግባራችንና ከበጎ ትሩፋታችን ብቻ የተነሳ ፍጹማን እንደማንሆን ያውቃልና፣ ከማያልቅ ልግስናው ከማይጓደል ምሕረቱ ዘመናትን እየመጸወተን ደስ የሚሰኝበትን ለእኛ እያደረገ በቸርነቱ ያኖረናል:: ከእርሱና ከዓላማው ጋር ጸንተን እንድንኖርም እንዲህ ሲል በቅዱስ ወንጌል አዝዞናል:: “ዘይፈቅድ ይትልወኒ ይጽላዕ ነፍሶ ያጥብዕ ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ (እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ) ወምንተ ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጉለ (ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?)” (ማቴ. 16:24-26)

ጥንቱንም ቢሆን እኛ የተፈጠርነው በሕይወት እንድንኖር ነው። ትንሳኤና ሕይወት ክርስቶስ ግን የተወለደው ስለኛ እንዲሞት ነው:: በዚህም ሁላችን ለእርሱ እንድንኖር እርሱ ስለ ሁላችን ሞተ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። “(1ቆሮ፣ 5:15)። ይህ ግን መስቀል የገደለው ያይደለ ይልቁንም በመስቀሉ ሞትን ገደለበት እንጂ:: “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።” (ፊል. 2:8) እንዲል::

ሊከተለኝ የሚወድ ነፍሱን ይጥላ አለ፣ ይህም ነፍሱንና ሥጋውን የሚለይ መከራ ለመቀበል ይጨክን ሲል ነው። ሰውስ ለክርስትና ፍኖቱ ለነፍሱ ሥምረት እያደረ የሥጋውን ፈቃድ እየገፋና እየጠላ ሊኖር ይገባዋል። ለዚህም ጌታችን ተከታዩን ሃሳብ እንዲህ ሲል አስፍሮታል ወምንተ ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጉለ፤ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” መከተሉም ቢሆን ሌጣውን ያይደለ የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይለናል::

መስቀል ምንድር ነው ?

መስቀል በቀደመው ዘመን ለኃጢአተኞች እግዚአብሔርን ለበደሉ መቅጫ የነበረ በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና” (ዘዳ፣21:23)። ነገር ግን በአዲስ ኪዳን ለክርስቲያኖች ኃይል፣ ጽንዕ፣ ቤዛና መድኃኒተ ነፍስ ሆኖ የሚያገለግል አርማ ነው:: ወደዚህ ክብር እንዴት ሊሻገር እንደቻለ ሊያስረዱ የሚችሉ በመስቀሉ ከተፈጸሙ ድንቅ መንክራት እፁብ ተዓምራት መካከል ተከታዮቹን ሦስት ዓበይት ነጥቦች እንደእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እንመለከታለን::

+ ጠላት የራቀበት ነው።

መስቀል የቀደመው እባብ የዲያቢሎስ ራስ የተቀጠቀጠበት እኛም ድል መንሳትን በግልጥ ያየንበት እጸ መድኃኒት ነው:: “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ (በመስቀል) እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” (ቆላ፣ 2:14) እንዲል።

+ እኛ የቀረብንበት ነው።

ተመልከቱ ራሱን ወደኛ ያቀረበበት ነው አላልንም አመ ተለአልኩ እምድር እስህብ ኩሎ ኃቤየ፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።” (ዮሐ፣12:32) እንዳለ እኛን ወደራሱ አቀረበበት፣ ምክንያቱም ሰው በድሎ ራቀው እንጂ እርሱ ከሰው የተለየበት ጊዜ አልነበረምና። እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም።” (ኤር፣23:23) እንዳለን። ይበልጡንም ለተዛምዶ ረቂቅ ቅርበቱ ያይደለ ሥጋችንን ነስቶ አማኑኤል ተሰኝቷል። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ።ይህም በኩነት ታዲያ ዓላማው ወደእኛ መቅረብ ብቻ ቢሆን ይህ ልደቱ በበቃው ነበር። መስቀሉ ግን ወደኛ መምጣቱን ባንቀበል ወደራሱ ሊወስደን ወደ ሰማይ ቤታችን ሊስበን በቀራንዮ ተተከለ። ለዚህም ሊቁ ማር ኤፍሬም አቅረበነ ኃቤሁ ዘዚአነ ሞተ ነሳ ወእንቲአሁ ሕይወተ ወኃበነወደራሱ አቀረበን የእኛን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠንሲል መነሻችንን ያስረዋል።

+ የጥል ግድግዳ የፈረሰበት

ሰው የሞትን እጽ ቆርጦ ቢበላ አምላኩን በደለ። በዚህም የጸብ ግድግዳ ተተከለ። ሰው ከአምላኩ ተለየ ልዑለ ቃል ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።” (ኢሳ፣59:2) ሲል እንደገለጸው፣ ታዲያ ከህገ ልቡና ወደ ህገ ኦሪት መሻገሩ ፍጻሜ ያለው ድኅነት ሊያመጣ ባለመቻሉ የሚበልጥና የሚሻል አዲስ ኪዳን የሚሰጥበት አዲስ መስዋዕት የሚሰዋበት አዲስ ድንኳን አስፈለገ (ዕብ፣ 9:11)። ለዚህም የአዲስ ኪዳን ሥርዓት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት የሕይወት ህብስት ቅዱስ ሥጋው የተቆረሰበት ዐረፍተ ማእከል የተናደበት እጸ መድኃኒት ቅዱስ መስቀሉ ተሰጠን። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።” (ኤፌ፣ 2:15)

እንግዲህ በጠቅላላው መስቀል የምንለው፣ በቁሙ ከቤተክርስቲያን ጉልላት እስከ ምዕመናን ንቅሳት የሚታይ የድል ምልክት፣ በሰሌዳ ተስሎ በጣት ተመሳቅሎ የሚገኝ የድኅነት አርማ፣ ካህናት በእጃቸው ይዘው የሚፈቱበት፣ ክርስቲያኖች በአንገታቸው አስረው ማንነታቸውን የሚመሰክሩበት መገለጫ ሲሆን. በሌላ አገባብ መከራ የተጋድሎ ፍኖት ማለት ነው።

እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ስለሁላችን መዳን መከራን ተቀብሎልናል። እናስተውል፣ እያንዳንዳችን በመዳን ኑሮ ሐሳባችን፣ እቅድ ምኞታችን በመከራው ልንካፈለው፣ በሞቱ ልንመስለው ፈለጋውን ልንከተለው ይገባናል።

ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ። “(ዕብ፣13:12) እንደተባለ፤ ከበር ውጪ አለ በቀራንዮ ኮረብታ የራስ ቅል በተባለ ጎልጎታ ሊቀድሰን ተሰቀለ። እኛ ክርስቶስ በደረሰበት መከራ ከድቅድቁ ጨለማ ድንቁርና ወደሚደነቀው ብርሃን እውቀት የተሻገርነው፣ ስለ አዳም በደል መከሰስን ጥለን ስለራሳችን ጽድቅ መከራን በመቀበል እንድንከተለው ነው:: ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። “(1ኛ፣ጴጥ.2:21) ሲል እንዳስረዳን። በዚህም ኅሩይ ነዋይ ቅዱስ ጳውሎስ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። “(ፊል.3:10-11)። ሲል ምኞቱን አስረዳን ምን ይጠቅማል? የሚል ቢኖር ልሳነ ዕፍረት እንዲህ ያስረዳዋል ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።” (ሮሜ. 6:5)

ሁሉ የራሱ መስቀል አለው ሸክሙን የሚሸከምበት

ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።” (ሉቃ፣9:23)

ሁሉ የራሱን ሸክም ይሸከማልና

ወኩሉ ያመክር ምግባሮ (ሁሉ ሥራውን ይመርምር ለሌላው ሳይሆን ለራሱ የሚመካበትን) እስመ ኩሉ ፆሮ ይፀውር (እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና)” (ገላ6:5) እንዲል።ስለዚህ የምንሸከመው መስቀላችን የምንሰቀልበት ሳይሆን ሸክማችንን የምንሰቅልበት ነው::”የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።” (ገላ፣ 5:24) እንደተባለ።

እስኪ አእምሮአችንን ከመባከን ሰብስበን ነፍሳችንን የሚያሳርፍ አንድ ታሪክ እናንብብ

እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና። ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው።እርሱም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው።ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና። አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፥ ተከተለኝ አለው።ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ።” (ማር 10:17)። አይገርማችሁም በምድራችን ላይ ገንዘብን መውደድ የከበደ ሸክም እየሆነባቸው ገፋኤነዳይ መፍቀሬነዋይመጠርያቸው የሆኑ ብዙዎች አሉ:: ፍቅረ ነዋይ (ገንዘብን መውደድ) ለኃጢዓት ሥርና ራስ ነው …… ጌታችን ተርቦ ሳይሳሳ፣ ተፈትኖ ድል ሳይሆን፣ ለሁላችን አርአያ በሆነበት ገዳመ ቆሮንቶስ ጠላታችንን ድል ከነሳባቸው መንገዶች አንዱ ፍቅረ ነዋይን በጸሊዓ ነዋይ ነበር። ይህም ፍቅረ ነዋይ ርዕሰኃጣውእ ከስስትና ከትዕቢት ጋር አርዕስተ ኃጥውእ እየተባለ ይጠራል። ይሁንና ግን ከአስራ ሁለቱ አንዱ በሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ገብቶ ተሳካለት። በዚህ ሥፍራ ደግም የኃጢዓት ሥር ተብሎ ተጠራ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።” (1.ጢሞ.6:10) እንዲል። እንግዲህ ይህን የመሰለው ኃጢዓት ሁሉ ክቡድ ሸክም ይባላል። የምሕረት አምላክ ግን በፍቅር ልሳን እንዲህ እያለ ይጠራናል እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።” (ማቴ.11:28-30)

ቀሊል የሆነውን የእርሱን ሸክም እንሸከም ዘንድ እሱ የኛን ክቡድ ሸክም በመስቀል ላይ ተሸከመ:: እንግዲህ ተመልከቱ በዚህ መንገድ እኛም ሕይወታችንን እንድንሰጠው ሕይወቱን ሰጠን ለምን? የሚል ቢኖር እርሱ የብዙዎችን ኃጢዓት በእንጨት ላይ የተሸከመው ብዙዎች የእርሱን ሕይወት በዘመናቸው እንዲሸከሙ ነውና:: ነቢዩ አስቀድሞ በትንቢት እንዲህ እንዳለ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።” (ኢሳ 53:12) ሊቀሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም የቃሉን መፈስጸም እንዲህ ሲል እንዳስረዳ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤” (1.ጴጥ፣2:24)

መከራን መቀበል (መስቀላችንን መሸከም)

+ ኃጢዓትን (አርእስተ ኃጣውእ) ያስተዋል።

በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና።” (1ጴጥ፣ 4:2)

+ ወደ እግዚአብሔር ያስገባል።

ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (ሐዋ 14:22) እንደተባለ ለብዙዎች ዘለፋ የሆነው ይህ የቅዱሳን ሐዋርያት ምስክርነት በጸጋ ድነናልእያሉ ባልተገባ ፍካሬ ቃሉን እየጠቃቀሱ፤ ለመብልና መጠጥ ይህን ለመሰለው የሥጋ ፈቃድ ራሳቸውን ለሚያስገዙ ጅራፍ ይሆንባቸዋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።” (ሮሜ.14:17) ይለናልና::

ማጠቃለያ

ቅዱስ አባታችን ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸው ፈተና ያለው ትምህርት ቤት አይደለም፣ ይልቁንም ትምህርት ቤት ያለው በፈተና ውስጥ ነውብለዋል። እኛም እንዲህ እንላለን ሕይወት በመከራ የተሞላ ነው ለሚል፣ የለም ለክርስቲያንስ መከራ በህይወት የተመላ ነው እንጂ፤ ሊቁ መከራ ኢርኅቀ እምርዕሰ ጻድቃን ወርዕሰ ጻድቃን ኢርኅቀ እምነ መከራ ግሩም.” ሲል ቅኔውን ይጀምራል። የማይጠፋ ስምና የሕይወትን አክሊል ገንዘብ ሊያደርጉ ሲሹ መከራ አይርቃቸውም። ቢርቃቸውም እንኳ እነርሱ ከመከራ መች ይርቁና። መክበርያቸውን ሽተው ራሳቸው ላይ ተጋድሎ ያጸናሉ ሌላውም ሊቅ የጸናውን ሰማዕት ተመለከተና ኦ ጊዮርጊስ ስቃየ ኮንከ ለሥቃይከሲል አደነቀ እንዴት ባለ መከራ እንዲገድሉት ይጨንቃቸው የነበሩ አላውያን ቢፈጩት፣ ቢያቃጥሉት፣ አመድ አድርገው ቢበትኑት እነሆኝ የክርስቶስ ባርያእያለ ሞትን ድል ቢነሳና ከመካከላቸው ቢገኝ ለስቃዩ ስቃይ ሆነበት ወይግሩም! ታዲያ የቀደሙ ምስክሮች ሕይወት ይህ ከነበረ የእኛ ተጋድሎ ወዴት ይሆን? “ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?” (1.ጴጥ.4:18)

እንግዲህ በሁሉ እናመስግን በፈተናችን ዋጋ በመከራችን ጸጋ እንድንቀበል እያሰብን ይህን እንጸልይ ኦ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ አአኩተከ በእንተ ኩሉ ግብር ዘአምጻእከ ላዕሌየ እመሂ ረኃበ አው ጽጋበ እመሂ ጥኢና አው ደዌ እመሂ ፍሰሐ አው ኃዘነጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእኔ ላይ ስላመጣህብኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ ረሃብ ቢሆን፣ ጥጋብ ጤንነት ቢሆን፣ ደዌ ደስታም ቢሆን ኃዘን“( ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ)

መስቀሉን የሚሸከም ምረረ ገኃነምን ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን እየተዘከረ በመከራው ይደሰታል እንጂ አይማረርም። የጌታችን ወንድም የተሰኘ ራሱን የክርስቶስ ባርያ እያለ የጠራ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ የመጀመርያ ምዕራፍ ቁጥር 2 እና 3 ላይ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩትይለናል እኛም ከሐዋርያው ጋር እንዲህ እንላለን ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።” (ሮሜ፣ 8:18)

+++ ከፍኖተ መስቀሉ ከህያው ቅዱስ ቃሉ በረከት ይክፈለን። +++

መስቀል ኃይላችን ነው!

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | 1 Comment »

የተአምረኛው ቅዱስ ሚካኤል ፀበል | የተጠመቅኩት ለአመኑኝ ሁሉ በረከትና ድኽነት ለመስጠት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 23, 2019

የተጠመቅኩት፣ በመሰቀል የተሰቀልኩትና የተሰዋኹት ለአመኑኝና ቃሌን ለተቀበሉኝ ሁሉ ለስጋቸው በረከት ለነፍሳቸው ድኽነት ለመስጠት ነው!”

ለእያንዳንዱ ለተጠመቀው ክርስቲያን፣ ስጋው ለተቆረሠለት፣ ደሙ ለፈሰሰለትና እግዚአብሔር ሰው ለሆነለት ክርስቲያን ጠባቂ መላእክት አሉት።

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጣዖት ማምለክ እንዲህ ያጣምማል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 22, 2019

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

አባታችን ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ከሠላሣ ዓመታት በፊት ያስተላለፉልን ዛሬም ወቅታዊ የሆነ ድንቅ መልዕክት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 22, 2019

መላው ዘመናቸውን ኢትዮጲያዊነታቸውን ተንከባክበውና ጠብቀው፣ ያለ ሱፍና ከረባት አለባበሳቸውን አሳምረው፣ የእንግሊዝኛው ቋንቋ በአማርኛው መሃል እየገባ ሳያሰናክላቸው ጥርት ባለ ኢትዮጵያኛ ለኢትዮጵያ ቆመውና ኢትዮጵያውያንን በእውቀት መግበው ወደ ሚቀጥለው ሕይወት አልፈዋል።

አዎ! ያለተዘመረላቸው ድንቁ አባታችን ለምሳሌ የሚከተለውን ተናግረው ነበር፦

ኢትዮጵያ እንኳን ዜጎቿን “ኢትዮጵያዉያን ነን” የሚሉትን ቀርቶ የዓለምን ሕዝብ ትመራለች ብንላችሁ “ኡ!!“ልትል ስለምትችሉ የንስሐ እድሜ ካገኛችሁ ተፈጽሞ እንደምታዩ እንነግራችኋለን። በዓመጻችሁ ጸንታችሁ ከተጠረጋችሁ ደግሞ ቅኖችና የዋሃን ትዉልዶች እንደሚያዩት በእግዚአብሔር ስም እናረጋግጥላችኋለን። እንደ እናንት የእግዚአብሔርን ኃይል የምንጠራጠር አይምሰላችሁ። እግዚአብሔር፤ ንጉሡ ሰናክሬም የተመካባቸዉንና የተማመነባቸውን 185000 (አንድመቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ” ሠራዊት በዐይን ቅጽበት ዉስጥ እንዳልነበሩ አድርጎ እንዳረገፋቸዉ ከመጽሐፍ ቅዱስ አላነበባችሁምን? ሲወራስ አላዳመጣችሁምን?

እግዚአብሔር አሁን በኛ ዘመን ኃጢአት እጅግ በነገሠበት ወቅት ደግሞ 185000 አይደለም 1850000000 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን)ሠራዊት በዐይን ቅጽበት ዉስጥ ማርገፍ የሚያቅተው ይመስላችኋልን? እናንተ ሆናችሁ በዓለም ዉስጥ ያለው ትዉልድ ማንም ይህን ማን በዓመፃዉ ከጸናና እጁን ለእግዚአብሔር አልሰጥ ካለ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ አመጸኛ ትዉልድ ረግፎ እንደ ኖኅና ቤተሰቡ ቅንነት፥ የዋህነት፥ እዉነተኛነት የተላበሱትን ሰዎች ብቻ የማያስቀር ይመስላችኋልን?

ስለዚህ “ሠራዊቱ፣ ድኅንነቴ፣ ጠባቂዬ፣ ዘሬ፣ ጎጤ ኃያላን መንግሥታት፤ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረትወዘተ” የሚባሉት እንኳን እናንተን ራሳቸውንም ማዳን እንደማይችሉ በዚሁ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ከእግዚአብሔር ቁጣ ሊድኑ የሚችሉት በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ሲሰጡና በኢትዮጵያ በቅርቡ እግዚአብሔር ለሚዘረጋው መንግሥቱ ለሥጋዊዉም ለመንፈሳዊዉም ሥርዓት ተገዥ ሲሆኑ ብቻ ነዉ። በተቀረ ግን የዓመጻ፣ የክህደት፣ የርኩሰት ጽዋቸዉን እያንዳንዱ መንገሥት፣ ቡድን ፣ ድርጅት፣ ግለሰብ እየጠጣ ነጻነቱ ተገድቦ ወደሚኖርባትና እንደ ዓመጻው ደረጃ ፍዳዉን ወደሚቀበልበት ቦታ መሄድ ነዉ የሚቀረዉ። ይህን ሁሉ የተናገርነዉ መቺስ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ ብለን በማሰብ ሳይሆን የእናንተ ልበ ደንዳናነት ቢታወቅም ባለማወቅ በቅንነትና በየዋህነት አብሮዋችሁ የተሰለፉ ሰዎች ካሉ ከዛሬ ጀምሮ ከእናንተ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲፈጥሩ፣ እንዲሁም በእዉነተኛ ንስሐ እንዲመለሱ ለማሳሰበ ነኡ።” በማለት ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቱን አቀርባለሁ።”

ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ

______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

ልዩነት ውበት መሆኑን ቤተክርስቲያን ብቻ ነች የምታሳየው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 20, 2019

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life, Love | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የምስራቅ ኦርቶዶክሱ ሊቅ | በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ደኖች መንፈሳዊ ቅናት ይሰማኛል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 19, 2019

ይህን የተናገሩት ካናዳዊው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዶ/ር ዴቪድ ጉዲን ናቸው።

Christology and Eco-Theology: Safeguarding Ethiopian Tewahedo Church Forests

Dr. David Goodin (Canada) presents “Christology and Eco-Theology: The Centrality of Cyril of Alexandria in Safeguarding Ethiopian Tewahedo Church Forests” at the Inaugural Conference of the International Orthodox Theological Association (IOTA), with the theme Pan-Orthodox Unity and Conciliarity, held January 9 to 12, 2019, in Iasi, Romania.

https://www.ancientfaith.com/specials/iota/50_christology_and_eco_theology_safeguarding_ethiopian_tewahedo_church_fore

+ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አሁን ማሕበረሰባቸውን ለማበረታት ደኖቻቸውን ለማስፋፋት እየሞከሩ ነው፤ይህም አበረታች የሆነ ተግባር ነው።

+ በኢትዮጵያ ጫካማ የሆነ ቦታ ካየን፥ መሀከል ላይ በርግጥ ቤተክርስቲያን እንዳለ የማወቅ እድል ይኖረናል።

+ ደኖቹ የመጠለያ፣ ፀሎት የማድረጊያ እና የመቃብር ቦታዎች ሆነው ያገለግላሉ።

+ አብዛኛው የአገሪቱ ጫካ እያደገ የመጣውን የአገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ለመመገብ ሲባል ለግብርና መስዋእትነት ወስዷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ 100 ሚሊዮን በላይ ነው፣ ይህም በዓለም 12 ኛ ደረጃ ትልቁ ነው። በተለይ ከ 1974-1991 .ም በሀገሪቱ የኮሚኒዝም ሥርዓት፡ በ “መሬት ለአራሹ” ዘመን፡ የደን ጭፍጨፋው አሳዛኝ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፤ በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰፋፊ ቦታዎች በመውረስ ደኖቻቸውን እየመነጠሩ ለእርሻ እንዲውሉ አድርገዋቸዋል። በአሁን ዘመን በአገሪቱ 5% ብቻ በደን የተሸፈነ ሲሆን፤ በሀያኛው ክፍለ ዘመን እስከ 45 በመቶ ነበር።

+ ምን ያህል ስብጥር እንደጠፋ በውል አናውቅም ፥ ነገር ግን ከጠበቅነው በላይ በጣም ጉልህ የሆነ የስብጥር መጠን መትረፉን እናውቃለን።

+ ደን ብዝሃህይወት ስብጥርን መጠበቅ ለእርሻ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በዓብያተ ክርስቲያናቱ ጫካዎች ውስጥ የሚኖሩት ብዙዎቹ ወፎች እና ነፍሳት ሰብሎችን ለማዳቀል እና ተባይን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉና ነው።

+ ከግማሽ በላይ ሚሆኑት ኢትዮጵያ ሕዝቦች እናት የሆነችው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ደኖቿ የሰማይ መንግስትን በምድር ላይ የሚወክሉ ናቸው፤ እያንዳንዱ ፍጥረት የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ መኖሪያ ይፈልጋል

+ የተፈጥሮ አካባቢዎች መንፈሳዊ ክልል አካል የሆኑት እነዚህ ደኖች በባህልና በሳይንሳዊ መልኩም በጣም አስፈላጊ ናቸው።”

______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ደኖችን የሚያሳዩት ምስሎች ዝነኛውን የዓለም-አቀፍ የፎቶግራፍ ሽልማት አገኙ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 18, 2019

በኢትዮጵያ እየቀነሰ ለመጣው የብዝሃ ሕይወት የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ደኖች የመጨረሻው መጠለያ መሆናቸውን የሚያሳዩት የሚያሳዩት ምስሎች የዘንድሮውን ሶኒ ዓለም አቀፍ የፎቶግራፍ ሽልማት አገኙ። በስኮትላንዳዊው ፎቶ አንሽ ኬይረን ዶድስ የተቀረጹት እነዚህ ምስሎች “ሄሮቶፒያ” በሚል ስያሜ በዚህ ከፍተኛ ደረጃ ባለው ዓለም አቀፍ የፎቶ ውድድር ላይ ቀርበው ነበር

መላው ዓለም በተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ አትኩሮት በማድረግ ላይ ነው!

___________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Photos & Videos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እነ ሞዛርት ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በኢትዮጵያችን ተወለደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 15, 2019

አውሮጳውያኑ የዜማ ሊቃውንት ሞዛርትና ቤትሆቨን ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ በኢትዮጵያችን የተወለደ ነው ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ። ጻድቁ የተወለደው በ505 /ም አክሱም ጽዮን አቅራቢያ ሲሆን አባቱ ይስሐቅ (አብድዩ ) እናቱም ክርስቲና (ታኡክልያ) ይባላሉ።

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን:

ክብራችን: ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን?

አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም): ልቡናው የቅድስና ማሕደር:

ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: እስከ አርያም

ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ!

+ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- “ቅዱስ ያሬድ

ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ

ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ: ሙሉ አካሏ ነው

የጻድቁ ረድኤትና በረከት ከሀገራችን ከኢትዮጵያና ከህዝቧም ጋር ይሁን አሜን።

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Music | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

በየቦታው አገር የሚያጠፉት ክፉ መካሪዎች ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 14, 2019

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» /ማቴ.3÷5-6/ እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመልካም ምክር እንዲያገናኘን ክፉውን እና መልካሙን ምክር እንድለይ ማስተዋሉን እንዲሰጠን ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን!

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: