ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ “ኃይለኛ የሆነ አውሎ ነፋስ ሊመጣብን ነውና አደጋ ላይ ነን ፣ እንተባበር ለክፉው ሁሉ አብረን እንዘጋጅ” ሲሉ ፥ ግራኝ አብዮት አህመድ ግን፤ “ቤተክርስቲያን ወደፊትም ትቃጠላለች ምንም ማድረግ አንችልም፤ ቻሉት! ተቀበሉት!” ይለናል። ቤተክርስቲያን እየተቃጠለች ነው፤ ሃገር እየነደደች ነው፤ ግራኝ አብዮት አህመድ ግን በባዕዳውያን ሃገራት እየተንሸራሸረ ነው።
እኛ ግን ስለጽዮን ዝም አንልም!
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፷፪፥፩]
“ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።”
[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፪፥፭]
“እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።”