በተክለ ሐይማኖት ዕለት ሌላ አሳዛኝ ዜና | በ ጎንደር የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን ተቃጠለ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2019
በደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል።
የአከባቢው ነዋሪ እንደገለጸው ከሰሞኑን ለነዋሪው እንግዳ የሆኑ ሰዎች መታየታቸውን እና ምንም አይነት ሌላ ምክንያት እንደሌለው ገልጸዋል። ቤተክርስቲያኑ ሙሉ ለሙሉ በእሳት ወድሟል።
ስንት አባቶች፣ እናቶች፣ ሕፃናት እና አገልጋዮች መገደል አለባቸው ግራኝ አብዮት አህመድን ለመቅጣት? ስንት አብያተክርስቲያናት መቃጠል አለባቸው ለሰላማዊ ሠልፍ ለመውጣት?
ተክልዬ አባቴ ሆይ፤ ይህንን መቅደስህን ሆን ብለው እሳት በለኮሱት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ላይ በእውነት አባታችን አንተ ማጥ ልቀቅባቸው።
የአባታችን የአቡነ ተክለ ሀይማኖት ምልጃና ጸሎታቸው ረድዔትና በረከታቸው በኛ በልጆቻቸው ላይ ይደርብን አሜን!
Leave a Reply