Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2019
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    262728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ዘመነ ዮሐንስ | የሉሲፈር ዘመዶች በኢትዮጵያ ተገኙ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 28, 2019

የሉሲፈር ጉዳይ ነውና የአውሮፓውያኑን ቀን አቆጣጠር ልጠቀም። በ 2016 (...) በ ናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኘው ክሊቨላንድ የተፈጥሮ ሣይንስ ቤተመዘክር፥ በሰው ዘር አመጣጥ ጥናት ክፍል ኃላፊ የሆኑት /ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ “በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሟላ” ቅሪተአካላት፡ ሉሲ/ ድንቅ ነሽ ተገችታበት በነበረበት የአፋር ቦታ አካባቢ አገኘን ይላሉ። እድሜውም ሶስት ሚሊየን ስምንት መቶ ሽህ ዓመት ነው ተብሏል። መጠሪያው ላኪ/ Lucky ሆኗል። Lucy – Lucky, „k“ ሲነሳ Lucy ይሆናል።

በቅድመታሪክ ጥናት የመስክና የቤተመኩራ መስክ ሰፊ ምርም ያደረጉት ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ እስካሁን በተገኙ መረጃዎች እና ጥናቶች መሰረት ኢትዮጵያ የዘመናዊው ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ይገልጣሉ።

ኢትዮጵያዊው “ሉሲ” (እድሜዋ 3.2 ሚሊየን ዓመት) ..አ በኅዳር 24 / 1974 .ም ነበር የተገኘችው። እንግዲህ ሉሲ በተገኘችበት ዓመት ሦስት ወራት ቀደም ሲል እ..አ በመስከረም 12 / 1974 .ም፤ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከኤርትራ በመጣው ጴንጤ ጄነራል አማን አንዶም ተተኩ። ያውም በዕለተ ቅዱስ ዮሐንስ። ዶ/ር ሀይሌ ላሬቦ በቀደም ዕለት ከአፄ ኃይለ ሥላሴ መስተዳደር በኋላ ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንዳትሆን መንግስቷ ከጦርነት እንዳይላቀቅ ማድረግ አለብን” ማለታቸው ትክክል ነው። ነጠብጣቦቹን እናገናኝ፦ ቅዱስ ዮሐንስ + አፄ ኃይለ ሥላሴ + /ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ

በነገራችን ላይ፡ ሉሲየሚለው ስያሜ የተሰጠው፡ አግኝቷል የተባለው አሜሪካዊ ተመራማሪ፡ ዶናልድ ዮሃንሰን Donald Johanson (ስሙ የ ዮሐንስ ልጅ ማለት ነው) ቅሪተአካላቱን ባገኘበት ወቅት “ሉሲ ከአልማዝ ጋር በሰማይ” / “Lucy in the Sky with Diamondsበመባል የሚታወቀውን የእንግሊዝ የሙዚቃ ቡድን ቢትልስ/ Beatles ዘፈን እያዳመጥኩት ስለነበር ነው ብሏል። የሙዚቃ ቡድኑ ደግሞ ይህን ዘፈን ያወጣው ለሉሲፈር ነው። ሰይጣን አምላኪዎች ይህን የቢትልስ ዝማሬ በጣም ይወዱታል፤ በሰይጣናዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸው ላይ ዛሬም ሲዘምሩት ይሰማሉ። በድብቅ ሉሲፈር ከአጋንንት ጋር በሰማይ / Lucifer In The Sky With Demons” መሆኑ ነው።

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፬፥ ፲፪፡፲፭]

አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ! አንተን በልብህ። ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።

[ንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፳፰፥፲፫ ]

በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።

ከአምስት አመት በፊት ሉሲ / Lucy“ የተባለና ከኢትዮጵያዋ ሉሲ/ Lucy ጋር የተያያዘ ፊልም ተሠርቶ ነበር። የፊልሙ ዋና ተዋናይት ታዋቂዋ ስካርሌት ዮህናሰን / Scarlett Johansson ( ዮሐንስ ልጅ) ናት። ከዶናልድ ዮህንሰን ጋር ስጋዊ ዝምድና የላትም። ዮሐንስ + የዮሐንስ ልጅ + /ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ።

መጭው ዘመነ ዮሐንስ ነው፤ ብዙ ተዓምራትን የምናይበት ድንቅ ዘመን ነው የሚሆነው

_____________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: