Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2019
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    262728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 25th, 2019

ዲያቆን አባይነህ ካሴ | እንደ ኢትዮጵያ መንግስት የገዛ አገሩን ቤተክርስቲያን የሚዋጋ መንግስት በዓለም ላይ የለም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 25, 2019

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያየ መንገድ ጥቃት እየደረሰባት ነው፤ ባለፉት ፵፭ ዓመታት ቤተክርስቲያን በመንግስት ደረጃ ስትገፋ ነው የⷆየችው።

አዎ! በሕገወጥ መንግሥት በደንብ የተቀነባበረ ጂሃድ በተዋሕዶ ላይ እየተካሄደ ነው።

አሁን አሁንማ አይደንቀንም፤ ልክ እነ ጄነራል አሳምነውን በሚገድሉበት ሰሞን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊና የጂሃድ አጋሩ ደመቀ መኮንን ሃሰን ቀደም ብሎ የተዘጋጀውን ምክኒያት እየሰጡ ከኢትዮጵያ ሹልክ ብለው እንደወጡት አሁንም የቁልቢ ገብርኤልን አባታችንን ሲገድሏቸው ወደ ደቡብ ኮርያ እና አሜሪካ ሸሽተዋል። ቅሌታሞች! አቤት የሚጠብቃችሁ ፍርድ! ሞኙ ወገኔ ይህን ሁሉ ዘመን በድክመቱ ገዳዩን መንግስቱ ኃይለማርያምን ለፍርድ ሳያቀርበው በመቅረቱ ሁሉም ንቀውታል፤ ግን ዛሬ እናንተን በድጋሚ እዲሁ ዝም አይላችሁም፤ ምንም ሳታደርጉለት ተቀብሮ የቆየውን ፍቅሩን በነጻ ከሰጣችሁ ሕዝብ የትም አታመልጧትም።

እነዚህን ከሃዲዎች ለፍርድ ለማቅረብና ለመቅጣት የሚያንገራግር የተዋሕዶ ልጅ እራሱ እንደ ክሃዲ ነው የሚቆጠረው። በዚያ ላይ ስለ ራሱ ሰዎች የማያስብ፣ ስለ ግል ራሱም ሆነ ስለሌሎችም ሊያስብ የማይችል ቆሞ የሞተ፤ ሕይወት እያለው በድን የሆነ ሰው ብቻ ነው።

ለክፋት ድል መቀዳጀት አስፈላጊው ብቸኛው ነገር ጥሩ ሰዎች ዝም ማለታቸው ወይንም ምንም ነገር አለማድረጋቸው ነው፡፡

ከአለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል እንደሚባለው ዝምታን አስወግደው ለእውነት የቆሙ፣ ለነጻነትና ለፍትህ የሚናገሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ቦታ ዝምታ ይብቃ በማለት ብቅ ብቅ በማለት ላይ መሆናቸው በጣም የሚያስደስት ነው።

በተዋሕዶ ልጆች ላይ፤ ክርስትያን በመሆናቸዉ ብቻ ግፍ ሲፈጸምባቸው፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲሰደዱ፣ ሲታረዱ፣ ሲቃጠሉና ሲታነቁ፣ ዝም ጭጭ ማለት ከክህደት ይቆጠራል። አውሬዎቹ አሕዛብ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በተከታታይ ሲገድሏቸውና ከእነ ቤተክርስቲያናቸው ሲያቃጥሏቸው ዝም ማለትና ቆሞ መመልከት ትልቅ ክህደት ነው፤ በ ፩ ጢሞቲዎስ ፭፥፰ ላይ የእርሱ ስለሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተሰቦቹ የማያስብ ማንም ቢሆን ሃይማኖትን የከዳ ከማያምን ሰዉ ይልቅ የከፋ ነዉ ሲል ቅዱስ ጳዉሎስ ነግሮናል።

[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።

______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: