የቁልቢ ገብርኤልን አስተዳዳሪን ማን ገደላቸው? | አህመድ ግራኝ?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 22, 2019
በምስራቅ ሃረርጌ ዞን የቁልቢ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት መልዓክኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ከቅዳሴ መልስ በቤታቸው ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ሞቶ 5 ሰዎች መቁሰላቸውን ምንጮች ለቪኦኤ አስታውቁ፡፡
ግድያው ቀጥሏል…
ወገን ልብ በል፤ ዜናውን አስቀድሞ ያቀረበው የአሜሪካው ድምጽ ቪ. ኦ. ኤ ነው።
የብፁዕ አባታችንን ነፍስ እግዚአብሔር ከቅዱሳን አበው ነፍስ ጋር ይደምርልን!
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፮፡፲፫]
“ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።”
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ…
Leave a Reply