Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2019
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    262728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

በሃገራችን ስልጣኑን የያዙት ባዕዳኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት በተለይ በግዕዝ ቋንቋ ላይ ነው ጦርነት የሚያካሂዱት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 12, 2019

ጦርነቱ በሌሎች “ኩሽቲክ” በተባሉት ቋንቋዎች ላይ አይደለም

ከቀናት በፊት በአፍሪቃ እና አፍሪቃውያን ላይ ትኩረት ባደረገ (Afrocentric) በአንድ ጉባኤ ላይ ተገኝቼ ነበር። የጉባኤው አዘጋጆችና ተሳታፊዎች በብዛት ጥቁር አሜሪካውያን ነበሩ። ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሃብታም ታሪክ፣ ባሕልና ቋንቋ የሚያዳንቁ ድርሰቶች ቀርበው ሳይ ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶኝ ነበር። አጋጣሚውን በመጠቀም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን በማስመልከት በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እየተካሄደ ስላለው የጎሳ እብደት ለጉባኤው ተሳታፊዎች ሳወሳላቸው ሁሉም በመገረም እራሳቸውን ይነቀንቁ ነበር። ስለ ኢትዮጵያ ቋንቋና ጽሑፍ፣ ስለ ተዋሕዶ እምነትና ነጮቹ ድብና አጋዘን እያደኑ በሚኖሩበት ዘመን ስለተገነቡት ዓብያተ ክርስቲያናት ብዙ ካወሳሁ በኋላ፤ ዛሬ “ኦሮሞ ነን” የሚሉ የኢትዮጵያውናን እና የጥቁር ሕዝቦች ጠላቶች ከአፍሪቃውያን ኩራት ከግዕዝ ይልቅ የአውሮፓውያኑን ፊደል በመውሰድ ፀረኢትዮጵያ እና ፀረኢትዮጵያውያን የሆኑ የጥላቻ መጽሐፍትንና ትረካዎችን አሳፋሪና ፋሽስታዊ በሆነ መልክ ለማተም መብቃታቸውን ገለጽኩ። የሚገርም ነው፤ አብዛኛዎቹ የጉባኤው ተካፋዮች ይህ መረጃ አልነበራቸው፤ እጅግ በጣም ነበር ያሳፈራቸው። “በ2019 .ም እንዲህ ዓይነት ቅሌት? 500 ዓመታት በፊት የተከሰተውን የባርነት ዘመን አስታወሰን” እያሉ በጥልቁ በማዘን ጉዳዩን በቅርብ ለመከታተል ቃል ገብተው ነበር።

አዎ! “ኦሮሞ ነን” የሚሉት ብልሹ ልሂቃን እጅግ በጣም አሳፋሪና በዝምታ የማይታለፍ ምሑራዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸው መታወቅ አለበት፤ አካሄዳቸው ልክ እንደ ጣልያን ፋሺስቶች፣ እንደ ጀርመን ናዚዎች፣ እንደ ሩዋንዳ ሁቱ እና ሰሜን ሱዳን እብዶች መሆኑን እያየን ነውና እንደ እስካሁኑ ሳንለሳለስ ቆንጠንጥ ብለን ልንዋጋቸው ይገባል። እስኪ እናስበው፤ ከአንድ ቢሊየን በላይ ቁጥር ላላቸው “ጥቁር” ሕዝቦች ኩራት የሚሆነውን ኢትዮጵያኛ ጽሑፍን፣ ባሕልንና ሃይማኖትን ለመዋጋት የኢትዮጵያን ጡት ለዘመናት ጠብተው ያደጉት ውርንጭሎች ደፋ ቀና ሲሉ።

ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሃገር ነች። የእነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መብታቸው ተጠብቆ ቋንቋቸውን ያለምንም ገደብ እንዲናገሩ ያው እስከ ዛሬ ድረስ እንዲናገሩ የከለከላቸው የሰሜን መንግስት ወይም ሥርዓት የለም። ይህን መሰሉ መብትለጋሽነት፣ ዜጎች የማንነታቸው መገለጫ የሆኑትን ቋንቋዎችና ባሕሎች ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያስችላቸው መብት በምዕራቡም ሆነ በአረብ ቱርክ ዓለም የለም፤ እነዚህ ሃገራት የአናሳ ብሔር ቋንቋዎችንና ባሕሎችን ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊያጠፉ ችለዋል። በአሜሪካ ቀይህንዳውያን ቋንቋዎቻቸውን አጥተዋል። አብዛኞቹ ነጭ አሜሪካውያን የጀርመን ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ ጀርመንኛ ቋንቋቸውንም በእንግሊዝኛ እንዲተኩ ተገድደዋል። በቱርክ ሁሉም ነዋሪ ከቱርክኛ በቀር ሌላ ቋንቋ እንዳይነገር ተደርጓል፤ ሠላሳ ሚሊየን የሚጠጉ የቱርክ ኩርዶች እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቋንቋቸውን መንገድ ላይ እንዳይናገሩ፣ በትምህርት ቤትና መንግስት ተቋማት እንዳይናገሩ ተደርገው ነበር። በአረቡ ዓለም ደግሞ ከአረብኛ ቋንቋ በቀር ሌሎች ብዙ የአገራቱ ቋንቋዎች ሙልጭ ብለው እንዲጠፉ ተደርገዋል።

በኢትዮጵያ ሃገራችን ግን በከፍተኛ ደረጃ ብቸኛ ጥቃት የደረሰበት ቋንቋ የኢትዮጵያ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ ነው። በውጭ ሃገራት ተጽዕኖ እና በኢትዮጵያውያኑ ደካማነት ላለፉት መቶ ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ላይ አሳፋሪና ቅሌታማ የሆነ ጦርነት ተካሂዷል። ለምን? ተብሎ ቢጠየቅ፤ ግዕዝ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ቋንቋ ስለሆነ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኃይሉ ከማንኛውም የዓለማችን ቋንቋ(ከትግርኛ እና አማርኛ ሳይቀር)በጣም የላቀና ኃብታም የሆነ ድንቅ ቋንቋ በመሆኑ ነው። ቀናተኛው ዲያብሎስ የግዕዝን ቋንቋ አጥፍቶ ደካማ በሆኑ የራሱ ቋንቋዎች ለመተከታት ፍላጎት ስላለው ነው።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ግብዞች ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ ነው የሚበጃቸዉ።

ግዕዝ ሊጠፋ አይችልም፤ የእግዚአብሔር የሆነው ነገር ሁሉ አይጠፋም፤ ሊጠፋም አይችልም። ግዕዝ ይለምልም!

_________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: