Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2019
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    262728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August, 2019

የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን የተቃጠለው እንዲህ ነው | በአቃጣዮች ላይ እሳቱን ያውረድባችሁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 31, 2019

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ “ኃይለኛ የሆነ አውሎ ነፋስ ሊመጣብን ነውና አደጋ ላይ ነን ፣ እንተባበር ለክፉው ሁሉ አብረን እንዘጋጅ” ሲሉ ፥ ግራኝ አብዮት አህመድ ግን፤ “ቤተክርስቲያን ወደፊትም ትቃጠላለች ምንም ማድረግ አንችልም፤ ቻሉት! ተቀበሉት!” ይለናል። ቤተክርስቲያን እየተቃጠለች ነው፤ ሃገር እየነደደች ነው፤ ግራኝ አብዮት አህመድ ግን በባዕዳውያን ሃገራት እየተንሸራሸረ ነው።

እኛ ግን ስለጽዮን ዝም አንልም!

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፷፪፥፩]

ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።

[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፪፥፭]

እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

_______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃይለኛ አዎሎ ነፋስ | “ኃያሏ” አሜሪካ ኢትዮጵያን ታምሳለች፤ ኃያሉ እግዚአብሔር አሜሪካን ያስጠነቅቃል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2019

ቃጠሎ በአውሮፓ፣ ድርቅ በአረቢያ፣ አውሎ ነፋስ በአሜሪካእራሳቸው የመረጧቸውን የኢትዮጵያ ቀለማት ተመልከቱ

ብዙ ሚሊየን አሜሪካውያን በሚቀጥሉት ቀናት ፍሎሪዳ ዙሪያ ባሉት ግዛቶች ከዚህ በፊት ያልገጠማቸውንና “ዶሪያን” የተባለ ቅጽል ስም የተሰጠውን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተሸብረው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ፕሬዚደንት ዶላንድ ትራምፕ፦ “ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እየመጣብን ነውና ተዘጋጁ፣ እነዘጋጅ!” በማለት ዜጎችን አስጠንቅቀዋል። እነዚህ አዎል ነፋሶች አሜሪካውያንን በየጊዜው ስለሚያሸብሩ፡ የአውሎ ነፋሶቹን ሰፌድ በኑክሌር ቦንብ ለመምታት እስከ ማሰብ ድረስ ፕሬዚደንት ትራምፕ ደርሰዋል።

ለነዋሪዎቹ ሰላሙን ያምጣላቸው፤ ግን ከእናንተ የበለጠ የኃያሎች ኃያል አለ፡ የሚነፍሰውን እስትንፋሱን አትችሉትምና ኢትዮጵያን ባትነኳት ይሻላችኋል!!!

______________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በተክለ ሐይማኖት ዕለት ሌላ አሳዛኝ ዜና | በ ጎንደር የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን ተቃጠለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2019

በደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል።

የአከባቢው ነዋሪ እንደገለጸው ከሰሞኑን ለነዋሪው እንግዳ የሆኑ ሰዎች መታየታቸውን እና ምንም አይነት ሌላ ምክንያት እንደሌለው ገልጸዋል። ቤተክርስቲያኑ ሙሉ ለሙሉ በእሳት ወድሟል።

ስንት አባቶች፣ እናቶች፣ ሕፃናት እና አገልጋዮች መገደል አለባቸው ግራኝ አብዮት አህመድን ለመቅጣት? ስንት አብያተክርስቲያናት መቃጠል አለባቸው ለሰላማዊ ሠልፍ ለመውጣት?

ተክልዬ አባቴ ሆይ፤ ይህንን መቅደስህን ሆን ብለው እሳት በለኮሱት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ላይ በእውነት አባታችን አንተ ማጥ ልቀቅባቸው።

የአባታችን የአቡነ ተክለ ሀይማኖት ምልጃና ጸሎታቸው ረድዔትና በረከታቸው በኛ በልጆቻቸው ላይ ይደርብን አሜን!

___________________

Posted in Ethiopia, Faith | Leave a Comment »

ኢትዮጲያዊነታቸውን በመካዳቸው “ኤርትራውያን” በመሰቃየት ላይ ናቸው | ሌሎቻችሁ ከዚህ ተማሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 29, 2019

ምከረው፣ ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው!

በጣም አሳዛኝ ነገር ነው! ወገን ለመማር አለመቻሉ ደግሞ ብዙ ንዴትንና ቁጣን ይቀሰቅሳል።

በኤርትራ የሚኖሩ ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊነታቸውን በመካድ ኤርትራ የምትባል አዲስ ሃገር ሲቆረቁሩ፤ በቃ ማርና ወተት የሚጎርፍባት የበለጸገች ሃገር ትሆናለች ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። በእውነት ለመናገር ስድስት ሚሊየን ብቻ ነዋሪዎች ያሏት ኤርትራ በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ የሚገኙትን ቦታዎች በማልማት በቱሪዝም ብቻ ትበለጽግ ነበር፤ ህዝቡም ታታሪ ስለሆነ እነ ምጽዋ እና የዳህላክ ደሴቶች ከግብጾቹ የቀይ ባሕር ቱሪስቶች ማዕከላት፡ ከ ሻርም አልሼክ እና ሁርጋዳ በበለጠ መልክ አውሮፓውያን ጎብኝዎችን በብዛት የመሳብ እድል ነበራቸው።

ነገር ግን ያው እንግዲህ የኢትዮጲያን ካባ አውልቀው ከጣሉ ሃያ ዓመታትን አስቆጥረዋል፤ ምንም የተሳካ ነገር የለም፤ ዜሮ! ናዳ! እንዲያውም ትውልዱ ኢትዮጵያዊነቱን በመካዱ ብቻ ታይቶ የማይታወቅ መቀመቅ ውስጥ ለመግባት ተገድዷል። አንድ የሃበሻ ትውልድ ተሰድዶ በማለቅ ላይ ይገኛል፤ ወጣት ኤርትራውያን ድኻ ዘመዶቻቸው ለፍተው ያጠራቀሙላቸውን ገንዘብ ይዘው በመጓዝ የአረብ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ምሳ በመሆን ላይ ናቸው፣ ከዚያ የተረፉት በሰሜን እና ምስራቅ ባሕራት ላይ የአሳ ነባሪዎች እራት ናቸው፤ የአባይ ወንዝ ቅዱሱን የጽዮን ተራሮች አፈር ጠራርጎ በመውሰድ ለአውሮፓው ባሕር ኢትዮጵያ ግብር የምትከፍለው አልበቃ ብሎ ኤርትራውያኑም ለዲያብሎስ የደም ግብር በውሃው ላይ እየከፈሉ ነው፣ በአረብ በርሃዎች ደግሞ የኩላሊትና ጉበት መለዋወጫ የሚገኙባቸው ሳጥኖች ሆነዋል፤ ሁሉም በነፃ፣ ሁሉም በፈቃዳቸው።

ቀደም ሲል፡ እነ ግራኝ አብዮት አህመድ ለቀመሙት ዲያብሎሳዊ ሴራ ማጣፈጫ ይሆን ዘንድ የሰሜኑን ድንብር ለኤርትራውያን ክፍት ሲያደርጉ ኤርትራውያኑ ኢትዮጲያዊነታቸውን መልሰው እንዳገኙት ሆኖ ስለተሰማቸው በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩት ወደተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት መጉረፍ ጀመሩ። ነገር ግን ይህ “የኩሽ መንገስት እንመሠርታለን” ብለው የተነሱትን እባቦቹን እነ ግራኝ አብዮት አህመድን አላስደሰታቸውም፤ “ኦሮሞ እንጅ ኢትዮጵያን መውረር ያለበት፣ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን መያዝ አይችሉም” በሚል የድንጋጤ ምላሽ፡ የኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር ወዲያው እንዲዘጋ አዘዙ።

አሁን ኤርትራውያን እንደገና በአረብ በረሃ ላይ እና በሜዲተራንያን ባሕር ውስጥ እያለቁ ነው። ኢትዮጵያዊነታቸውን ለመክዳት በመዘጋጀት ላይ ያሉት ሌሎቹ ግብዞች እና ከሃዲዎች በእውነት ሉሲፈርን በማገልገል አገር ለማጥፋት አቅደው ካልሆነ በቀር፡ እውነት በጎ ነገር ካሰቡ እንዴት ከዚህ መማር ያቅታቸዋል? እንዴት መንደርተኘነቱን እንተው፣ የጠላት መጫወቻዎች መሆኑ ይብቃን ማለት ያዳግታቸዋል???

በ “ሀበሻ” ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ ትውልድ እያለቀ ነው፡ ወገን!

በ “ሀበሻ” ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ ትውልድ እያለቀ ነው፡ ይህ በዝምታ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡ ወገን!

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዘመነ ዮሐንስ | የሉሲፈር ዘመዶች በኢትዮጵያ ተገኙ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 28, 2019

የሉሲፈር ጉዳይ ነውና የአውሮፓውያኑን ቀን አቆጣጠር ልጠቀም። በ 2016 (...) በ ናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኘው ክሊቨላንድ የተፈጥሮ ሣይንስ ቤተመዘክር፥ በሰው ዘር አመጣጥ ጥናት ክፍል ኃላፊ የሆኑት /ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ “በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሟላ” ቅሪተአካላት፡ ሉሲ/ ድንቅ ነሽ ተገችታበት በነበረበት የአፋር ቦታ አካባቢ አገኘን ይላሉ። እድሜውም ሶስት ሚሊየን ስምንት መቶ ሽህ ዓመት ነው ተብሏል። መጠሪያው ላኪ/ Lucky ሆኗል። Lucy – Lucky, „k“ ሲነሳ Lucy ይሆናል።

በቅድመታሪክ ጥናት የመስክና የቤተመኩራ መስክ ሰፊ ምርም ያደረጉት ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ እስካሁን በተገኙ መረጃዎች እና ጥናቶች መሰረት ኢትዮጵያ የዘመናዊው ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ይገልጣሉ።

ኢትዮጵያዊው “ሉሲ” (እድሜዋ 3.2 ሚሊየን ዓመት) ..አ በኅዳር 24 / 1974 .ም ነበር የተገኘችው። እንግዲህ ሉሲ በተገኘችበት ዓመት ሦስት ወራት ቀደም ሲል እ..አ በመስከረም 12 / 1974 .ም፤ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከኤርትራ በመጣው ጴንጤ ጄነራል አማን አንዶም ተተኩ። ያውም በዕለተ ቅዱስ ዮሐንስ። ዶ/ር ሀይሌ ላሬቦ በቀደም ዕለት ከአፄ ኃይለ ሥላሴ መስተዳደር በኋላ ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንዳትሆን መንግስቷ ከጦርነት እንዳይላቀቅ ማድረግ አለብን” ማለታቸው ትክክል ነው። ነጠብጣቦቹን እናገናኝ፦ ቅዱስ ዮሐንስ + አፄ ኃይለ ሥላሴ + /ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ

በነገራችን ላይ፡ ሉሲየሚለው ስያሜ የተሰጠው፡ አግኝቷል የተባለው አሜሪካዊ ተመራማሪ፡ ዶናልድ ዮሃንሰን Donald Johanson (ስሙ የ ዮሐንስ ልጅ ማለት ነው) ቅሪተአካላቱን ባገኘበት ወቅት “ሉሲ ከአልማዝ ጋር በሰማይ” / “Lucy in the Sky with Diamondsበመባል የሚታወቀውን የእንግሊዝ የሙዚቃ ቡድን ቢትልስ/ Beatles ዘፈን እያዳመጥኩት ስለነበር ነው ብሏል። የሙዚቃ ቡድኑ ደግሞ ይህን ዘፈን ያወጣው ለሉሲፈር ነው። ሰይጣን አምላኪዎች ይህን የቢትልስ ዝማሬ በጣም ይወዱታል፤ በሰይጣናዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸው ላይ ዛሬም ሲዘምሩት ይሰማሉ። በድብቅ ሉሲፈር ከአጋንንት ጋር በሰማይ / Lucifer In The Sky With Demons” መሆኑ ነው።

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፬፥ ፲፪፡፲፭]

አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ! አንተን በልብህ። ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።

[ንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፳፰፥፲፫ ]

በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።

ከአምስት አመት በፊት ሉሲ / Lucy“ የተባለና ከኢትዮጵያዋ ሉሲ/ Lucy ጋር የተያያዘ ፊልም ተሠርቶ ነበር። የፊልሙ ዋና ተዋናይት ታዋቂዋ ስካርሌት ዮህናሰን / Scarlett Johansson ( ዮሐንስ ልጅ) ናት። ከዶናልድ ዮህንሰን ጋር ስጋዊ ዝምድና የላትም። ዮሐንስ + የዮሐንስ ልጅ + /ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ።

መጭው ዘመነ ዮሐንስ ነው፤ ብዙ ተዓምራትን የምናይበት ድንቅ ዘመን ነው የሚሆነው

_____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Ethnicity, Genetics & Anthropology, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በመርከብ ተሳፍረው ሲጓዙ የነበሩት ሁሉም ሲሞቱ የኦነጉ ፖለቲከኛ ብቻ ተርፎ ሬሳቸውን ወደ ባሕር ለመወርወር በቃ | ታምኑታላችሁን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 28, 2019

መሀመድ አደም ኦጋግ ከስደተኞች ጀልባ የተረፈው ሰው ነበር ፡፡ ሊቢያን ለቀው ሲወጡ በመርከብ ተሳፍረው 15 ነበሩ ፡፡

በመርከብ ተሳፍረው የነበሩት አስራ አምስት ሰዎች ወንድ እና ነፍሰ ጡር ሴት ከጋና ፣ ሁለት ወንዶች ከኢትዮጵያ እና 11 ሶማሊያን ያቀፉ ናቸው፡፡

በታሪኩ መሠረት እያንዳንዱ ስደተኛ ከሊቢያ ወደ አውሮፓ ክፍት በሆነው ሞቃታማ የማዕከላዊው ሜድትራንያን ባህር ጉዞው ለአንድ አዘዋዋሪ 700 ዶላር እያንዳንዳቸው ከፍለው ነበር፡፡

መሀመድ ኦጋ የሚከተለውን ተናግሯል፦

11 ቀናት በባህር ላይ ነበርን፡፡ በመሃል የባህሩን ውሃ መጠጣት ጀመርን ፡፡ ከአምስት ቀናት በኋላ ሁለት ሰዎች ሞቱ፡፡ በየቀኑ ሁለት በተጨማሪ ይሞታሉ። ”

አንድ በአንድ ፣ በጀልባው ላይ የነበረ ሰው ሁሉ ይሞታል ፣ እኔና ሶማሌው እስማኤል ብቻ ተረፍን፡፡ እስማኤልም አለአሁን ሁሉም ሰው ሞቷል ፡፡ ለምን እንኖራለን፤ አብረን እንሙት አለኝ፡ እኔ ግን አይሆንም አልኩት”

አሁን በጀልባው ውስጥ ሁሉም ሞቱ ፡፡ ፀሐያማና ሞቃታማ ነበር። ምግብም ሆነ ውሃ አልነበረንም፡፡ ከእስማኤል ጋር ሆነን አስከሬኖቹን አንድ በአንድ ወስደን ወደ ባህሩ ወረወርናቸው፡፡ አስከሬኖቹ መሽተት ጀመረው ነበር። ከዚያም እስማኤልም ሞተ፣ አላህ እኔን ብቻ በተዓምር አተረፈኝ”

ባሕር ውስጥ ህይወታቸው ላለፈው ምስኪኖች ነፍሳቸውን ይማርላቸው።

በጣም ይገርማል፦ ግን መሀመድ ኦጋ በእነርሱ ሞት ምን ዓይነት ሚና ተጫውቶ ይሆን? አንድ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ፕለቲከኛ በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ይፈራል እንዴ? እንደው ይህ እንዴት ሊታመን ይችላል? መወሻከት አይሆንበትምን? እንደሚመስለኝ ምናልባት ከእስማኤል ጋር ሆኖ መርዞ የገደላቸውን መንገደኞች ወደ ባሕር ወርውሮ ከጨረሰ በኋላ ምስክር እንዳይሆን እስማኤልንም ገድሎ ወደ ባሕሩ ወርውሮት ይሆናል፤ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ አሳዛኝ ክስተት ወደ የመን በሚጓዙ ብዙ ኢትዮጵያውያን ላይ ታይቷል ፥ እኔ በበኩሌ ይህን ሰው አላምነውም፤ ማንኛውንም የኦነግ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ሰው ለማመን ያዳግተኛል፤ እነዚህን ሰዎች ከፍተኛ የሆነ የመንፈሳዊ ቀውስ ገጥሟቸዋል፤ ከእነ መሪዎቻቸው ሁሉም ታመዋል፣ ተረብሸዋል፣ አብደዋል፤ ምን ይሻላቸዋል?

ቢቢሲ ካወሳቸው ነገሮች መካከል፦

ራሱን የቀድሞው አመፀኛ ቡድን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፖለቲከኛ እንደሆነ የገለፀው የ 38 ዓመቱ መሀመድ ኦጋ ፣ ከጀርመን ወዳጆቹ ጋር ከተገናኘ በኋላ ነበር ጉዞውን ለማድረግ የወሰነው፡፡”

(38-year-old Oga, who describes himself as an exiled Ethiopian politician from former rebel group, the Oromo Liberation Front, said he decided to make the journey after he was contacted by friends from Germany.)

መሀመድ ኦጋ እንደ ቢቢሲ ገለፃ የቀድሞው አመፀኛ ቡድን ኦነግ አባል ነው፤ ኦነግ በኢትዮጵያ ሕገ ወጥ ስለሆነ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በቁጥጥር ስር እውላለሁ፣ እታሰራለሁ ብሎ ሰግቷል፡፡

(Mohammed Oga, according to the BBC, believes he faces arrest if he returns to Ethiopia because his former rebel group is outlawed.)


No Food, Water And Fuel: The Horrific Journey Of 15 Migrants From Libya To Europe As Told By Lone Survivor


Mohammed Oga

Mohammed Oga was the only one who survived on the voyage from Libya to Europe. There were fifteen people on board, including a pregnant woman

First, their fuel ran out. Next, was their food. And then their water. And then one by one, fourteen out of the fifteen people (including a pregnant woman) on the canoe they were aboard, took their last breath and were toppled overboard.

Mohammed Adam Oga, the lone survivor, was spotted and picked up in Maltese waters on Monday, August 19, after the European Border and Coast Guard Agency, Frontex, spotted a dinghy adrift at sea, reports the BBC.

Footage of the rescue by Malta’s armed forces showed Oga slumped over a man’s body before he was airlifted to hospital.

According to the story, each migrant had paid a smuggler $700 to aid them in making the journey from Libya to Europe in the open sea and in the scorching heat of the Central Mediterranean, which is one of the deadliest stretches of water in the world.

38-year-old Oga, who describes himself as an exiled Ethiopian politician from former rebel group, the Oromo Liberation Front, said he decided to make the journey after he was contacted by friends from Germany.

He told the Times of Malta that once in Libya, he met a Somali named Ismail and together they arranged their passage via a smuggler.

And then, on August 1, having been given the GPS and showed where to head towards, they set off from the Libyan city of Zawia, 45km (28 miles) west of the capital, Tripoli, he said.

The fifteen people on board comprised of a man and a pregnant woman from Ghana, two men from Ethiopia, and 11 Somalis, he added.

Mohammed Oga described the moment after which they run out of fuel, food and water, as a desperate situation as they tried in vain to get help from boats and helicopters passing by.

We were at sea for 11 days. We started drinking sea water. After five days, two people died. Then every day, two more died.”

Oga described his survival as a ‘God-sent.’

God sent the Maltese to save me,” he told Times of Malta, while being attached to a drip and too weak to walk.

Narrating his ordeal to the Times of Malta, Oga demonstrated, by slowly closing his eyes, how each fellow passenger of his died.

One by one, almost everybody on the boat died, leaving him with Ismail. “Ismail said, ‘Everyone is dead now. Why would we live?”

They died in the boat. It was sunny, hot. No food and no water. Ismail said we should put the bodies in the sea. We took the bodies and threw them in the water. The bodies were smelling.”

Rubber Boat

A critically ill Mohammed leans over the dead body of his friend Ismail before the rescue on Monday

Oga narrated how at one point, Ismail became frustrated, going as far as asking that they both die together but he refused. Not long after that, Ismail also died.

He remembers the last days of his journey like being a dream although he does not remember his rescue and was unaware that Ismail had died.

Mohammed Oga, according to the BBC, believes he faces arrest if he returns to Ethiopia because his former rebel group is outlawed. He left 15 years ago, first for Eritrea and then Sudan, and wants to travel to the UK.

According to the UN, 839 people have died trying to cross the Mediterranean, making it the most dangerous sea route for refugees and migrants in the world.

Mohammed is one of more than 40,000 people who have survived crossing the treacherous Mediterranean to Europe’s coasts this year, including 1,000 to Malta.

ምንጭ

____________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | 3 Comments »

ቅሌታማዋ ሶማሊት ኢልሃን የሌላ ሴት ባል ስታማግጥ ተያዘች | እንዲህ አጋልጣቸው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 28, 2019

የሰውዬው ሚስት ባሌን ታማግጣለች በማለት ኢልሃንን ወነጀለቻት!

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፥፪፯]

ኃጢአተኞች እንደ ሣር ሲበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ሲለመልሙ፥ ለዘላለም ዓለም እንዲጠፋ ነው።”

እውነት ሙስሊሞች እንደሚሉት የሻሪያ ህግ ይህን መሰሉን አመንዝሮ በጥብቅ የሚቃወም ከሆነ እስኪ ለኢልሃን ኦማር ፋትዋ ይስጧትና በድንጋይ ወግረው ይግደሏት! ወይስ እንደሚሉት የእስልምናን አጀንዳ ለማራመድ ነው የምትሸረሙጠው?! እስኪ እናያለን!

በጣም የሚገርመው ደግሞ “ሂጃብ የምለብሰው ለአላህ ስል ነው፤ እስልምናን ለማስተዋውቅ ነው” የምትልዋ ሴት ሚስት እንዳለው የምታውቀውን ወንድ ታማግጣለች። ግብዝ፣ ቀጣፊ፣ አስመሳይ፣ ወስላታ፣ የዲያብሎስ ልጅ!

ለነገሩማ በእስልምና መሀመድ ጊዚያዊ ጋብቻን(ሽርሙጥናን)ፈቅዷል “ሙጣ” ይባላል። በሳውዲ አረቢያ እና ኢራን የሽርሙጥና ባሕል በሚያስገርም ብዛት ተስፋፍቷል። ይህን ያንብቡ።

ኢልሃን ኦማር ከሰዶማዊ ወንድሟ ጋር መጋባቷን የሚያረጠውን ሰነድ ቀደም ሲል አይተን ነበር፤ ኢልሃን ኦማር ከሰዶማዊ ወንድሟ ከ አህመድ ኤልሚከ ጋር በመጋባቷ እና ለግብረሰዶማውያን ቅርርብ ስላላት ነው የተወካዮች ምክር ቤት አባል ለመሆን የበቃችው። የሴትዮዋ ወንጀል ተዘርዝሮ አያልቅም፤ እዚህ ለመድረስ ብዙ ሕገወጥ የሆኑ ወንጀሎችን እየሰራች ነው የተጓዘችው። ባለፈው ጊዜ የፌዴራል ግብርን(IRS)አስመልክቶ የማጭበርበሪያ ወንጀል ስለሰራች የጥቂት ገንዘብ መቀጮ እንድትከፍል ታዛ ነበርባለፈው ወር ላይ ደግሞ የመጀመሪያ ባሏን እና የልጆቿን አባት ለሁለተኛ ጊዜ መፍታቷን አሳውቃ ነበር። ባጠቃላይ ለሦስተኛ ጊዜ ስትፋታ ነው። ይህን ባሳወቀች ማግስት ቪዲዮው ላይ የሚታየውን ባለትዳር ወንድ አማገጠች። እኔና እናንተ እሷ የሠራችውን ዓይነት ወንጀል ሠርተን ቢሆን ወይ የሚሊየን ዶላር መቀጮ እንድንከፍል እንገደድ ነበር፣ ወይ ወህኒ ቤት እንገባ ነበር ካልሆነ ደግሞ ወዲያውኑ ከአሜሪካ ተጠርፈን ነበር። ሴትየዋ ግን ከመንግስት ሰራተኝነቷ እንኳን እስከ አሁን ድረስ አልተወገደችም። ዋው! የዛሬዋ ዓለማችን ሰይጣን የሚመራት የወንጀለኞች፣ የአመንዛሪዎችና ግብረሰዶማውያን ዓለም መሆኗ ይህ ጥሩ ማስረጃ ነው።

ግን አየን አይደል የአምንዝራ እና ግብረሰዶማውያን አምላክ አላህ እንደሆነ። ለዚህ እኮ ነው በተለይ የመንፈሳዊ ሕይወትን በሚመለከት ምድረ በዳ በሆነችው የሚነሶታ ግዛት የዋቄዮአላህ ልጆች የሆኑት ሶማሌዎች እና ኦሮሞዎች በብዛት ለመኖር የወሰኑት። ሚነሶታ = ሚኒኦሮሚያ + ሚኒሶማሊያ

አጋልጣቸው አምላካችን፤ እንዲህ አጋልጣቸው ጠላቶችህን!!!

በአንድ በኩል የኢሊሃን ኦማር ወደ አሜሪካ ምክር ቤት መግባት በጣም ጥሩ ነገር ነው፣ በአንድ በኩል የአብዮት አህመድ ስልጣን ላይ መውጣት በጣም ጥሩ ነገር ነው፣ በአንድ በኩል የጀዋርና ጀራቶቹ በሜዲያ ላይ ብቅ ብቅ ማለት እጅግ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ለምን? ምክኒያቱም ፈጠነም ዘገየም ማንንታቸውን በግልጽ ለማየት ያስቸለን ዘንድ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልናል እና ነው። ብዙዎች እውሮች ስለሆኑና በአጉልቶ ማሳያ መነጽር እንዲያዩ ካልተደረጉ በቀር ትንሽ እንኳን አይተው ለማመን የሚቸገሩ ስለሆኑ ነው። አማላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ በመልበስ ወደ ዚህች ምድር ላይ የመጣው ከሃጢአታችን ሊያድነን እና አየተን ለማመን እንችል ዘንድ ነው። አባቶችና እናቶች እየተሰውልን ያሉት እኮ ጠላታችን ዲያብሎስን እና ጠላቶቻችንን ለይተን ለማየት፣ ለማወቅና ለመጋፈጥ አሻፈረን ስለምንል ነው ፥ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ያሉት እኮ እኛ ከእንቅልፋችን ነቅተን “በቃን! አትንኩን!” በማለት ሰላማዊ ሰልፎችን ለማዘጋጀት ፈቃደኞች ስላልሆንን ነው።

ባጭሩ፤ የቤተክርስቲያናችንን የፈተና እና የሕዝባችንን የስቃይ ጊዜ በማራዘም ቁልፍ ሚና የሚጫወቱት አይን እያላቸው የማያዩት ፤ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙት ወገኖች ናቸው። መጥፎውን ሽሹ መልካሙን እሹ!

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፮፥፬]

ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል

___________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በሕልሜ ግራኝ አብዮት አህመድ ላሊበላን እና የሕዳሴውን ግድብ ሲተናኮል አየሁት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 27, 2019

ባለፈው ጊዜ ያለምክኒያት ወደ ላሊበላ አልተጓዘም ማለት ነው።

ነፍሳቸውን ይማርላቸውና በግራኝ አብዮት አህመድ የተገደሉት ጄነራሎች ከላሊበላ እና አካባቢዋ የፈለሱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ይህ ግድያ ግራኝ አህመድ ካቀደው የላሊበላ ጥቃት ጋር የተያያዘ ይሆን? ላሊበላን ሊከላከሉ የሚችሉትን ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ማስወገዱ ይሆን?

ከአምስት መቶ አመታት በፊት በቱርኮች፣ ግብጾች፣ ሶማሌዎች እና ሱዳኖች የተደገፈው ግራኝ አህመድ በኢትዮጵያ የጥቃት ዒላማ አድርጓቸው የነበሩት ቦታዎች ላሊበላ እና አክሱም ነበሩ። ይህ ግን አልተሳካለትም። ዛሬ ልጆቹም እነዚህን የክርስቲያኖች ቅዱሳት ቦታዎች ለማጥፋት ከምናስበው በላይ ከፍ ያለ ፍላጎት እና ጉጉት አላቸው።

ታሊባን ሙስሊሞች የሺህ ዓመታት እድሜ የነበራቸውን የቡድሃ ሃይማኖት ኃውልቶችን በአፍጋኒስታን ማፈራረሳቸው ይታወሳል። አይሲሶች ደግሞ የግብጽን ፒራሚዶች ሳይቀር ለማፈረስ በመዛት ላይ ነበሩ። በቅድሚያ ግን ለሕዝበ ክርስቲያኑ፡ በተለይ ለሶሪያ፣ ኢራቅና ግብጽ ኦሮቶዶክስ ክርስቲያኖች ክቡር የሆኑትን ቦታዎች ማውደም ነበረባቸው፤ በሶሪያና ኢራቅ ተሳክቶላቸዋል፤ ኮፕቶችንም በከፊል ለመረባበሽ በቅተዋል። አሁን ደግሞ አትኩሮታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ቀይረዋል ተብሏል።

የተዋሕዶ ልጆች በሊቢያ በርሃ እንደ ዶሮ ሲታረዱ፤ በማግስቱ የደስታ “ኢድ” አዘጋጅተው የነበሩትን ሶማሌዎች እና ሱዳኖች እኔ እራሴ በቅርቡ ለመታዘብ በቅቼ ነበር። አፄ ኃይለ ሥላሴ ከዙፋናቸው እንዲወርዱ ሲደረጉና መንግስቱ ኃይለማርያም ስልጣኑን ሲይይዝ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዘንድ የደስታ “ኢድ በዓል” በየቦታው ይካሄድ እንደነበር አባቶቻችን ነግረውናል፤ እንዲያውም ይህን የሚያሳይ ቪዲዮ በአዲስ አበባ መርካቶ ተቀርጾ አይተን ነበር። አዎ! ዲያብሎስ እስልምናን ሲፈጥር በተለይ የክርስትና ጠላት አድርጎ ነው የፈጠረው። ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት የክርስትና ሽንፈት ለሙስሊሞች ድል ነው፤ አስደሳች ነው። ባለፉት ወራት ብቻ ብዙ አባቶች መገደላቸውና ሰላሳ አብያተክርስቲያናት መውደማቸው ለእነርሱ ድል ነው፤ ሙስሊሞች “እስልምና አይደለም፣ እኛ አይደለንም፣ አይሲስ እውነተኛ ሙስሊሞች አይደለሙ ቅብጥርሴ” ከማለት ሌላ ድርጊቱን ሲያወግዙና ከክርስቲያኖች ጋር ስሜታዊ በሆነ መልክ የትብብር ምልክት ሲያሳዩ አይታዩም። ምክኒያቱም እስልምና የክርስትና ቀንደኛ ጠላት በመሆኑ ነው!

ስለዚህ አክሱም እና ላሊበላ ላይ ጥቃት ለማድረስ የአምስት መቶ ዓመት ህልማቸው ነው ብንል በጭራሽ አልተሳሳትንም። ዛሬ፡ ለጊዜውም ቢሆን፡ ሁኔታዎች በደንብ ተመቻችተውላቸዋል። ዳግማዊ ግራኝ አህመድ ስልጣኑን ጨብጧል፤ ም ዕራባውያኑም አረቦቹም ድጋፍ ስለሚሰጡት ሁሉም የልብ ልብ ብሏቸዋል፤ በክርስቲያኖች ላይ የመጨረሻውን የጥቃት ዘመቻ ለማድር ለማድረስ ጊዜው የደረሰ መስሎ ይታያቸዋል፤ ምናልባት በጽንፈኝነት እንዳይወነጀሉ ደግሞ የጽንፈኞች ንግስት የሆነውን አይሲስ የተሰኘ ቡድን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ ለመጠቀም ተዘጋጅተዋል። እንግዲህ በእነ ላሊበላ ላይ የሆነ ጥቃት ቢደርስ እነ ግራኝ አህመድ እራሳቸውን ለማዳን አይሲስ ነው ይላሉ።

ባለፈው ሰንበት የሕዳሴውን ግድብ የተመለከተ አንድ ልዩ የሆነ ህልም በእንቅቅልፌ ታይቶኝ ነበር፤ ትናንትና ዛሬ ስለዚህ ህልም ሳስብና ሳሰላስል የተጋጠመልኝ “አይሲስ አትኩሮቱን ወደ ኢትዮጵያ ቀይሯል” ከሚለው ዜና ጋር ነው። ሠራዊትአልባዋ ኢትዮጵያ በደከመችበት በዚህ ዘመን ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ አትኩሮትን ሊያገኝላቸው የሚችለውን ተግባር(በሕዳሴው ግድብ እና ላሊበላ ላይ ጥቃት መሰንዘር)በጥድፊያ መፈጸም አቅደዋል ማለት ነው” የሚለው ሃሳብ ነው።

ወገን፤ ሳይዘገይ የአባቶችህን ፈለግ ተከተል፤ ሌላ አማራጭ የለህም፤ አገርህና ቤተክርስቲያንህ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል፤ ደም የሚያስለቅሰው የጽንፈኞች ድርጊት ከመከሰቱ በፊት የአባይን ውሃ ለመበከል ያስችል ዘንድ የራዲዮ አክቲቭ መርዝን ማዘጋጀት ተገቢ ነው፤ ለዚህ የሚገጋጅ ቡድን መስርቱ፤ ሩሲያን እንጠይቅ፤ አንድ ጆንያ ይበቃል። የአረቦች ኩራት የሆነችው እባቧ ግብጽ በዚህ መልክ ማስጠንቀቂያ ካልተሰጣት ድብቅ ትንኮላዋን በቀላሉ አታቆምም

ቅዱስ ላሊበላ ሞቶም መላዉ ኢትዮጵያዉያንን እየጠቀመ ነዉ ፤ ሞቶም እንኳን ኢትዮጵያን አይረሳም!

______________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ፕሮፊሰር ሀይሌ ስለ አሜሪካ ተንኮል | ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንዳትሆን መንግስቷ ከጦርነት እንዳይላቀቅ ማድረግ አለብን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 27, 2019

አንድ ኢትዮጵያዊ እንዲህ ነው መሆን የሚገባው፤ ረጅም እድሜ ይስጥዎት፡ ጋሽ ሀይሌ ላሬቦ፤ እንወድዎታለን!

በተለይ ተቃራኒ ወገኖች መስለው በዓለም የፖለቲካ መድረክ ላይ ዋና ተዋንያን የሆኑት ምዕራባውያን እና ምስራቃውያን እርስ በእርሳቸው ጠላቶች በመምሰልና የተለያዩ ርዕዮተ ዓለማትን በመከተል ለአንድ ዓላማ በመነሳሳት ፀረክርስቶስ የሆነውን ተግባራቸውን በማካሄድ ላይ ናቸው። በተለይ በጠላትነት የሚዋጓቸው አገራት የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮች የሆኑትን አገራትን፤ በዋናነት ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን መናኸሪያዎች ነው። ኦሮቶዶክስ በሆኑት በግሪክ፣ ቆጵሮስ፣ ጆርጅያ፣ አርሜኒያ፣ ዩክሬይን፣ ሰርቢያ፣ ሩሲያ፣ ግብጽና ሶሪያ ላይ ላለፉት ሺህ ዓመታት ሲፈጽሙት የነበረው ተንኮልና ግፍ በታሪክ መጻሕፍት በደንብ የተመዘገበና ዛሬም የምናየው ነው።

በነገራችን ላይ፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ወዳጅና እህታማ ኦርቶዶክስ አገሯ አርሜኒያ ከኢትዮጵያ ጋር እስከ አሁን ድረስ የዲፕሎማቲክ ግኑኝነት አልነበራትም። ግን በቅርቡ ኢምባሲ እንደምትከፍት ዛሬ የወጣው መግለጫ ይጠቁማል።

We are opening this new direction by way of establishing close cooperation with Ethiopia, our historical friend in Africa,” the minister added. “It’s planned to open our diplomatic mission in [the Ethiopian capital city of] Addis Ababa, as early as this year.”

ኢትዮጵያና አርሜኒያ ጠላት የሆነችው የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ ሳተላይት ሃገር አዜርቤጃን ግን አዲስ አበባ ላይ ኤምባሲ ከከፈተች ቆየታለች። እንዲያው ይገርማል!

ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም ፥ በዓለም ላይ በጣም ጥንታዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ክርስቲያን ህዝብ ለመቆጣጠር ፣ ለማዳከም እና በመጨረሻም ለማጥፋት ሉሲፈራውያኑ ምዕራባዊያን ፣ ሶቪዬቶች እና ሙስሊም አረቦች ፀረክርስቲያናዊ ርዕዮተ ዓለማትን በወጣቱ ሕዝባችን ዘንድ በማስፋፋት(ሊበራሊዝም፣ ዲሞክራሲ፣ ኮሚኒዝም እና እስልምና)፣ የአየር ሁኔታን የሚቀይሩ ጦርነቶችን በማካሄድ(ድርቅ እና ረሀብ)፣ በሽታዎችን በማሰራጨት(ኤድስ እና ኮሌራ)እንዲሁም ብዙ ደም የሚፈስባቸውን ጦርነቶች በመቀስቀስ(ለኤርትራ ፣ ለሶማሊያ) 50 ዓመታት ያህል(1966 .ም– እስከ ዛሬ ድረስ)በግልጽ ተግተው ሲን፡ቀሳቀሱ በግልጽ ይታያሉ። ልብ በል፤ “66፥ “50ኢዮቤልዩ።

ልክ እንደ እነ ዶ/ር ሀይሌ ላሬቦ ወደ ማንንታችን በመመለስ ይህን የዔሳውያን እና እስማኤላውያን ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ አንድ ላይ ሆነን በተደጋጋሚ ካላጋለጥን የሕዝባችን ስቃይ እና ቁልቁል ጉዞ መቀጠሉ አይቀረም። ዶክተሮች ብቅ ብቅ ባሉበት በዚህ ዘመን የህመማችንን መንስኤ የሚነግረን ዶክተር እንጅ መርዛማውን መርፌ የሚወጋን ወይም የሉሲፈራውያኑን “መድኀኒት” እንድንገዛ ሪሴፕት የሚጽፍልንን ወስላታ ዶክተር አይደለም የምንፈልገው።

ቪዲዮው ላይ በተጨማሪ እንዳቀረብኩት፤ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የዘጠና ስድስት ዓመቱ ሰይጣን ሄንሪ ኪሲንጀርና አጋሮቹ አፄ ኃይለ ሥላሴን በማታላል ከተዋሕዶ እምነታቸው እንዲርቁና ሆራ/ደብረዘይት ላይ ለዋቄዮአላህ መስዋዕት እንዲያደርጉ፣ ቀጥሎም ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር የነበራትን የዲፖሎማቲክ ግኑኝነትን በማቋረጥ ልክ እንደ አሁኑ ከከንቱዎቹ አረቦች ጋር እንድትቀራረብ በማድረግ የገበጣ ጨዋታውን ጀመሩት። ብዙም አልቆየም፤ ኢትዮጵያን ለማናጋትና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ድርቅና ረሃብ ለመፍጠር አየሩን ቀያየሩት (Weather Manipulation/ Weather warfare)። በጊዜው ኤርትራ ውስጥ ተቀማጭነት የነበረው የአሜሪካ ሠራዊት(ቃኘው ስቴሽን) አንዱ ተልዕኮ ይህ ነበር። ከስድስት ዓመታት በፊት ይህን አስመልክቶ ጦማሬ ላይ ቀርቦ ነበር። “አየሩን ሊቀይሩብን – አለመረጋጋት ሊፈጥሩብን?

ይህን ከሃምሳ ዓመታት በፊት  በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የቀረበውን ጽሑፍ(እንደ አጋጣሚ ሆኖ፡ ልክ በዛሬው ዕለት(ዋው!)እናንብብ፦ “ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአሜሪካ ሬዲዮ ጦር ሠፈር ላይ ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡Ethiopians Are Suspicious of Big U. S. Radio Base. https://www.nytimes.com/1970/08/28/archives/ethiopians-are-suspicious-of-big-us-radio-base.html

ዛሬ ግን ኤምባሲዎቹ ናቸው መሬት ውስጥ የተቀበሩ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሃገራችንን በመቃኘት ላይ ያሉት።

ለአምስት ሺህ ዓመታት ያህል ሰፍኖ የነበረውን ጥንታዊ የንጉሣዊ ሥርዓት ሲያስወግዱ የብዙ መቶ ዓመታት ቅደም ተከተል በያዘ የውጊያ ስልት ነው። እስኪ እናስብው፤ በድርቁ፣ ረሃቡ፣ ጦርነቱና በሽታው ሲተናኮሉን ኃያል ሊሆን የሚገባውን ተዋሕዶ ክርስቲያኑን ሕዝብ ለማድከም/ለማዳከም በመሻት ነው። ወገኔ፡ እስከ ዛሬ ድረስ የረሃብ፣ በሽታ፣ ጦርነትና ስደት ሰለባ የሆነው እኮ ሕዝበ ክርስቲያኑ ነው፤ አዎ አሁንም ለውድ ሃገሩ ክቡር ደሙን እያፈሰሰ ያለው ሕዝበ ክርስቲያኑ ብቻ ነው።

እነ ሲ አይ ኤ፣ ሄንሪ ኪሲንጀር እና ጆርጅ ሶሮስ ልክ እንደ አሁኑ ተዋሕዶ ክርስቲያን ያልሆኑትን እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም የመሳሰሉትን ቅጥረኞቻቸውን ስልጣን ላይ ካስቀመጧቸው ጊዜ አንስቶ የሃገራችን የቁልቁለት ጉዞው ያው እስካሁን ድረስ ቀጥሏል።

በእግዚአብሔር ድጋፍ የጽዮን ተራራን እንደገና መውጣታችን አይቀርም፤ ነገር ግን የአቀበቱ ጉዞ አጭር እንዲሆንና ብዙም እንዳያደክመን ማንነታችንን በማወቅ ጠላታችንና ጠላቶቻችንን ያለምንም ይሉኝታ ማጋለጥ እና መምታት ይኖርብናል

_____________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዲያቆን አባይነህ ካሴ | እንደ ኢትዮጵያ መንግስት የገዛ አገሩን ቤተክርስቲያን የሚዋጋ መንግስት በዓለም ላይ የለም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 25, 2019

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያየ መንገድ ጥቃት እየደረሰባት ነው፤ ባለፉት ፵፭ ዓመታት ቤተክርስቲያን በመንግስት ደረጃ ስትገፋ ነው የⷆየችው።

አዎ! በሕገወጥ መንግሥት በደንብ የተቀነባበረ ጂሃድ በተዋሕዶ ላይ እየተካሄደ ነው።

አሁን አሁንማ አይደንቀንም፤ ልክ እነ ጄነራል አሳምነውን በሚገድሉበት ሰሞን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊና የጂሃድ አጋሩ ደመቀ መኮንን ሃሰን ቀደም ብሎ የተዘጋጀውን ምክኒያት እየሰጡ ከኢትዮጵያ ሹልክ ብለው እንደወጡት አሁንም የቁልቢ ገብርኤልን አባታችንን ሲገድሏቸው ወደ ደቡብ ኮርያ እና አሜሪካ ሸሽተዋል። ቅሌታሞች! አቤት የሚጠብቃችሁ ፍርድ! ሞኙ ወገኔ ይህን ሁሉ ዘመን በድክመቱ ገዳዩን መንግስቱ ኃይለማርያምን ለፍርድ ሳያቀርበው በመቅረቱ ሁሉም ንቀውታል፤ ግን ዛሬ እናንተን በድጋሚ እዲሁ ዝም አይላችሁም፤ ምንም ሳታደርጉለት ተቀብሮ የቆየውን ፍቅሩን በነጻ ከሰጣችሁ ሕዝብ የትም አታመልጧትም።

እነዚህን ከሃዲዎች ለፍርድ ለማቅረብና ለመቅጣት የሚያንገራግር የተዋሕዶ ልጅ እራሱ እንደ ክሃዲ ነው የሚቆጠረው። በዚያ ላይ ስለ ራሱ ሰዎች የማያስብ፣ ስለ ግል ራሱም ሆነ ስለሌሎችም ሊያስብ የማይችል ቆሞ የሞተ፤ ሕይወት እያለው በድን የሆነ ሰው ብቻ ነው።

ለክፋት ድል መቀዳጀት አስፈላጊው ብቸኛው ነገር ጥሩ ሰዎች ዝም ማለታቸው ወይንም ምንም ነገር አለማድረጋቸው ነው፡፡

ከአለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል እንደሚባለው ዝምታን አስወግደው ለእውነት የቆሙ፣ ለነጻነትና ለፍትህ የሚናገሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ቦታ ዝምታ ይብቃ በማለት ብቅ ብቅ በማለት ላይ መሆናቸው በጣም የሚያስደስት ነው።

በተዋሕዶ ልጆች ላይ፤ ክርስትያን በመሆናቸዉ ብቻ ግፍ ሲፈጸምባቸው፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲሰደዱ፣ ሲታረዱ፣ ሲቃጠሉና ሲታነቁ፣ ዝም ጭጭ ማለት ከክህደት ይቆጠራል። አውሬዎቹ አሕዛብ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በተከታታይ ሲገድሏቸውና ከእነ ቤተክርስቲያናቸው ሲያቃጥሏቸው ዝም ማለትና ቆሞ መመልከት ትልቅ ክህደት ነው፤ በ ፩ ጢሞቲዎስ ፭፥፰ ላይ የእርሱ ስለሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተሰቦቹ የማያስብ ማንም ቢሆን ሃይማኖትን የከዳ ከማያምን ሰዉ ይልቅ የከፋ ነዉ ሲል ቅዱስ ጳዉሎስ ነግሮናል።

[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።

______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: