Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • July 2019
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for July 30th, 2019

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ችግኝ ተካይ ሳይሆን ፥ እንደ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የቤተ ክርስቲያን ችግኝ የሚሆን አባት እንጅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 30, 2019

ከወር በፊት አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ኃውልት ሥር እሳት መቀስቀሱን ገና አሁን መስማቴ ነው፤ እንዴት ይህን በጊዜው አልሰማነውም? የተቀሰቀሰው እሳት ከየት መጣ? ማን ቀሰቀሰው? የዜና ማሠራጫዎች ለማይረባ ነገር ሃያ አራት ሰዓት ይቅበጣጥራሉ፤ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ላይ ግን ጭጭ። ለምንድን ነው በሲዳማ ስለ ቤተክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ ጅሃድ እስካሁን ምስሎችንና መረጃዎችን ለማግኘት ያልቻልነው? እስኪ ተመልከቱ ስለ ችግኝ ተከላው ጉዳይ ምን ያህል አትኩሮት እንደሰጡት። በጉዳዩ ላይ ሁሉም አካላት(ቤተ ክህነትን ጨምሮ)ሁሉም ፈጥነው ህዝብን ለማነሳሳት በቁ ፤ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጊዜአቸውን፣ ጉልበታቸውና ገንዘባቸውን መስዋዕት አድረገው ለተከላው እንዴት መነሳሳታቸውን ስናይ እራስ ያስነቀንቃል።

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግብፅ የኢሚግሬሽን ሚኒስትር |“በግብፅ ላይ መጥፎ ነገር የሚናገር ሁሉ ይታረዳል”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 30, 2019

ናቢላ ማክራም የተባለቸው ሚንስትሯ ካናዳን ስትጎበኝ በእጇ የመታረድ ምልክት ታሳያለች፡፡ ይመልከቱ!

የዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በግብፅ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመንቀፍ ለሚሞክሩ የካናዳ ዜጎች የካናዳ ባለሥልጣናት ምን ያደርጉ ይሆን?

መግለጫው የቀረበው በቶሮንቶ ከተማ ከሚኖሩ ግብፃውያንካናዳውያን ጋር በተደረገ አንድ ውይይት ወቅት ነው፡፡ ሰው ያጨበጭባል!

የትነው ተመሳሳይ ነገር ሲነገር የተገዙት አድማጮች ሲያጨበጭቡ ሰምተን የነበረው? አዎ! አብዮት አህመድ በእስክንድር ነጋ ላይ ሲዝት።

የሰይጣናዊ አዕምሮ መቆጣጠሪያ መርሃ ግብር መሠረት የሆነው ዒላማዊ የማህበራዊ ቅኝት መመሪያዎች

  • + ከብዙዎቹ (ከብቶች) ጋር ሂድ

  • + ከከብቶች ተለይተህ አትቁም

  • + አትከራከር፤ ጀልባውን አታናውጥ

  • + ባለሥልጣንን አትጠይቅ

  • + አብረህ ሂድ፣ ተስማማ ፥ አሊያ ትገለላለህ

  • + ዝም በል እና ተቀላቀል/ ተደመር

  • + መሪዎችህ እና መገናኛ ብዙኃን የሚነግሩህን ነገር ሁሉ እመን

  • + ማን ነህና ነው ነገሮችን የምትጠይቅ?

_____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: