እኅተ ማርያም | ይህ መንግስት ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ስድስት ዓይነት የሱዳን መተት ተጠቅሟል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 23, 2019
ይህ በታሪካችን ተደርጎ አያውቅም!
ጀግናዋ እኅታችን ትክክል ነች። ከሦስት ሳምንታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ዶ/ር ወዳጄነህ የተባለውን ፓስተር በቪዲዮ አየሁት፤ ወዲያው ፊቱ ላይ የታየኝ መንፈስ ባራክ ሁሴን ኦባማ ላይ የሚታየውን አይነት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው። በዚህ ጉዳይ አንድ ቪዲዮ ለመስራትና የተዋሕዶ ልጆችን ለማስጠንቀቅም እያሰላሰልኩ ነበር፤ ግን ያው እኅታችን ቀደመችኝ… በጣም የሚገርም ነው።
ዶ/ር ወዳጄነህ በጎ ሰው ይመስላል፤ ነገር ግን የ ዶ/ር አብዮት ጠበቃ ይሆን ዘንድ ቀድም ብሎ የተዘጋጀ ሰው ነው የሚመስለኝ። እንዲያውም የዶ/ር አብዮትን “እርካብና መንበር“ የሚለውን መጽሐፍ የፃፈለት የስነ–ልቦና ተመራማሪው ዶ/ር ወዳጄነህ ሆኖ ነው የታየኝ። ጎብዞ ከደፈረ ያለፈውን የምንፍቅና ማንነት እርግፍ አድርጎ መተው አለበት። ቅድስት ማርያም ትርዳው!
Leave a Reply