ባቢሎናውያኑ ለሃገራችን ገንዘቡን እና ድጎማውን ሲነፍጉን፣ በአዲስ አበባ ትራንስፎርመሮችን ሆን ብለው ሲያሰርቁና መብራትን ሲከለክሉን የባቢሎን ኒው ዮርክ ትራንስፎርመሮች መፈንዳት ጀመሩ። ዋው!
በትናንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ሙሉ በሙሉ መብራት በመጥፋቱ ለብዙ ሰዓታት የቆየ ጨለማ ሰፍኖ ነበር፣ የምድር ባቡሮች ቆመውና የከተማዋ እስትንፋስም ቀጥ ብሎ ነበር።
ይህ የተከሰተው ከ42 ዓመታት በፊት፡ እ.አ.አ 1977 ዓ.ም በኒው ዮርክ ተመሳሳይ ችግር ከሰፈነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው።
ልክ በዚህ ጊዜ፡ በዚህ ዓመተ ምህረት ነበር በሃገራችን አረመኔው መንግስቱ ኃይለ ማርያም በሚሊየን የሚቆጠሩ ዘመዶቻችንን በቀይ ሽብር መግደል የጀመረው።
ምናልባት የትናንትናው የኒው ዮርክ ማንሃተን መብራት መጥፋት በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ከተጀመረው የገዳይ አል–አብይ ዳግማዊ ቀይ ሽብር ዘመቻ ጋር የሚያገናኘው ነገር ይኖር ይሆናል። ምናልባት የሚጠቁመን ነገር ሊኖር ይችላል፤ ዓለም እኮ ትንሽ ናት።
በጣም ይገርማል፡ በሉሲፈራውያኑ ቀስቃሽነት በመንግስቱ ኃይለ ማርያም ኮሙኒስታዊ አብዮት ከ42 ዓመታት በፊት ታይቶ የነበረው ጭካኔ ዛሬም በ42 ዓመት እድሜው አብዮት አህመድ በመደገም ላይ መሆኑ በጣም ያሳዝናል።
ኒው ዮርክ እና ለንደን የክርስቶስ ተቃዋሚው የገንዘብና ምጣኔ ኃብት ዋና ከተሞች ሲሆኑ ፥ በርሊን የፖለቲካው፣ ቱርክ እና አረቢያ ደግሞ የመንፈሳዊው መናኽሪያዎች ናቸው።