Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 13, 2019
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ጋባዥነት ምስክርነት እንድትሰጥ የተጋበዘችው ጥቁሯ የቺካጎ ከተማ ክርስቲያን፡ ላታሻ ፊልድስ፡ ምን ዓይነት ከባድ የሆነ የልጅነት ኑሮ እንደነበራት፣ በአስራ ሰባት አመቷ ልጅ እንደወለደች፣ ሁለት ሦስት ቦታዎች እየተመላለሰች ለሥራ ትደክም እንደነበር፤ ሆኖም በክርስቶስ እርዳታ በጣም ጠንካራ ሴት ለመሆን እንደበቃችና የተባረከ ቤተሰብም አምላክ እንደለገሳት ክርስቶስን እያመሰገነች ስትናገር ፥ የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለመሆን የበቃችው ሶማሊት፡ ኢልሃን ኦማር፡ እብደት በተሞላበት መንፈስ፤ “ፀሎት ከችግርሽ እና መከራሽ አያወጣሽም፤ መንግስት እንጅ” በማለት አሳፋሪና አክብሮት የሌለበት መልስ ሰጠቻት።
እርኩስ ጂሃዲስት!
“በቀን አምስት ጊዜ እፀልያለሁ፣ በሂጃብ የተሸፋፈንኩት ለአላህ ክብር ስል ነው” የምትለዋ ሙስሊም ፀሎት አይረዳም ትላለች፤ ዋው! ሁሉ ነገሯ የዱርዬ ነው፤ እርይ በከንቱ ያለች ባለጌ ነው የምትመስለው ፥ ዲያብሎስ የሚጋልባት ነው የሚመስለው።
UPDATE
ወንድሟን ያገባችው ኢልሃን ኦማር የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤትን አንድ ቀን ታፈነዳው ይሆናል። ወንድሞቿ የተለመደውን ጽንፈኛ ተግባር በመፈጸም ላይ ናቸው። ኪስማዮ ከተማ ሆቴል ውስጥ ሠላሳ ሦስት ሰዎች ዛሬ ተገድለዋል፤ በካናዳ ነዋሪነት ያላት ታዋቂ ሶማሊያዊት ጋዜጠኛንና በሃገራችን ላይ ሤራ በመጠንሰስ ላይ የነበሩ ሌሎች የቱርክ ወኪሎችን ጨምሮ።
https://www.voanews.com/africa/somalia-hotel-attack-kills-33
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: Abortion, ሙስሊሞች, ሚነሶታ, ተቃውሞ, አሜሪካ, ኢልሃን ኦማር, ኢየሱስ ክርስቶስ, ክርስትና, የአሚሪካ ተወካዮች ምክር ቤት, ፀረ-ክርስቲያን ሤራ, ፀረ-ክርስትና, ፀረ-ክርስቶስ, Ilhan Omar, Latasha Field, US House Budget Committee, USA | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 13, 2019
ሁለቱ የዓለማችን ጥንታውያን የክርስቲያን ሃገራት የክርስቶስ ተቃዋሚውን በጣም መማረካቸው ሊያስደንቀን አይችልም።
ከመቶ ዓመታት በፊት ሁለት ሚሊየን አርሜናውያን ክርስቲያን ወገኖቻችንን የጨፈጨፈችው ቱርክ ዛሬም አርሜኒያን በማሳደድ ላይ ነች። የገዳይ ግራኝ አል–አብይ አጋር የሆነው እብዱ የቱርክ ፕሬዚደንት ኤርዶጋን አሥር ሺህ ኪሎሜትር ያህል ተጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ በመሄድ አርሜኒያ ተብላ በተሰየመችው የኮሎምቢያ ከተማ አንድ የቱርክ ኃውልትን ለመትከል በቅቷል። ይህ በጣም የሚገርም ነገር ነው።
እንደምናየው ቱርክን የክርስቲያን ሰማዕታት ደም በጣም ያቁነጠንጣታል ያለው። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት አክሱምን ለመቆጣጠር በመሻት ግራኝ አህመድን በመልመል በሃገራችን ላይ ብዙ ጥፋቶችን አስከትላ ነበር። ዛሬም እኛ በጉለሌ ጉዳይ እርስበርስ ስንባላ ለስለስ ባለ መንገድ በሐረር በኩል በመግባት ላይ ናት። በአንድ በኩል፡ ትምህርት ቤቶችን፣ የባህል ማዕከላትን፣ ምግብ ቤቶችንና መስጊዶችን ልስራ እያለች ሰላማዊ በሆነ መልክ ሰተት ብላ ስትገባ ፥ በሌላ በኩል ደግሞ በሶማሊያ ከፍተኛ የጦር ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች። እርኩሷ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ደም ጠምቷታል፤ ስለዚህ ለአርሜኒያ ያሰበችው ለኢትዮጵያም ይሆናል። ከመቶ ዓመታት በፊት በዘመነ ግራኝ አህመድ ከሶማሌዎች ጋር ጥብቅ ግኑኝነት የነበራት ቱርክ ዛሬም በዳግማዊ ግራኝ አህመድ ዘመን ለሶማሌዎች ያላት ዲያብሎሳዊ ፍቅር በጣም ጥብቅ ነው። ዓይናችንን በተለይ በቱርክ ላይ ይሁን!
ሁለቱ ጥንታውያን ክርስቲያን ሃገራት ለቱርክ ውድቀት ምክኒያት ይሆናሉ። ታዋቂው የግሪክ ኦርቶዶክስ አባት ፓይሲዮስ እንደተነበዩት ከሆነ ቱርክን በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እርዳታ የምታጠፋት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት የመከላከያ ሮኬቶችን ለቱርክ የሸጠችላት ኦርቶዶክስ ሩሲያ ናት። Elder Paisios’ Amazing Prophecies About Constantinople
ከቱርክ ጋር የሚያብር፣ ለቱርክ የሚሠራ የሃገረ ኢትዮጵያና አምላኳ ጠላት ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ተዋሕዶ መሪዋ ክርስቶስ ይባላል፤ ኢትዮጵያን(ኃይማኖቷን ተዋሕዶን)የነካ ሐያሉ አምላክ ይገስፀዋል።
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: ሶማሊያ, ቅዱስ ጊዮርጊስ, ቱርክ, አርሜኒያ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኮሎምቢያ, የክርስቲያን ደም, የክርስቶስ ተቃዋሚ, ግራኝ አህመድ, ፀረ-ክርስቶስ | Leave a Comment »