Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • July 2019
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for July 9th, 2019

ሰውዬው አብዷል | ገዳይ አል-አብይ = የሂትለር + ኤርዶጋን + ቢን ላድን እና መንግስቱ ኮክቴል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 9, 2019

የኢትዮጵያን ጠላቶች እንዲህ ገላልጦ የሚያሳየን ቸሩ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

ዓይኑን እንመለከት….

መቼስ፡ ሁሉም ነገር በደንብ የተቀነባበረ ስለሆነ የሚገርም ነገር የለም። ሰውዬው ለክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ሱዳን እና ግብጽ ጠበቃ ሲቆም አዳመጥን? አዎ! የጀግናውን ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ ዮሐንስን አንገት ለቆረጡት ሱዳን ድርቡሾች። ሌላው ደግሞ ሰውዬው ልክ ንግግሩን፡ ያለአግባብ የእግዚአብሔርን ስም በማንሳት፡ ሲያገባድድ ETV ወይም “የኢትዮጵያ” የተባለው ቴሌቪዥን ካሜራውን ወደ ሦስቱ የሃይማኖት መሪዎች አዞረው። ወንበር አያያዛቸው ላይ ስናተኩር፦ በስተቀኝ የተዋሕዶው ፥ በስተግራ የካቶሊኩ ፥ ሁለቱን ክርስቲያኖች ለያይቶ መሀል ላይ ቁጭ ያለው ሙስሊሙ ነው። ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። አይ ሃገሬ!

ግድ የለም፤ ኢትዮጵያዊነትን የተቀበለ፣ ያከበረና ያፈቀረ ዜጋ ብቻ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ የሚረከበው መጭው ትውልድ ይህን ትውልድ እንደሚንቅና እንደሚፈርድ እርግጠኛ ነኝ፤ “እንዴት ኢትዮጵያን ይህን ያህል የሚጠላ እና በጋኔን የተሞላ ወሮበላ ሰው መሪ እንዲሆን ፈቀዳችሁ?” ብሎ መጭው ትውልድ እንደሚኮንነንም በፍጹም አልጠራጠርም።

_______________________

Posted in Ethiopia, Faith, Photos & Videos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የገንዘቡ ዓለም ከፍተኛ ቀውስ | የኢትዮጵያን ባንክ ለመውረስ ሽርጉድ የሚለው የጀርመን ባንክ እራሱ ፈራረሰ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 9, 2019

ኢትዮጵያን አትንኳት!!!

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፯፥፲፮፡፲፯]

ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል። የኃጥአን ክንድ ትሰበራለችና፤ እግዚአብሔር ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።

በአውሮፓ አንጋፋው እና፣ በዓለም አሉ ከሚባሉት የባንክ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነ የጀርመን/ ዶቼ ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ገብቷል፤ የሠራተኞች ደሞዝ መክፈል ስላልቻለ እስከ ሃያ ሺህ ሠራተኞችን ከሥራ ቦታቸው እንደሚያነሳ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን አትንኳት እያልን ስንጠቁም ይህን መሰሉ ክስተት እንደሚፈጸም እርግጠኞች በመሆናችን ነው። “ለረጅም ጊዜ አልገኝም/ አልያዝም ያለችንን ኢትዮጵያን አሁን አገኘናት፣ የእኛን ሰዎች ሥልጣን ላይ አውጥተናል፣ ለሺህ ዓመታት ያቀደነውን እየተገበሩልን ነው፤ አሁን እርስበርስ ሊባሉ ነው፣ የእኛና አረቦች ባሪዎች ሊሆኑልን ነው፤ እልልል!” እያሉ በመደሰት ላይ ያሉት ምዕራባውያን ዔሳውያን እና ምስራቃውያን እስማሌላውያን እራሳቸው አንድ ባንድ በመፍረስከስ ላይ ናቸው።

ልብ ብለን ካየን፤ ችግሩን የሚፈጥሩብን፣ የሚተናኮሉን እና ሤራውን ሁሉ የሚጠነስሱልን እነርሱው፣ ለችግራችን ተቆርቆሪዎች ሆነው የሚጮሁት እነርሱው፣ ለችግራችን መፍትሔ ነው ብለው መርዛቸውን ይዘው የሚመጡት እነርሱው መሆናቸውን እናውቃለን። የተለመደውን አሰልቺ የዲያብሎስ ፎርሙላን፤ Problem – Reaction – Solution እያየን ነው።

ሰሞኑን በተከሰቱት የሃገራችን ሁኔታዎች ላይ ቀድመው ቱልቱላቸውን በመንፋት ላይ ያሉት እነማን እንደሆኑ ስንታዘብ፤ የሃገረ ኢትዮጵያ ጠላቶች የሆኑት የአሜሪካ ድምጽ (VOA) የእንግሊዝ ድምጽ (BBC) እና የጀርመን ድምጽ (DW) መሆናቸውን እናያለን። ስለምን እነድሚያወሩ ምን ያህል ጊዜ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንደሚያጠፉ፣ ማንን ለኢንተርቪው እንደሚጋብዙ ወዘተ ከተከታተልን ምን እንዳቀዱልን ለማየት እንችላለን። እስኪ እንታዘብ፤ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የሚቆረቆሩት ጋዜጠኞች በዶ/ር አህመድ መንግስት እየታሠሩና እየተገደሉ ሲሆን ፥ ምዕራባውያኑን እና አረቦችን የሚያገለግሉት “ጋዜጠኞች” ግን በነፃነት ሲዘዋወሩና ሪፖርት ሲያቀርቡ ይታያሉ።

በተለይ ለእነዚህ ሦስት የሉሲፈራውያን ሜዲያ ተቋማት የሚሠሩ “ኢትዮጵያውያን” ቅጥረኞችና ከሃዲዎች ፥ ለጡረታ ዕድሜ በሚደርሱበት ጊዜ ቀጣሪዎቻቸው የሚገድሏቸው ናቸው። ነፍሳቸውን ይማርላቸውና፤ ብዙዎቹ ሲገደሉ እያየን ነው። የሃበሻ ነገር ሆኖ የሞታቸውን መንስዔ አይጠይቅም እንጅ ነገሮች ቢመረመሩ ብዙዎችን የሚያስደነግጥ ጉድ እየተሠራ እንደሆነ እናይ ነበር። ለጊዜው ስም አልጠቅስም።

መረጃ በቀላሉ በሚገኝበት በዚህ ዘመን እነዚህ ሦስት የራዲዮ ጣቢያዎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ሚና መጫወት አልነበረባቸውም፤ ግን በእኛ ጥሬነትና ድክመት እንዳፈቀዳቸው ጣልቃ እንዲገቡ ዕድሉን አግኝተዋል።

አሁን የሚታየው የጀርመን ባንክ ቀውስ ሙሉውን አውሮፓን ነው አሁን የሚያንቀጠቅጠው። ጀርመን ስታነጥስ አውሮፓ በጉፋን ትያዛለች። በተለይ ከትናንትና ወዲያ ከተያዘው አሜሪካዊ ሕፃናት ደፋሪ ባለኃብት ከጄፍሪ ኤፕሽታይን ጉዳይ ጋር መገጣጠሙ ያለምክኒያት አይደለም። ገዳዩ የሉሲፈራውያኑ ወኪል ዶ/ር አልአብይም ሃምሳ ሺህ ኢትዮጵያውያንን ለአረቦች በባርነት ለመሸጥ መዘጋጀቱም ባጋጣሚ አይደለም። ዲያብሎሳዊ ድፍረታቸው ግን የሚያስገርም ነው።

እኅተ ማርያም ከዓመት በፊት የጠቆመችን፣ እንዲሁም ወንድማችን ከሦስት ዓመታት በፊት የኦሮሞው እንቅስቃሴ የምዕራባውያኑን እና የአረቦችን ውድቀት እንደሚያስከትል በመናገር የተነበዩልን ሁሉ በአሁኑ ሰዓት እየተከሰተ እንደሆነ እያየን ነው።

__________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: