የእስራኤል ፖሊስ አባል አንድ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊ ወጣትን መግደሉ የኢትዮ–እስራኤሎችን ቁጣ ቀስቅሷል። የጠበቃ ድርጅት ኃላፊ እንዳሉት ሰለሞን ተካ የተገደለዉ ባለፈዉ ዕሁድ ሐይፋ ከተማ ላይ ነዉ።
ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ቢሄዱ አያልፍላቸው፣ ወደ አረብ ሃገራት ቢሄዱ አያልፍላቸው፣ ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራሊያም ቢሄዱ ተገቢውን እርካታ–የተሞላበትን ኑሮ መኖር አይቻላቸው። አንድ ሃገር ያላቸው ኢትዮጵያ ናት፡ ነገር ግን እርሷንም ለማጥፋት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ወዴት ለመሄድ?
ሌላ የታዘብኩት፦
1ኛ. በእስራኤል ከኢትዮ–እስራኤሎች ጎን ሌሎች እስራኤላውያን በተፈጠረው ጽንፈኛ ድርጊት ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሳዩና ሲያሰሙ፣ ይታያሉ፤ ሜዲያው ሲነጋገርበት፣ መሪዎች ይቅርታ ሲጠይቁ ይሰማሉ፥ በአረብ ሃገራት በእህቶቻችን ላይ በሚደረሰው ግፍ ላይ ለምንድን ነው አረቦቹ ከኢትዮጵያውያን ጎን ለፍትህ የማይቆሙት?
2ኛ. ላለፉት ወራት በሃገረ ኢትዮጵያ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል፤ የራሳችን ፖሊሶች እናቶችንና ልጆቻቸውን፣ ጋዜጠኞችን እና ተቃዋሚዎችን በማንገላታት ላይ ናቸው። በእስራኤል አንድ ኢትዮጵያዊ ሲገደል የእስራኤል ከተሞች በእሳት ጋዩ፤ በኢትዮጵያ ግን ይህ ሁሉ ግፍ እየተፈጸመ ዜጎች መንገድ ላይ ወጥተው ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት ያልደፈሩበት ምክኒያት ምን ይሆን? የእነ መሀንዲስ ስመኘው፣ የእነ ጄነራል ሰዓረ እና አሳምነው ግድያ ለምን የኢትዮ–እስራኤሎችን ዓይነት ቁጣ አለቀሰቀሰባቸውም? ምን የሚያስተኛቸው ወይም የሚያስራቸው ኃይል ቢኖር ነው?