ሰውየው ልክ ከመሀንዲስ ስመኘው ግድያ በኋላ ተደርጎ እንደነበረው አሁንም ስለ ጄነራሎቹ ግድያ ነገሮችን ለማረሳሳት ሲል ዲያብሎሳዊ ተግባሩን በድራማ መልክ ማቅረቡን ቀጥሏል። ከፊሉን ሕዝባችንን ማታለል ይችል ይሆናል፤ እግዚአብሔርን ግን ማታለል አይቻለውም፤ አምላካችን በቪዲዮ የቀረጸውን ሁሉ በቅርቡ እንደሚያሳየን አትጠራጠሩ።
የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።” ዘጸ. ፳፥፯።
* ይህ ሕግ የሚከለክለውና የሚያስተምረው በሆነው ባልሆነው የእግዚአብሔርን ስም ከመጥራት መታቀብን፣ በሐሰት መማልና መገዛትን ብቻ አይደለም። በቀልድ፣ በዋዛ ፈዛዛና በዘፈቀደ የእግዚአብሔርን ስም ማንሣት፣ ሐሰትን እውነት አስመስሎ ለማቅረብ፣ ሐሰትን የእውነት ሽፋን አድርጎ ስሙን በድፍረት መጥራት የማይገባ መሆኑን ይገልጻል።
የእግዚአብሔር ስሙ ቅዱስ፣ ታላቅና ድንቅ ነው
* የልዑል እግዚአብሔር ስም እንደማንኛውም ሰው ስም በልማድ የምንጠራው አይደለም። ስለሆነም በጸሎተ ዕጣን ጊዜ በመኃልየ መኃልይ “ዘይትህ መልካም መዐዛ አለው፤ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው” እንደተባለ ባማረ ቃል ስሙን እንጠራዋለን። መኃ. ፩፥፲፫። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷ “ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ነገር አድርጓልና ስሙም ቅዱስ ነው” ብላለች። ሉቃ. ፩፥፵፱። አባቷ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊትም እንዲሁ “ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው” በማለት የእግዚአብሔርን የስሙን ቅድስና ተናግሯል። መዝ. ፻፲፥፱። የእግዚአብሔር ስም ቅዱስ በመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ባስተማረው ጸሎት “ስምህ ይቀደስ” እንድንለው ነግሮናል። ማቴ. ፮፥፱።
ስለ ስመ እግዚአብሔር የእኛ ግዴታ
* ይህ ቅዱስ ስም የእግዚአብሔር ስም ነውና ልናከብረው በመፍራትና በመንቀጥቀጥም ልንጠራው ይገባል። ነቢዩ ሙሴ “አምላክህ እግዚአብሔር የተባለውን የተመሰገነውንና የተፈራውን ስም ባትፈራ” በማለት እንዳስጠነቀቀ /ዘዳ. ፳፰፥፶፰/ ስሙን የሚፈሩ የሚያከብሩትም የሚገባቸውን መንፈሳዊ ዋጋ ያገኛሉ፤ በራእይ “ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ” የሚል ተጽፏልና። ራእ. ፲፩፥፲፰።
* የእግዚአብሔር ስም የከበረና ቅዱስ ሲሆን በተራው ነገር ሁሉና በየአጋጣሚው ልንጠራው አይገባም፤ ምክንያቱም በሆነው ባልሆነው ስሙን በመጥራት ልማድ ወደማድረግ ደረጃ ደርሰን ክብሩንና ፍቅሩን እናጣለንና ነው። ከዚህ ይልቅ ልንጠራው የሚገባው በጸሎት ጊዜ ቸርነቱን ስንለምንና ስለተደረገልን ቸርነቱም ስናመሰግን፣ ስጦታውንም ተስፋ በማድረግ መሆን አለበት። ቅዱስ ዳዊት “በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ፤ ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች” “በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ” “ለልዑል እግዚአብሔር ስም እዘምራለሁ” በማለት በተደጋጋሚ የተናገራቸው ቃሎች የሚያስረዱት የእግዚአብሔርን ስም እንዴት ባለ ጊዜና በምን ሁኔታ ልንጠራው የሚገባ መሆኑን ነው። መዝ. ፷፪፥፬ – ፭፤ ፻፬፥፫፤ ፯፥፯።
__________________
Like this:
Like Loading...