እብዶቹ አብዱሎች በእኛ ላይ ያሽሟጠጡ መስሏቸው ነው፤ ግን በክርስቶስ ላይ እየተሳለቁበት ነው፦
የፕሬዚደንት ኤርዶጋን ደጋፊ የሆኑት የቱርክ ሜዲያዎች የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚደንትን የመሀመድ ሙርሲን ሞት በማስመልከት ተሰምተው የማይታወቁ ነገሮችን በመናገር ላይ ናቸው። ፕሬዚደንት ኤርዶጋንን ጨምሮ ሁሉም ሜዲያዎች የግብጹን ፕሬዚደንት አል–ሲሲን፣ የሳውዲውን ልዑል አል–ስለማንን እንዲሁም የአረብ ኤሚራቶችን መሪዎች በሙርሲ ሞት እጃቸው አለበት ይሉናል።
በጣም የሚገርመው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን በጉዳዩ ላይ ለማስገባት መፈለጋቸው ነው፦
+ „ክርስቶስን የሰቀሉት መሀመድ ሙርሲን ገድለውታል”
„Those Who Crucified Christ’ Killed Mohamed Morsi„
+ “ክርስቶስን የሰቀሉት ሰዎች፡ ነቢያችንን መሀመድን ከመካ ያባረሩትና፣ መሀመድ ሙርሲን ከዚህ ዓለም ያሰናበቱት ሰዎች ናቸው”
„Those who crucified Christ, drove prophet Muhammad from Mecca, are the ones who drove Mohammad Mursi from this world”
ሁሌ እንደ አዲስ “ወቸውጉድ!„ የሚያሰኝ ጉዳይ ነው። እስኪ እነዚህ ሦስት ነገሮች እንመልከት፦
፩ኛ. እስልምና፡ ጌታችንን መድኃኒታችንን በማርከስ “ክርስቶስ አልተወለደም፣ አልተሰቀለም፤ ክርስቲያኖች ቀጣፊዎች ናቸው” ይለናል። ታዲያ ሙስሊሞች አሁን ለክርስቶስ መሰቀል እውቅና እየሰጡት ነውን?
፪ኛ. ክርስቶስን የሰቀሉት ሮማውያን ናቸው። ሮማውያን ደግሞ የሰልጁክ ቱርኮች ከመካከለኛው እስያ መጥተው በወረሯት የአሁኗ ቱርክ ወይም አናቶሊያ ግዛት ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ነበሩ። ታዲያ የአሁኗ ቱርክ የቀድሞዋ ምስራቅ ሮማ ግዛት ከነበረች ክርስቶስን የሰቀሉት ቱርኮች ናቸው ማለት አይደለምን? የክርስቶስ ገዳዮች ማን እንደነበሩና ተቃዋሚዎቹ እነማን እንደሆኑ ኤርዶጋን እራሱ እየጠቆመን ይሆን?
፫ኛ. አሁን በአንድ በኩል ቱርክ፣ ካታር እና ኢራን በሌላ በኩል ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኤሚራቶችና ግብጽ ተቀናቃኝ የሆኑ ቡድኖችን ሠርተው እርስበርስ በመፎካከር ላይ ናቸው። ይህ የዲያብሎስ ጨዋታ ነው፤ እርስበስ በመፎካከር እራሳቸውን በሁለት በኩል ለማጠንከር ይሻሉ፤ ሆኖም ሁለቱም ወገኖች ሰይጣን አባታቸውን ነው የሚያገለግሉት(ልክ አሜሪካና ሩሲያ ጠላቶች መስለው የነጭን ዘር የበላይነት ለማቆየት ጠላት–መስለው–ሆነው እንደሚታገሉት፤ አንዱ ሌላውን የሚቆጣጠረው ተቃዋሚ ነው ይሉናል Controlled Opposition)
በአሁኑ ሰዓት አንዱ ይህ ቡድን፤ የሳውዲ፣ ኤሚራቶችና ግብጽ ቡድን ዶ/ር ግራኝ አህመድን ይዘውታል፤ ወደ ቱርክ ብዙም እንዳይጠጋ፣ ቱርክን እንዳይጎበኝ አዘውታል፤ የቱርክ ወዳጅ የነበረውንም የቀድሞ ዲፕሎማትና ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን በፍጥነት እንዲያነሳው ተደርጓል።
ያም ሆነ ይህ፤ እኛ ከእነርሱ መራቅ አለበን፤ እርስበርስ ተበላልተው በቅርብ መጥፋታቸው አይቀሬ ነው !
በነገራችን ላይ፤ በኢትዮጵያ ላይ ሲፎክር የነበረውንና ለብዙ ኮፕት ክርስቲያን ወገኖቻችን ሞት ተጠያቂውን የመሀመድ ሙርሲን ሞት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በታላቅ ሃዘን ነው የተቀበሉት። እስኪ አንዳንድ አስተያየቶቻቸውን እናንብብ፦