Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የአሜሪካ ዲፕሎማቶች | ኢትዮጵያ ከብሔር ፌደራሊዝም ውጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የላትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 17, 2019

መዥገሮቹ የሳጥናኤል ልጆች አይለቁንም!

የውይይቱን ሥነ ሥርዓት የከፈተው ወስላታው “ጆኒ ካርሰን” ነው። ይህ አሜሪካዊ “ዲፕሎማት” ባለፈው ዓመት ላይ “ትግሬዎችን” በማጥላላት በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግስት እንደሚደረግ አውጆልን ነበር። ቪዲዮው እታች ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት መመሪያ አውጭዎች/ አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሰዶሮች ሲሆኑ፤ በግልጽ የሚነግሩንም፡ “የኢትዮጵያ ድብቅ መሪዎች እኛ ነን”። የሚለውን ነው። ከዚህ በፊት ይህን ያህል አይታዩንም/አያሳዩንም ነበር፤ አሁን ግን ነገሮች በግልጽ መታየትና መታወቅ ስለጀመሩ እራሳቸውንና ተግባራቸውን ማሳወቅ ተገድደዋል። እንደሜያቸው የገፋ ጡረተኞች ስለሆኑ ምንም የሚያጡት ነገር የለም። የሚገርም ነው፦ ሴቷ ዲፕሎማት፡ አምባሳደር አውሬሊያ ብሬዚል የሩሲያውን ሰርጌ ላቭሮቭን በጣም ትመስላለች!

እነዚህ የሉሲፈራውያኑ አገልጋዮች የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ወዳጆች አልነበሩም፣ አይደሉም፣ ሊሆኑም አይችሉም። ዲያብሎሳዊ አላማቸው በሕዝብ ቁጥር አንጋፋ እየሆነች የመጣችውን ኢትዮጵያን በመበታተን የሕዝቦቿን ቁጥር መቀነስ ብሎም ለኢትዮጵያ ሰላም፣ አንድነት፣ እድገት፣ ጥንካሬና ሃያልነት የጀርባ አጥንት የሆነችውን ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ማዳከም ነው።

እነዚህ ተንኮለኞች የአሁኑን ሁኔታ ብቻ አይደለም የሚመለከተቱ፤ ከሃምሳ መቶ ዓመታት በኋላ ሊከሰት የሚችለውን እንጂ። አሜሪካና አውሮፓ አሁን ያላቸውን ዓይነት ኃያልነትና ታላቅነት በመጪዎቹ ዓመታት እንደሚያጧቸው ምንም የሚያጠራጥር ነገር አይደለም፤ ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን መጪዎቹን ሃያላን ሕዝቦችን ገና በእንጭጩ መቆጣጠር ይሻሉ።

እነዚህ በአብዛኞቹ አሜሪካውያን ዘንድ የማይታወቁት የእነ ሲ.አይ.ኤ ወኪሎችና “የዩ ኤስ አሜሪካ የሰላም ተቋም” አባላት ናቸው። አሁን ወቅቱን ጠብቀው ባዘጋጁት በዚህ ውይይት ላይ “እኛ” እያሉ (በተረጋጋ መልክ መወያየታቸው እንዳያታልለን) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ ካስተላለፉልን (በተለይ “የእኛ” ለሚሏቸው አንዳንድ የዲያስፐራ ከሃዲዎች) መልዕክቶች መካከል የሜከተሉትን ፲ ነገሮች ማየት ችያለሁ፦

፩ኛ. የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በእኛ በጡረተኞቹ አሜሪካውያን እጅ ነው፤ የእኛን ምክር/ትዕዛዝ መቀበል አለባችሁ

፪ኛ. የዶ/ር አህመድን መንግስት እኛ ነን ያስቀመጥነው፤ አሁን የምንፈልገውን እየሠራልን ነው

፫ኛ. /ር አህመድን ከኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እንዲገናኝ አዘዝነው፤ ከዚያም ለኢትዮጵያ ምንም ነገር እስከማያገኝ ድረስ ተጫወትንበት

፬ኛ. ኢትዮጵያ ከብሔር ፌደራሊዝም ውጭ ሌላ አማራጭ የላትም፤ ክልሎቹ በዚህ መልክ መቀጠል አለባቸው፤ አሊያ እናበጣብጣችኋለን

፭ኛ. የሕዝብ ቆጠራውንና ምርጫውን በፍጥነት ማካሄድ አለባችው

፮ኛ. የሕዝባችሁን ቁጥር መቀነስ አለባችሁ፤ በተለይ የተዋሕዶ ክርስቲያኑን

፯ኛ. የኢትዮጵያ ቴሌኮምን፣ ንግድ ባንክን እና አየር መንገድን በጨረታ መሸጥ አለባቸው፥ ጤፋችሁንም ገና እንነጥቃችኋለን

፰ኛ. ከእኛ ጋር ብቻ እንጂ ከቻይና ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ሊኖራችሁ አይገባም

፱ኛ. ዶላርና ዶናት የምንሰጣችሁ ዲያስፐራ ከእኛ ጋር ተባበሩ፡ አሊያ

፲ኛ. ኢትዮጵያ ስትራቆት ማየት ምርጥ ሲኒማ ነው

______________________

Leave a comment