Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for June 17th, 2019

ኢትዮጵያን ለመውረር ሲዝት የነበረው የግብጽ ፕሬዚድንት መሀመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ ወድቆ ሞተ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 17, 2019

አብዱሎች ሊያብዱ ነው፤ ሰውዬው ለስድስት ዓመታት ያህል እስር ቤት ሲማቅቅ ነበር፤ ሙስሊሞች መሪያቸውን ለማስፈታት ምንም ያደረጉት ሙከራ አልነበረም፤ ታዲያ እነዚህ ደካሞች አሁን ቢያብዱ ምን ዋጋ አለው?!

ሙርሲ ስልጣን ላይ በቆየበት በአንድ ዓመት ውስጥ ደጋፊዎቹ ሃምሳ የሚሆኑ የኮፕት ኦርቶዶክስ ዓብያተክርስቲያናትን አቃጥለዋል። ተመሳሳይ ጽንፈኛ ድርጊት በዘመነ ዶ/ር አህመድ በሀገረ ኢትዮጵያ ም እየታየ ነው።

አቡነ ጳውሎስ እና ጠ//ር መለስ ዜናዊ ከፕሬዚደንት ሙርሲ ጋር ከተገናኙ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር ተከታትለው ያረፉት (ነፍሳችን ይማርላቸው!)የሙርሲ + ኦባማ + አላሙዲ ሤራ! እስኪ ስለዚህ ጉዳይ ዶ/ር አህመድንና ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ጠይቋቸው።

በዚሁ ዕለት የዶ/ር አብይ አህመድ አባት መሞታቸው በአጋጣሚ?

ለማንኛውም በሱዳን እና በግብጽ የሚታየውን ውጥንቅጥ የሆነ ሁኔታን በጥሞና መከታተል ይኖርብናል።

ግብጽ ስትረጋጋ ኢትዮጵያ ትናወጣለች፤ ኢትዮጵያ ስትረጋጋ ግብጽ ትናወጣለች!

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የኤርትራ መንግስት ፳፪ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጤና ማዕከላትን እንዲዘጉ አዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 17, 2019

ባለፈው ሳምንት ላይ የኤርትራ መንግስት ይህን ድርጊት በመፈጸሙ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አውግዛለች።

ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በተላኩ ደብዳቤዎች እንደሚያመለክቱት ሕሙማኖቹ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። ከዚያም ወታደሮቹ ወደ ማእከላቱ ተልከው ንብረቶችን እንዲጠብቁ ታዘው ነበር።

የፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ስለ ቤተክርስቲያኗ አቤቱታዎች ገና አልተናገረም።

በርካታ ተቺዎች በበኩላቸው መንግስቱ ይህን እርምጃ የወሰደው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኤርትራ ወጣቶችን አውሮፓ ስደት በሚገፋፋው ሁኔታ ላይ ለውጥ እንዲደረግ ባለፈው ሚያዝያ ወር በመጠየቋ አሁን እይተበቀላት መሆኑን ይናገራሉ።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ሃያ ሁለት የጤና ማእከሎች ሲኖሯት፣ እናም መዘጋታቸው በሺህ የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን በተለይም በገጠር አካባቢ የሚኖሩ እናቶች እና ልጆቻቸው ያለ ጤና ጥበቃ አገልግሎት ቀርተዋል ተብሏል።

ኢሳያስ አፈወርቂ ይህን ሁሉ ዘመን ሥልጣን ላይ የቆየው ያለምክኒያት አይደለም፤ ይህ ሰው፤ ልከ እንደ ዶ/ር አህመድ ለምድረ ሃበሻ እንደ መቅሰፍት ሆኖ የተላከ ነው። ያሁኖቹ “ኤርትራውያን” እግዚአብሔር የሰጣቸውን ኢትዮጵያዊነት እስከ ካዱ ድረስ ወጣት ኤርትራውያን በየበርሃው የአረብ ሽማግሌ ኩላሊት መለዋወጫ ከመሆን አይድኑም። ኢትዮጵያን በመተው “አማራ”፣ “ትግሬ”፣ “ኦሮሞ” ነን ለሚሉት ግብዞች ይህ ትልቅ ትምህርት ሊሆናቸው ይገባል! ወዮላችሁ እናንት ወስላቶች! እግዚአብሔር እንዳይተፋችሁና ፥ የግብረ-ሰዶማውያን እና መሀመዳውያን መጫወቻ አሻንጉሊቶች እንዳትሆኑ፤ አምላካችን በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው የሚያውቃችሁ።

__________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Health | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የአሜሪካ ዲፕሎማቶች | ኢትዮጵያ ከብሔር ፌደራሊዝም ውጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የላትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 17, 2019

መዥገሮቹ የሳጥናኤል ልጆች አይለቁንም!

የውይይቱን ሥነ ሥርዓት የከፈተው ወስላታው “ጆኒ ካርሰን” ነው። ይህ አሜሪካዊ “ዲፕሎማት” ባለፈው ዓመት ላይ “ትግሬዎችን” በማጥላላት በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግስት እንደሚደረግ አውጆልን ነበር። ቪዲዮው እታች ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት መመሪያ አውጭዎች/ አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሰዶሮች ሲሆኑ፤ በግልጽ የሚነግሩንም፡ “የኢትዮጵያ ድብቅ መሪዎች እኛ ነን”። የሚለውን ነው። ከዚህ በፊት ይህን ያህል አይታዩንም/አያሳዩንም ነበር፤ አሁን ግን ነገሮች በግልጽ መታየትና መታወቅ ስለጀመሩ እራሳቸውንና ተግባራቸውን ማሳወቅ ተገድደዋል። እንደሜያቸው የገፋ ጡረተኞች ስለሆኑ ምንም የሚያጡት ነገር የለም። የሚገርም ነው፦ ሴቷ ዲፕሎማት፡ አምባሳደር አውሬሊያ ብሬዚል የሩሲያውን ሰርጌ ላቭሮቭን በጣም ትመስላለች!

እነዚህ የሉሲፈራውያኑ አገልጋዮች የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ወዳጆች አልነበሩም፣ አይደሉም፣ ሊሆኑም አይችሉም። ዲያብሎሳዊ አላማቸው በሕዝብ ቁጥር አንጋፋ እየሆነች የመጣችውን ኢትዮጵያን በመበታተን የሕዝቦቿን ቁጥር መቀነስ ብሎም ለኢትዮጵያ ሰላም፣ አንድነት፣ እድገት፣ ጥንካሬና ሃያልነት የጀርባ አጥንት የሆነችውን ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ማዳከም ነው።

እነዚህ ተንኮለኞች የአሁኑን ሁኔታ ብቻ አይደለም የሚመለከተቱ፤ ከሃምሳ መቶ ዓመታት በኋላ ሊከሰት የሚችለውን እንጂ። አሜሪካና አውሮፓ አሁን ያላቸውን ዓይነት ኃያልነትና ታላቅነት በመጪዎቹ ዓመታት እንደሚያጧቸው ምንም የሚያጠራጥር ነገር አይደለም፤ ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን መጪዎቹን ሃያላን ሕዝቦችን ገና በእንጭጩ መቆጣጠር ይሻሉ።

እነዚህ በአብዛኞቹ አሜሪካውያን ዘንድ የማይታወቁት የእነ ሲ.አይ.ኤ ወኪሎችና “የዩ ኤስ አሜሪካ የሰላም ተቋም” አባላት ናቸው። አሁን ወቅቱን ጠብቀው ባዘጋጁት በዚህ ውይይት ላይ “እኛ” እያሉ (በተረጋጋ መልክ መወያየታቸው እንዳያታልለን) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ ካስተላለፉልን (በተለይ “የእኛ” ለሚሏቸው አንዳንድ የዲያስፐራ ከሃዲዎች) መልዕክቶች መካከል የሜከተሉትን ፲ ነገሮች ማየት ችያለሁ፦

፩ኛ. የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በእኛ በጡረተኞቹ አሜሪካውያን እጅ ነው፤ የእኛን ምክር/ትዕዛዝ መቀበል አለባችሁ

፪ኛ. የዶ/ር አህመድን መንግስት እኛ ነን ያስቀመጥነው፤ አሁን የምንፈልገውን እየሠራልን ነው

፫ኛ. /ር አህመድን ከኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እንዲገናኝ አዘዝነው፤ ከዚያም ለኢትዮጵያ ምንም ነገር እስከማያገኝ ድረስ ተጫወትንበት

፬ኛ. ኢትዮጵያ ከብሔር ፌደራሊዝም ውጭ ሌላ አማራጭ የላትም፤ ክልሎቹ በዚህ መልክ መቀጠል አለባቸው፤ አሊያ እናበጣብጣችኋለን

፭ኛ. የሕዝብ ቆጠራውንና ምርጫውን በፍጥነት ማካሄድ አለባችው

፮ኛ. የሕዝባችሁን ቁጥር መቀነስ አለባችሁ፤ በተለይ የተዋሕዶ ክርስቲያኑን

፯ኛ. የኢትዮጵያ ቴሌኮምን፣ ንግድ ባንክን እና አየር መንገድን በጨረታ መሸጥ አለባቸው፥ ጤፋችሁንም ገና እንነጥቃችኋለን

፰ኛ. ከእኛ ጋር ብቻ እንጂ ከቻይና ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ሊኖራችሁ አይገባም

፱ኛ. ዶላርና ዶናት የምንሰጣችሁ ዲያስፐራ ከእኛ ጋር ተባበሩ፡ አሊያ

፲ኛ. ኢትዮጵያ ስትራቆት ማየት ምርጥ ሲኒማ ነው

______________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: