Archive for June, 2019
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 30, 2019
በአባታችን በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፦
“እግዚአብሔር አሁን በኛ ዘመን ኃጢአት እጅግ በነገሠበት ወቅት ደግሞ አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን)ሠራዊት በዐይን ቅጽበት ዉስጥ ማርገፍ የሚያቅተው ይመስላችኋልን? እናንተ ሆናችሁ በዓለም ዉስጥ ያለው ትዉልድ ማንም ይህን ማን በዓመፃዉ ከጸናና እጁን ለእግዚአብሔር አልሰጥ ካለ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ አመጸኛ ትዉልድ ረግፎ እንደ ኖኅና ቤተሰቡ ቅንነት፥ የዋህነት፥ እዉነተኛነት የተላበሱትን ሰዎች ብቻ የማያስቀር ይመስላችኋልን?
ስለዚህ “ሠራዊቱ፣ ድኅንነቲ፣ ጠባቂዬ፣ ዘሬ፣ ጎጤ ኃያላን መንግሥታት፤ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት…ወዘት” የሚባሉት እንኳን እናንተን ራሳቸውንም ማዳን እንደማይችሉ በዚሁ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ከእግዚአብሔር ቁጣ ሊድኑ የሚችሉት በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ሲሰጡና በኢትዮጵያ በቅርቡ እግዚአብሔር ለሚዘረጋው መንግሥቱ ለሥጋዊዉም ለመንፈሳዊዉም ሥርዓት ተገዥ ሲሆኑ ብቻ ነዉ። በተቀረ ግን የዓመጻ፣ የክህደት፣ የርኩሰት ጽዋቸዉን እያንዳንዱ መንገሥት፣ ቡድን ፣ ድርጅት፣ ግለሰብ እየጠጣ ነጻነቱ ተገድቦ ወደሚኖርባትና እንደ ዓመጻው ደረጃ ፍዳዉን ወደሚቀበልበት ቦታ መሄድ ነዉ የሚቀረዉ። ይህን ሁሉ የተናገርነዉ መቺስ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ ብለን በማሰብ ሳይሆን የእናንተ ልበ ደንዳናነት ቢታወቅም ባለማወቅ በቅንነትና በየዋህነት አብሮዋችሁ የተሰለፉ ሰዎች ካሉ ከዛሬ ጀምሮ ከእናንተ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲፈጥሩ፣ እንዲሁም በእዉነተኛ ንስሐ እንዲመለሱ ለማሳሰበ ነኡ።” በማለት ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቱን አቀርባለሁ።”
የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን አበው ነፍስ ጋር ይደምርልን!
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ, አባቶች, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያዊነት, ኢየሱስ ክርስቶስ, ከሃዲ ትውልድ, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የእግዚአብሔር መንግስት | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 29, 2019
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: መስዋዕት, አሳምነው ፅጌ, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ዋቄዮ አላህ, ዶ/ር አሳምነው መኮንን, ጄነራል, ጄነራል ሰዓረ መኮንን, ጄነራል ሰዓረ መኮንንን, ጄነራል አሳምነው, ግድያ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 29, 2019
በሰኔ ሃያ ልዕልት ሀያ…
የዱባይ መሪ ሼክ መሐመድ ቢን ራሺድ አል–ማክቱም ሚስት ከተባበሩት ኤሚራቶች አምልጣ ወደ አውሮፓ ሸሽታለች፡፡
የ 45 ዓመቷ ልዕልት ሀያ 31 ሚሊዮን የብሪታኒያ ፓውንድ እና ልጆቻቸውን ይዛ ነው የሸሸችው ተብሏል፡፡
የ 69 ዓመቱ ሼክ፣ ሚስቱን “በክህደት” በመከሰስ በ Instagram ላይ ቁጣውን ለቅቆታል፡፡
ባለፈው ዓመት ላይ የሸኩ ሴት ልጅ ላቲፋ መሀመድ አል ማክቱም ሸሽታ በባህር ላይ ስትንከራተተ እንደነበር የሚያሳየውን ይህን ቪዲዮ አቅርበን ነበር፦
በሃገራችን ላይ ትልቅ ሤራ በመጠንሰስ ላይ ካሉት ግለሰቦች መካከል የዱባዩ ሼክ አንዱ ነው፡፡ የተባበሩት ኤሚራቶች በአሁኑ ሰዓት የዶ/ር አል–አብይን ገዳይ ፖሊሶች እና ኮማኖዶዎች በማሰልጠን ላይ ነው፡፡ ዶ/ር አልአብይ “የጎረቤት ሃገራት የወታደር እርዳታ እናድርግላችሁ በማለት ጠይቀውን ነበር” ብሎ ነበር፤ የኤሜራቶች አራቦች ምናልባት ከፊሎቹ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ግን እነዚህ ፍየሎች ገና፣ ገና ብዙ እርስበርስ ይባላላሉ፣ ገና እሳት ነው የሚወርድባቸው!
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: ልዕልት ሀያ, ሸክ አል ማክቱም, አብይ አህመድ, ክህደት, የተባበሩት አራብ ኤሚራቶች, ዱባይ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 28, 2019
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: ሙቀት, ቀለማት, ቃጠሎ, አውሮፓ, አየር, ኢትዮጵያ, ፈረንሳይ, Europe, France, Heatwave, Summer, Weather | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 28, 2019
ያው እንግዲህ በእኛ ድክመት ሃገራችንን እንዲህ ይከፋፈሉ ዘንድ እድሉን የሰጠናቸው ጠላቶቻችን እየተገለጡልን ነው፤ አንዴ ጥቁሩን ጆኒ ካርሰንን ሌላ ጊዜ ደግሞ አይሁዱን ሄርማን ኮኸንን!
ይህኛው ደግሞ ሄርማን ኮኸን ይባላል። የሰማንያ ሰባት ዓመት አዛውንት ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያስታውሰው በእንግሊዞችና በአሜሪካኖች ተቀነባብሮ በአቶ ሄርማን ኮኸን አጋፋሪነት/“ሽምግልና“፡ ከሦስት ተገንጣይ ብሄራዊ ድርጅቶች (EPLF, TPLF ና OLF – የቪዲዮው ፎቶ ያሳያል)ጋር እ.አ.አ. በ1991 ዓ.ም ላይ በለንደን የተደረገዉ ስብሰባ በዋናነት ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎችን ለስልጣን የሚያበቃና ጥቅም የሚያስጠብቅ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሃገራችን እንድትበታተን የሚያስችል ስትራተጂ የተነደፈበት የኢትዮጵያውያን የጨለማ ቀን ነበር። ኢትዮጵያን በብሔር የሚከፋፍለው ሕገ–መንግስት ለእነዚህ ተገንጣይ ድርጅቶች የተሰጠው በዚሁ ወቅት ነበር።
የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ሄንሪ ኪሲንጀር በኦሮሞዎች የሚመራውን የፀረ–ክርስቲያኑን የደርግ መንግስት ሥልጣን ላይ ለማውጣት እንዲሁም እነ ዶ/ር አምባሳደር ሄርማን ኮኸን የኢሃዴግና ኦነግ ፀረ–ተዋሕዶ መንግስትን ለማደራጀት ትልቅ ሚና ተጫውተው ነበር። (ዶክትሮች)
አሁን ከ፳፰ ዓመታት በኋላ ሁለተኛው የሉሲፈራውያኑ ልሳን (አንደኛው ቪ. ኦ. ኤ. ነው) ቢቢሲ ወስላታውን ሄርማን ኮኸንን ሊገቡ ከተጋጁብት የሲዖል ደጃፍ መልሰው በመጥራት ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያን በመርዛማ ትንፋሻቸው አፍነው ለመግደል ሲሞክሩ ይሰማሉ።
ተዋሕዶ የሰሜን ሰዎች ሥልጣን ላይ እንዳይወጡ ሁሉም ጠላቶቻችን እንደሚሹ ይህ ቃለመጠይቅ ጥሩ ማስረጃ ነው። ቢቢሲን ጨምሮ (የአጠያየቃቸውን ስልት እንታዘብ)በጄነራሎቻችን መገደል ሁሉም እንደረኩና ስልጣን ላይ ያስቀመጡት ገዳይ አብዮት አህመድ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ማስወገዱ ትክክል እንደሆነ በድፍረት/በግልጽ እየጠቆሙን ነው። የሚፈልጉት ይህ ነውና! አዎ! ጭራቅ አብዮት አህመድ ከ666ቱ ነው።
በመካከለኛው አሜሪካ፤ በኒካራግዋ ኒካራግዋንን ሲጨፈጭፍ የነበረው አምባገነናዊ ፕሬዚደንት ሶሞዛን የወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለፕሬዚደንት ሩስፌልት “ሶሞዛ እኮ ጭራቅ ነው” ብሎ ሲነግራቸው፥ ፕሬዚደንት ሩስፌልት፤ “አዎ! ግን የእኛ ጭራቅ ነው” በማለት መልሰውለት ነበር።
አሁን ገዳይ አብዮት አህመድ የእነርሱ ጭራቅ ነው ማለት ነው።
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: ሄርማን ኮኸን, ሕገ-መንግሥት, ቢቢሲ, አብይ አህመድ, ኢትዮጵያ, የብሔር ሤራ, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Herman Cohen | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 27, 2019
___________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia | Tagged: መንቀጥቀጥ, በርሊን, ተሪዛ ሜይ, አንጌላ ሜርከል, ኢማኑኤል ማክሮን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 27, 2019
ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም! — በአገር–ወዳድ ኢትዮጵያውያን ላይ ዘመቻው ጀምሯል፦
አገራችንን እየመሯት ያሉት የተዋሕዶ ኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን መቶ በመቶ መናገር እደፍራለሁ። አዎ! እነ አብዮት አህመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ደመቀ መኮንን ወዘተ ሁሉም የተዋሕዶ ኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው።
ብሔራዊ ማንነትን በየሃገራቱ ለማጥፋት በመላው ዓለም በመታየት ላይ ያለው ሉላዊው እንቅስቃሴ በተለይ በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ላይ ነው በጠላትነት ያነጣጠረው። በሶሪያ እና ኢራቅ የተካሄደው ዘመቻ በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ላይ ነበር፤ ከሞላ ጎደል ክርስቲያኖችን በእነዚህ ሃገራት ለማጥፋት ተችሉቸዋል።
አሁን ትኩረታቸው በኢትዮጵያ ላይ ነው። ያስቀመጧቸው መሪዎች የሰጧቸውን የቤት ሥራ አንድ ባንድ በመሥራት ላይ ናቸው። ላለፉት ሃምሳ አመታት ፀረ–ኢትዮጵያ የሆኑትን ኃይሎች በተለይ “ኦሮሞ” የተባሉትን የኢትዮጵያ ጠላቶች በማደራጀት ላይ ነበሩ፤ ነገሮች በአንዴ አልመጡም፤ ቀስበቀስ ነው። ደርግና ኤሕአፓ እርስበርስ ተቃራኒዎች በመመሰል የኢትዮጵያን ጥንካሬና አንድነት የሚጠብቁትን ጄነራሎች፣ ሚንስትሮች፣ ዳኞችና መምህራን ባሰቃቂ መልክ እረሸኑ፣ ተተኪውን ኢትዮጵያዊ ትውልድ ለማድከም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ የተዋሕዶ ወጣቶችን ገደሉ፤ በዚህም ኢትዮጵያን አዳከሟት፣ አዋረዷት፥ ኢትዪጵያዊነትን አረከሱት።
ወገኖቼ፤ ታሪክ እየተደገመች ነው፤ አሁን እነ አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የምንጠራ ዘመቻ በደርግ ጊዜ ኢትዮጵያን ለማድከም ከሚካሄደው ዘመቻ ጋር በጣም የሚመሳሰል ነው። ብዙ ልምድ ያላቸውን አገር–ወዳድ ጄነራሎችና የጦር መሪዎች ደርግ ሲረሽናቸው፤ የሶማሊያ እስላማዊ ሠራዊት አጋጣሚውን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ሰተት ብሎ እንደገባው፤ አሁንም እነ ዶ/ር አህመድ ልምዱ ያላቸውን እና የሃገር ፍቅር ያላቸውን የጦር መሪዎች በመግደል ላይ ይገኛል። “የጎረቤት ሃገራት እርዳታ ሊያደርጉልን ዝግጁ ነበሩ” ማለቱ የግብጽ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ እስላማዊ ሠራዊቶች ወደ ኢትዮጵያ ሰተት ብለው እንዲገቡ ልፈቅድላቸው ነው” ማለቱ ነው። ግብጽ የሕዳሴው ግድብ የሚገኝበትን እና ሆን ተብሎ ለዚህ ወቅት የተከፈለውን “ቤኒሻንጉል–ጉሙዝ” የተባለውን ክልል ለመቆጣጠር በመዘጋጀት ላይ ናቸው፤ በዚህ ክልል እና በሱዳን የተፈጠረው ህውከት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው።
የእነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሤራ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ኢትዮጵያን ለመበታተን አይቻላቸውም፤ ነገር ግን ብዙ ጥፋቶችን ያጠፋሉ፤ ለዚህም በተለይ ያልነቁና በደፈናው ሁሉንም አቅፈው አንድ ለመሆን የሚመኙት ሞኝ ኢትዮጵያውያን ተጠያቂዎች ናቸው። ከማን ጋር፣ ምንን ይዘን፣ በማን ሥር ነው አንድ የምንሆነው? ይህ ድብልቅልቅ ሁኔታ ከዚህ ቀደም ስንሄድበት በነበረው የኑሮ ጎዳና እንዳንጓዝ ጥሩ እድል ሰጥቶናል፤ ማን የኢትዮጵያ ጠላት እንደሆነ ለማየት አጋጣሚውን ፈጥሮልናል፣ አዝማቹ ጠላት በሞተ ሥጋ የማያርፍ ዲያብሎስ እንደሆነ በብሩህ ልቡና እንድናውቅ ረድቶናል፡፡ በመልካም እርሻ /ማሳ/ የተዘራው ንጹሕ ስንዴና ጠላት ጨለማ ለብሶ በስንዴው ማሳ ላይ የበተነው እንክርዳድ እስከ መኸር ጊዜ ዐብረው እንደሚኖሩ ጌታችን ራሱ ባለቤቱ በቅዱስ ወንጌል አስተምሮናል [ማቴ. ፩፫፥፳፬፡ ፴፩]ይህ የማይሻር ቃል ስለሆነ ሌላ ምን ይባላል?
አባቶቻችን ባቆዩልን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ ዛሬም ግልጽ የሆነ ጦርነት ተከፍቶባታል። ይህች ሃይማኖት ጥንታዊት፣ የቀናችና የጠራች ስለሆነች ተካታዮቿን የምታኮራ እንጂ የምታሳፍር አይደለችም፡፡ በሰዎች የግል ድካም እንጻርም አትመዘንም፡፡ ለመከራም አትበገርም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን እስከ ዛሬ ድረስ በእምነቷ፣ በጾሟና በጸሎቷ የማያቋርጥ የገቢረ-ተአምራት ወመንክራት፣ ኀይላትም ሥራ ስትሠራ የምትገኝ ለተከታዮቿ ተስፋ ሆና የምትኖር እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ርግጥ ነው፤ በቅን ልቡናና በትሑት ሰብእና ለተቀበለው ሸክሟ ቀላል ቀንበሯ ልዝብ ነው፡፡ ዳሩ ግን በገድል የተቀመመ ሕጓ፣ ባህሏና ሥርዐቷ ጥብቅ ስለሆነ የሕግና የሥርዐት ቀንበር ላለመደ ስስ ጫንቃ አይመችም፡፡ መንገዱ ቀጭን፣ በሯ ጠባብ ነው፡፡ የእግዚአብሔርም መንግሥት የምትወርሰው በመከራ መስቀልና ብዙ ትዕግሥት፣ በዚሁ ቀጭን መንገድ ተጉዞና በጠባቡ በር ዐልፎ ስለሆነ በቀና ሃይማኖት ጸንቶ፣ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሕይወቱን = አኗኗሩን በሥነ ምግባር፣ ገዝቶ በአበው፣ መንፈሳዊ መንገድ መጓዝ ለክርስቲያን አምላካዊ ትእዛዝ ነው፡፡ ማቴ. ፯–፲፫–፭ የሐዋ.፲፬–፳፪ ይህ ጠባብ በርና ቀጭን መንገድ የሃሪካችን መዛባት የለበትም፡፡ ተቆርቋሪዎች እንሁን፡፡ የወይራ ዛፍ ተቀጥላው ብሳና ቢሆን እጅግ ያሳፍራልና፡፡ በነገረ ጠቢባን «ሳይረቱ አይበረቱ» ተብሏልና፡፡
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: መንፈሣዊ ውጊያ, ምዕራባውያን, አብይ አህመድ, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያዊነት, እምነት, ክርስትና, የቤተክርስቲያን ፈተና, የተዋሕዶ ተቃዋሚ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ, የኢትዮጵያ ጠላቶች, የክርስቶስ ተቃዋሚ, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, ፖሊሶች | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 26, 2019
የጉዞ ወኪሉ፦
“እናንት የሰው ፍጥረታት አይደላችሁም ተብለን፡ የጥቃትና ግድያ ዛቻ ሰለተሰጠን በጥቅምት ወቅት ያሰናዳነውን ጉዞ ሰርዝነዋል፡፡ የኢትዮጵያን ቅዱሳት ቦታዎች የመጎብኘት እቅድ ነበረን፤ ይህን ቅሌት የዓለም ማህበረሰብ ማወቅ ይገባዋል፤ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡” በማለት በሃገራችን ላይ ዝቷል። “የራሳቸውን ልጆች በመኖሪያ ቤታቸው የሚገድሉ፥ እኛንማ ገድለው ከበሉን በኋላ አኝከው ይተፉናል” በማለት በፍርሃት የተደናገጡ ይመስላሉ፡፡ ምናልባት ዶ/ር አብያቸውን ላለማዋረድ አስበው ይሆናል፤ ለማንኛውም ፕሮፓጋንዳው ተሳክቶላቸዋል!
ሌላ ማስረጃ፦ አላህ = የግብረ–ሰዶማውያን አምላክ
የሚገርመው ይህ ግብረ–ሰዶማዊ “ባሃይ” የተባለውን የእስልምና እምነት የተቀበለ መሆኑ ነው፡፡ በሃገራችን የምናስታውሰው፤ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኝበት የነበረው የቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን መቃብር በሙሉ ሲነሳ በላይ በኩል ለብቻው ተከልሎ የተሠራው የባሃይ ሙስሊሞች መቃብር እንዳይነካ መደረጉ ነው፡፡
ከጥቂት ዓመታት በፊት ሃዘኔን ለሚመለከታቸው አቅርቤ ነበር፤ “ኢትዮጵያውያን በአገራቸው የመቅበሪያ ቦታ እንኳን ሲነፈጋቸው፤ የኢትዮጵያውያንን አስከሬን በሃገሮቻቸው ምድር መቅበር የማይፈልጉት አረቦች ሬሳዎችን ቀይ ባህር ላይ ይጥሏቸው እንደነበር፤ ታዲያ አሁን ለእነዚህ እርኩሶች የተለየ መቃብር በኢትዮጵያ መሰጠቱ በሃገራችን ላይ መቅሰፍቱን ያመጣብናል”
ከዚህ በተጨማሪ፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “ፀሀይ” የተባለውን ሕፃናት–በራዥ የልጆች ፕሮግራም የሚያዘጋጁት የባሃይ እመነት ተከታዮች ነበሩ። አዎ! በኢትዮጵያ!
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: መንፈሣዊ ውጊያ, ምዕራባውያን, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያዊነት, እምነት, ክርስትና, የቤተክርስቲያን ፈተና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ, ጉብኝት, ግብረ-ሰዶማውያን፣, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 25, 2019
ፓሪስ፣ ለንደን፣ በርሊን፣ ማድሪድ፣ ወዘተ ታይቶ በማይታወቅ ሙቀት እየተቃጠሉ ነው…ከሦስት ቀናት በፊት በማርክሮን ፈረንሳይ እንዲህ ሃይሎ የማያውቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር (5.1)…
የዛሬዋ ኢትዮጵያ “አርኤል”ን (የጽዮን ተራራን) ታስታውሰናለች፦
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፳፱፥]
፩ ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፥ በዓላትም ይመለሱ።
፪ አርኤልንም አስጨንቃለሁ፥ ልቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።
፫ በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፥ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፥ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።
፬ ትዋረጂማለሽ፥ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፥ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል።
፭ ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል።
፮ ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
፯ በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል።
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ሙቀት, ትንቢተ ኢሳያስ, አርኤል, አውሮፓ, ኢትዮጵያ, የጽዮን ተራራ, የፍርድ ቀን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Europe, Heatwave, Judgment Day | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 25, 2019
አዞ እየበላ እንደሚያለቅሰው… እነደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች በግሌ ብዙ ነው የማውቀው
የየዋሁን ኢትዮጵያዊ ልብ ለመስረቅ ነው ይህ ሁሉ አሳዛኝ ድራማ። የቀረችውን ልብ ለመስረቅ እንዲህ ሲሰባሰቡ ትንሽ አያፍሩም? ምነው ወገኔ፤ እነዚህ ውዳቂ ወሮበሎች ይህን ያህል እንዴት ያታሉልሃል? ምን አቅመሰውህ ቢሆን ነው?
አብዮት አህመድ ፊት ለፊት የሚናገረውን ነገር ሁሉ በተቃራኒው ነው መተርጎም ያለብን፦
-
“መግደል መሸነፍ ነው” ሲል “እኔ ብቻ መግደል እችላለሁ” ማለቱ ነው
- መደመር ሲል ፥ መቀነስ ማለት ነው
-
„የቀን ጅቦች” ብሎ ሌሎችን ሲወነጅል ፥ “የቀን ጅቡ” እኔ ነኝ ማለቱ ነው። እኅተ ማርያም፤ “ቀን ሰው ሌሊት አውሬ ነው” ያለችው ትክክል ነው
-
“ግብረ–ሰዶማውያን” እያለ ወደ ሌሎች ያመለክታል፤ ግብረ–ሰዶማውያኑ ግን እርሱ እራሱ ነው
-
“ኢትዮጵያ” ሲል “አረቢያ”፥ “ክርስትና” ሲል “እስልምና” ማለቱ ነው
ለተገደሉት ነፍሳቸውን ይማርላቸው፣ ገዳዮቹን እግዚአብሔር ይበቀላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ያጽናናቸው!
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: ለቅሶ, መስዋዕት, አሳምነው ፅጌ, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ዋቄዮ አላህ, የቀበር ሥነስርዓት, የአዞ እንባ, የገዳይ መንፈስ, ጄነራል, ጄነራል ሰዓረ መኮንን, ጄነራል ሰዓረ መኮንንን, ግድያ | Leave a Comment »