Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2019
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሶማሊያን የጠቀለለ የኢትዮጵያን ካርታ ተጠቀመ | ሶማሌዎችን ለመቆስቆስ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2019

 

የግራኝ አህመድ መንግስት ይህን ሆን ብሎ ለተንኮል ተጠቅሞበት ነው የሚሆነው። ሶማሌዎችን ለማነሳሳት!

ኢትዮጵያን የሚጠሏት ሶማሌዎች እንኳን አገራቸው ከካርታ ላይ ጠፍታ፡ የኢትዮጵያ ስም ገና ሲነሳባቸው ነው ልክ በመርፌ እንደተወጉ ያህል በጩኸት የሚዘልሉት። ለነገሩማ አገራቸውን ያጠፏት እራሳቸው ናቸው፤ ኢትዮጵያን በመተናኮላቸው።

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው የአፍሪካን ካርታ በድረ ገፁ ላይ በመጠቀሙ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሶማሊያ የሌለችበት የአፍሪካ ካርታ መጠቀሙንና በምትኩ ሶማሌ ላንድ ራሷን የቻለች አገር አድርጎ አቅርቧል ሲል ሚሞ የተባለው የሶማሊያ ሚዲያ ድርጊቱን ኮንኖታል።

መሥሪያ ቤቱ ካርታውን የተጠቀመው ባለፈው ቅዳሜ የተከበረውን የአፍሪካ ቀንን አስመልክቶ በፃፈው ጽሁፍ ላይ ነበር።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦፊሴላዊ ድረ ገፁ የተጠቀመው የአፍሪካ ካርታ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ግዛት እንደሆነች ተደርጎ ቀርቦበታል።

በካርታው ላይ በሶማሌ ላንድ የምትገኘው ሃርጌሳ አስተዳዳር ራሷን የቻለች አገር እንደሆነች አሳይቷል።

ካርታው በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተዘዋወረ ከሰዓታት በኋላ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ካርታውን ከገፁ ላይ ያጠፋው ሲሆን በኢፌዴሪ አርማ ተክቶታል።

ስህተቱ በፈጠረው ውዥንብር መፀፀቱን የገለፀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቡድኑ የድረ ገፁን ደህንነት ለማረጋጋጥ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኮሎኔል አህመድ ጦርነት በጣም ናፍቆታል። የሲ አይ ኤ አምባሳደር ሆኖ በብዙ መቶ ሺህ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን መገደል ምክኒያት በሆነው፤ ለባድሜው ጦርነት ወደ ሰሜን ዘምቶ የነበረው ይህ ሰው የተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ደም አሁን ጠምቶታል። ለዚህም የግብጹ አል ሲሲ አምባሳደር በመሆን አንዴ ከኢሳያስ አፈወርቅ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ኬኒያ መሪዎች ጋር በመምከር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጦርነት ለመቀስቀስ እየተወራጨ ነው። በኢንጂነር ስመኘው ቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ (“እንትና የሚባል ሰው ተገድሏል አሉ” ነበር ያለው አሜሪካ ሆኖ፤ አይደል?) አለመገኙትን የመረጠው ዶ/ር አብዮት አህመድ ሞኙ የሰሜን ሕዝባችንን እርስበርስ ለማባላት ምኞቱ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ራያ፣ ወልቃይት፣ ቤኒሻንጉል እያለ እሚቀበጣጥረውም ያለምክኒያት አይደለም።

የሱዳን አዲሱ ወታደራዊ መንግስት መሪዎች ሰሞኑን ከግብጹ አልሲሲ ጋር መገናኘት አዘውትረዋል። ግብጽ ዳግማዊ ማህዲን ካርቱም ላይ ለማስቀመጥ ወደ ሱዳን ወታደሮቿን ለመላክ በመዘጋጀት ላይ ናት።

የኢትዮጵያ ሠራዊት በዋቄዮ አላህ ልጆች፣ በሰዶማውያን እና በሴቶች መሪነት እንዲዳከም እና ሕዝቡም እራሱን ለመከላከል እስከማይችል ድረስ እርስበርስ ተባልቶ እንዲኮላሽ ከተደረገ በኋላ ከተደረገ በኋላ በዙሪያችን ባሉ ጎረቤት ሃገራት ያጠናከሯቸውን ሠራዊቶች ወደ ኢትዮጵያ መላክ ይጀምራሉ፤ ልክ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመን እንደነበረው።

ኢትዮጵያ ተከብባለች” ስል አስራ አምስት ዓመት ሊሞላኝ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ እንዲህ ነው የተከበበችው፦ በኤርትራ ሳውዲ አረቢያ እና ኤሜራቶች፣ በሱዳን ግብጽ፣ በሶማሊያ ቱርክ፣ በጂቡቲ አሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስፔይን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ጃፓን፣ ህንድ እና ቻይና በመጠጋጋት ሠፍረው “ታላቁን ቀን” በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ግን በቀድሞዋ ግዛቷ ከኢምባሲ በቀር እና ለወደብ ከመክፈል ሌላ ምንም ነገር የላትም። የሃፍረት ዋው!

__________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: