ዓለም እጅግ አደገኛ የሆነው መንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ናት፤ ከ ጠላቶቻችን ጎን ሰይጣን አለ፤ ከእኛ ጎን ኢየሱስ ክርስቶስ አለ!
“ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።” [፪ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ምዕራፍ ፫፥፫]
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፰፥፪፡፬]
“እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ።”