Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2019
ፕሪያንካ ቾፕራ በህንድ አገር/ በቦሊውድ ትኩስ፣ ታዋቂና ኃብታም ከሆኑት ተዋናይቶች መካከል አንዷ ናት። ከሃያ ዓመታት በፊት የአለም የቁንጅና ውድድር አሸናፊ የሆነችዋ ፕሪያንካ በአሜሪካዋ ሆሊውድ በፊልም ተዋናይነት ስኬታማ ከሆኑት ጥቂት የህንድ ተዋናይቶች መካከል አንዷ ናት። ዶ/ር አብዮትን የ2019 ዓመት ከ100 ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ያደረገው የኢሉሚናቲዎቹ “ታይም መጽሔት” ፕሪያንካ ቾፕራንም በ2016 ዓ.ም ላይ መርጧት ነበር።
ከትናንት ወዲያ ኢቫንካ ትራምፕ፣ ትናንትና የኔዘርላንድሷ ማክሲማ፣ ዛሬ ደግሞ የህንዷ ፕሪያንካ፤ ተልዕኳቸው ብቻ ሳይሆን ስማቸውም ሳይቀር ተመሳሳይ ድምጽ አለው። የማሕበረሰባዊነቱን ካርድ መዝዘው በቡና እና በእስክስታ በኩል እየገቡብን ነው!
Priyanka Chopra Visits Schoolchildren in Ethiopia as an UNICEF Goodwill Ambassador… After Wowing at Cannes Film Festival

__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia | Tagged: ህንድ, ሆሊውድ, ቦሊ ውድ, ተዋናይት, የተባበሩት መንግስታት፣ ኢትዮጵያ, ጉብኝት, ፕሪያንካ ቾፕራ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2019
የጀርመን ሕግ መንግስትን በማስመልከት ተዘጋጅቶ በነበረው በዚህ ልዩ የክብር በዓል ሳምንት፡ የጀርመን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቅርንጫፍ፡ የሆነው ኤም.ዲ.አር ቴሌቪዥን እና ራዲዮ፡ ሃያ ሺህ ለሚጠጉ ጀርመናውያን፡“እስልምና ጀርመን ውስጥ ቦታ አለውን?”የሚል ጥያቄ በስልክ፡ አቅርቦላቸው ነበር።
መልሱ ግልጽ ነው፦ 4% ብቻ አዎ!ሲሉ፤ 96% ው የለም! እስልምና ቦታ የለውም፤ አንፈልገውም በማለት ተቃውሟቸውን ገልጠዋል።
የዳሰሳው ጥናት በተለይ በስልክ መካሄዱ ጉዳዩን ከበድ ያደርገዋል።
ያው እንግዲህ፤ አውሮፓውያን እስልምና የሚባል እርኩስ ርዕዮተ ዓለም ወደ አገሮቻቸው እንዳይገባ ይፈልጋሉ፤ ሉሲፈራውያኑ የመንግስታቱ እና የአውሮፓው ህብረት መሪዎች ግን የአይሁድና–ክርስቲያናዊ ስልጣኔን ከአገሮቻቸው በማጥፋት ለአንድ የሉሲፈራዊ የዓለም መንግሥት ምስረታ ስለሚታገሉ እስልምና እና ሙስሊሞች ለጊዜው አጋሮቻቸው እንዲሆኑ ወስነዋል። በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩትን ጥገኛና በጥባጭ ሙስሊሞችን ወደ አገሮቻቸው እያስገቡ ለፀረ–ክርስትና ተልዕኳቸው እንደ መሳሪያ እየተጠቀሙባቸው እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው። ሕዝቡ አሁን እየነቃ መጥቷል፤ ምርር ብሎታል፤ ለጊዜው ቤቱና ሆዱ ሙሉ ስለሆነ ስሜቱን በአደባባይ እምብዛም አያሳይም፤ ሆኖም በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት አስከፊ የሆነ ፀረ–እስልምና ዘመቻ በሙስሊሞች እና ደጋፊዎቻቸው ላይ እንደሚካሄድ ምንም የሚያጠራጥር ነገር አይደለም። የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ኢ–አማንያን እርስበርስ ይጨራረሳሉ ማለት ነው።
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: ARD, መስጊድ, አውሮፓ, እስልምና, የዳሰሳ ጥናት, ጀርመን, ጥላቻ, ፀረ-እስልምና አቋም, Germany, Islam, MDR, Survey | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2019
ይህን ባየንበት ወቅት የሁላችንም እምባ መጥቶ ነበር። ዛሬ ማክሰኞ ነው፤ እግዚአብሔር፦ የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፦ ሕያው ነፍስ ላለውም ሁሉ ስም ያወጣላቸው ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። እግዚአብሔር ሰኞ ማክሰኞ አዕዋፋትን አመጣለት፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበርና አጭቶ፥ ወድዶ፥ ፈቅዶ እንዲገባበት ሔዋንን ከጎኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ሴት አድርጎ ሠራለት። አዳምም፦ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” ብሎ እግዚአብሔር የሰጠውን በጸጋ ተቀበለ።
አዳምና ሔዋን በጋብቻ አንድ አካል መሆናቸው፦ ሔዋን ከአዳም የጎን አጥንት በመፈጠሯ ብቻ አይደለም። አንድ ክብር በመውረስም ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ “እናንተ ባሎች ሆይ ፥ ደካማ ፍጥረት ስለሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድረጋችሁ አክብሩ አቸው።” ያለው ለዚህ ነው። ፩ኛ ጴጥ ፫፥፯። ከዚህም ሌላ አንድነታቸው አንድ ልብስ በመልበስ ነው። ፈቃደ ሥጋቸው በጠ የቃቸው ጊዜም በግብር አንድ ይሆናሉ። ወንድ ቢወለድ ያንተ ነው፥ ሴት ብትወለድ ያንቺ ነው አይባባሉም። ሁለት ሆነው አንድ ልጅ ያስገኛሉ። አንድም፦ ከእናት ደም ፥ ከአባት ዘር ተከፍሎ አንድ ሰው ሁኖ ይወለዳል።
የጋብቻ ዓላማዎች ሦሰት ናቸው፦
የመጀመሪያው። “የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት” እንዲል፦ ለመረዳዳት ነው። መረዳዳት ሲባልም በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስም ጭምር ነው። ለሥጋቸው በሥራ ሲረዳዱ ለነፍሳችው ደግሞ በጸሎት ይረዳዳሉ። ለምሳሌ፦ ይስሐቅ፦ ሚስቱ ርብቃ ለሃያ ዓመታት መክና ልጅ አልወለደችለትም ነበር። በዚህም ምክንያት ስለ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ፥ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም መንታ ፀነሰች ይላል። ዘፍ ፳፭ ፥፳፩። ሁለተኛው በፍትወተ ሥጋ ላለመቸገር ነው። ሦስተኛው ደግሞ፦ “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ፥እግዚአብሔርም ባረካቸው ፥እንዲህም አላቸው፦ ብዙ ተባዙ ፥ምድርንም ሙሉአት።” እንዲል፦ ዘር ለመተካት ነው። ዘፍ ፩፥፳፰። እነዚህም እንደ ሦስት ጉልቻዎች የሚቆጠሩ ናቸው።
አዎ! እግዚአብሔርን ስንቀርበው ፥ ይቀርበናል፤ ስንረቀው ይርቀናል። እግዚአብሔርን በቀረቡ ተዋሕዶዎች ዘንድ ፩ + ፩ = ፩ ሲሆኑ እግዚአብሔርን በራቁት በሌሎች ዘንድ ግን ፩ + ፩ = ፪ ናቸው። ስለዚህ ቅዱስ ጋብቻ በሌሎች ዘንድ የለም ለማለት ያስደፍራል…በሌሎች ዘንድ ሁሉም ነገር ሂሳብ ነው፡ ዓለማዊ ነው፤ ከጋብቻ በፊት “መልአክ” የተባለ የትዳር ጓደኛ ከጋብቻ በኋላ “ሰይጣን” ይባላል። በመላው ዓለም እንደምናየው ወንዱ ወንድነቱን ሴቷ ሴትነቷን በማጣት ፍቅር–አልቦች፣ አመጸኞች እና ጨካኞች ለልጆቻቸው ነፍስ የማይቆረቆሩ ግድ–የለሾች ይሆናሉ፤ ትዳራቸውም የሲዖል ነው። ይህ ክስተት ዛሬ “ለዘብተኞች”፣ “ፌሚኒስቶች” ፣ “ሰዶማውያን”፣ “መሀመዳውያን” በሚባሉት ዘንድ በደንብ እየተንጸባረቀ ይታያል።
ኢትዮጲያዊ ሲፋቀር አቤት ሲያምር ፥ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ጎዳና ሲራመዱ ሁሉም መዋደዱ! የምንጓዝበት መንገድ መንፈሳዊ ከሆነ በሁሉም በኩል ሰላም፣ ፍቅር፣ ብልጽግና እና ደስታ ሲነግሱ እናያለን፤ እርግቦቹ (መንፈስ ቅዱስ) እንደሚያሳዩን።
ታላቋ አገራችን ከተዋሕዶ ውጭ የሚገኙትን ትርኪምርኪ መጤ የምዕራባውያንን (ዔሳው)እና የአርቦችን(እስማኤል)አምልኮቶችን፣ ርዕዮተ-ዓለሞችንና ባሕሎችን አስገብታ መቀበል ስትጀምር ነው ፍቅር እየቀዘቀዘ፣ ሰላም እየጠፋባት፣ እንስሳቱ፣ አራዊቱ እና አዕዋፋት እየራቁባት፣ ድርቅ፣ ረሃብ እና በሽታ እየሰፈኑባት፤ ባጠቃላይ እያነሰችና እየወደቀች የመጣችው።
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: መስከረም ፪ሺ፲፩, መንፈስ ቅዱስ, ሥርዓተ-ተክሊል, ቅኔ, ትዳር, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, እርግቦች, እግዚአብሔር አብ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጋብቻ, ፍቅር, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »