Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • May 2019
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

በመቅደላ ውጊያ ከኢትዯጵያ የተዘረፉትና በለንደን የሚገኙት ፲፩ ታቦታት “በውሰት” ሊመለሱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2019

የብሪቲሽ ብሄራዊ ሙዚየም ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በነበረው የመቅደላ ውጊያ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱት እነዚህ ታቦታት በውሰት ሊመልስ ነው።

የሙዚየሙ ሀላፊዎች ጽላቶቹን በመመለሱ ረገድ ሀሳቡን እንደሚጋሩትና የህግ ጉዳይ ሆኖ በነፃ ለመመለስ መወሰን ባይችሉም ታቦቶቾን በረጅም ጊዜ ብድር ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ በቦታው ለተገኙት ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በሙዚየሙ የሚገኙ ታቦታት ለኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ልዩ ክብርና ቦታ ያላቸው ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙባቸው ህያው በመሆናቸው ወደ ትክክለኛ ቦታቸው እንዲመለሱ ጠይቀው ነበር

ከእነዚህ ፲፩ ታቦታት መካከል ፱ኙ ከእንጨት ሲሆኑ ፪ቱ ደግሞ ከድንጋይ ናቸው። ሁሉም በእዚህ የብሪቲሽ ሙዚየም ድብቅ የዕቃ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደተቀመጡና እስከ ዛሬ ድረስ፤ ኃላፊዎቹንም ጨምሮ፤ ማንም ከፍቶ እንዳላያቸው ተጠቁሟል። ታቦታቱ ላይ ምናልባት የተቀረፀ መስቀል ሳያርፍባቸው አይቀርም ተብሏል።

በሌላ በኩል የሙዚየሙ ሃላፊዎች ኢትዮጵያን መጎብኘትና አብረው ለመሥራት እንደሚፈልጉ፣ ወደፊት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡም የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ ገልጸዋል

የኢትዮጵያ ቅርሶች በአብዛኛው በእንግሊዝ፣ በጀርመንና በጣልያን አገር ነው የሚገኙት።

መቅደላ ወይም በአሁኑ ስሙ አምባ ማርያም የሚባለው አምባ፣ ወሎ ውስጥ የሚገኝ በአጼ ቴወድሮስ ዘመን ለዋና ከተማነት ታጭቶ በመካከሉ በእንግሊዞች ጦርነት ወቅት የተቃጠለ ከተማ ነው።

የእንግሊዝ ጦር ውድ ብራናዎችን፣አክሊሎችን፣መስቀሎችን፣የወርቅ ዋንጫዎችን፣የንጉሳዊያንና የቤተ ክርስትያን ቁሳቁሶችን ጋሻና የመሳሰሉትን ቅርሶችን በመዝረፈ ፲፭ ዝሆኖችንና ፪፻ በቅሎዎችን ለማጓጓዣነት ተጠቅመው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ወሰዱ።

በጣም ይገርማል! እግዚአብሔር የሰጠንን የራሳችንን ንብረት በብድር መልክ ሊሰጡን ነው። ለመሆኑ ይህን ኢትዮጵያ የተረሳችበትን ቀውጥ ጊዜ ለምን መረጡ? ዓብያተክርስቲያናት በሚቃጠሉበትና በሚዘረፉበት ዘመን? ይህ ንብረት የመንግስት ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርስና ንብረት ስለሆነ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተክርስቲያንን ነው፤ ለምንድን ነው መንግስት ወይም የባሕል ሚንስቴር እዚህ ላይ እጁን የሚያስገባው? ምን ዓይነት ተንኮል ታስቦ ይሆን?

ወይስ ያለፈውን እና መጪውን “ቴዎድሮስን” ፈርተው ይሆን? የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ በዊንድሶር ቤተመንግሥት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው የተቀበረው። ከሁለት ሣምንታት በፊት የስሴክስ ልዑልን የወለደችው የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ አዲስ ደም፡ ልዕልት ሜጋን ሜርክል ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቷን የፈጸመችው የልዑል አለማየሁ አጽም በሚገኝበት በዚሁ በውንድሶር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው።

ባለፈው ሣምንት ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያለባት የብሪታኒያ ንግሥት ኤልሳቤጥ የልዑል አለማየሁን አጽም ለኢትዮጵያ አልመልስም ብላ ነበር። ይገርማል! እዚህ ያንብቡ

ለማንኛውም ቅዱስ ታቦታቱን ይመለሱልን እና ሕዝባችንን አደንዝዞና አሥሮ ያለውን እርኩስ መንፈስ ካገራችን ያጥፉልን! እነርሱ ለክፋት አስበውት ሊሆን ይችላል እግዚአብሔር ግን ለበጎ ያደርገዋል

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን!

__________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: