ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በ ድሬዳዋ እና “አዳማ” በተባለችው ናዝሬት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 18, 2019
[ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ ፰፥፯]
“ነፍስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፍስንም ያጭዳሉ፤ አገዳ የለውም፥ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም እንግዶች ይበሉታል።“
ከጥቂት ሰዓታት በፊት በአዲስ አበባዋ እግዚአብሔርአብ ቤተክርስቲያን ስለተካሄደው የሰርግ ሥነ–ሥርዓት ቪዲዮ አቅርቤ ነበር። አሁን ድሬዳዋንና በክህደት አዳማ የተባለቸውን ናዝሬትን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እንዳናወጣቸው ዜናው ደረሰኝ። የሚገርም ነው! ንፋስ፣ በተልይ አውሎ ንፋስ ቀላል ነገር አይደለም። እግዚአብሔር አምላክ እያናገረን ነው፣ ምልክቱን እያሳየን ነው፣ ይህ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው።
ድሬዳዋ ሰኞ፡ ጥር ፲፫ / ፪ሺ፲፩ ዓ.ም / እግዚአብሔርአብ
ሰኞ የእግዚአብሔርአብ ታቦት ገብቶ ሲመለስ ፖሊስ መሬት በሚባል አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የጀመረው የድሬዳዋ ውጥረት ዛሬም ቀጥሏል።
አርብ ዕለት ከማለዳ ጀምሮ ወጣቶች ሰልፍ ሲያካሄዱ፣ የተቃሞው ድምጾችን ሲያሰሙ፣ አልፎ አልፎም ድንጋይ ሲወራወሩ ነበር።
የወጣቶች ጥያቄ እየሰፋ መጥቶ የሥራ አጥነት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄዎች ጎልተው መውጣት ጀምረዋል። በተለይም የድሬዳዋን ፍቅር አታደፍርሱ፣ በብሔር አትከፋፍሉን፣ «40/40/20» የተሰኘው የአስተዳደር ቀመር ይውደም፣ የሚሉ ተቃውሞዎች ሲሰሙ ነበር።
ረፋድ ላይ ድሬዳዋ ራስ ሼል አካባቢ «ከንቲባው ይውረድ!ድምጻችን ይሰማ!» የሚሉ ድምጾችም ከፍ ብለው ይሰሙ ነበር። በዚያ ያልፉ የነበሩ ሦስት መቶ የሚገመቱ ወጣቶች ባንዲራዎችን ከመያዝ ውጭ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ያቀርቡ ነበር።
[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩፥፳፭፡፳፯]
“በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።”
Leave a Reply