መለስ ዜናዊ ፊት አበበ ገላው የተባለ ሰው እንደጮኸ ዜናውን በጊዜው እንደሰማሁ ቪዲዮውን ማየት እንኳን አላስፈለገኝም – ያየሁት ገና ባለፈው ወር ላይ ነው፣ ኢሳት ቴሌቪዥንንም አልፎ አልፎ ማየት የጀመርኩት እንዲሁ ገና ባለፈው ወር ላይ ነው – ለዚህ ምክኒያቱ አበበ ገላውና ኢሳት የሲ.አይ. ኤ ምልምሎች፣ በባለ ኃብቱ ጆርጅ ሶሮስ ዓይነት አገራት–አፍራሾች የሚደገፉ መሆናቸውን የሚነግረኝ ነገር ስለነበረ ነው። አሁን ሁሉንም አንድ ባንድ እያየን ነው።
እብዱ አበበ ገላው፡ ልክ እንድ አጋሮቹ እንደነ ዶ/ር አብዮት የተዋሕዶ ኢትዮጵያ ማዕከል በሆነችው በትግራይ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳለው ይህ ቪዲዮ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች የተሳተፈባቸው ሌሎች ቪዲዮዎች ያሳዩናል። እብዱ ገላው መለስ ዜናዊ ፊት ሲለፈልፍ ብዙ ጥፋቶች ያጠፋውን ፖለቲከኛ መለስን ሳይሆን እና አባቶቹ ከተዋሕዶ የሆኑትን ትግራይ ኢትዮጵያዊውን መለስን ለማዋረድ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር መለስን እና አቡነ ጳውሎስን ያስገደላቸው ፕሬዚደንት ኦባማ፣ ሼክ አላሙዲንና የግብጹ ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ቡድን ነው በማለት በተደጋጋሚ አውስቼ ነበር። አሁን የቡድኑ ተዋናዮች ቀስበቅስ እየተሰባሰቡ ማንነታቸውን እንዲያሳዩን እየተደረገ ነው። ኢንጂነር ስመኘውን የገደለው ቡድን እነ መለስ ዜናዊንም አስገድሏል።
ፀረ–ኢትዮጵያ፣ ፀረ–ተዋሕዶ የሆነው የእነ ኦቦ አብዮት አህመድ + ኦቦ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ + ኦቦ ሰመኦን በረከት + ኦቦ ለማ መገርሳ + ኦቦ አበበ ገላው + ኦቦ ሲሳይ አጌና ቡድን።
እንዴት? ተከታዩን በሚቀጥለው አጋጣሚ አቀርበዋለሁ
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፳፮]
“እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።”