የኢየሩሳሌሙ መስጊድ የመሬት መናወጥ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 16, 2019
በኢየሩሳሌም የንጉሥ ሰለሞን ቤተመቅደስ የነበረበት ቦታ ላይ የተገነባው የአል–አክሳ መስጊድ እንደገና መፍረስ ይኖርበታል። ጌታችን ኢየሱስ በተሰቀለ ልክ ከ፩ሺ ዓመታት በኋላ፡ እ.አ.አ በ1033 ዓ.ም ላይ ይህ መስጊድ በመሬት መናወጥ ሙሉ በሙሉ ፈራርሶ ነበር። ፪ኛ ሺው የሚሞላው ከአስራ አምስት ዓመታት በኋላ ነው፤ በ2033 ዓ.ም። 33 = የ 66 ግማሽ።
የሚገርም ነው በዚህ የኢየሩሳሌም መስጊድ እና በመካ ጥቁር ድንጋይ መካከል ያለው ርቅት በትክክል 666 የባሕር ጉዞ ማይሎች ነው።
ታዲያ ይህ የክርስቶስ ተቃውሚዎቹ ያላግባብ የሠሩት መስጊድ በዚህ ዓ.ም ተመልሶ ይፈራርስና የእስልምና መቅሰፍት ከምድራችን ዕልም ብሎ ይጠፋ ይሆን? ፈጠነም ዘገየም ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ ጠላቱን እያንቀጠቀጠ የዲያብሎስ ሥራዎች የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንደሚያጠፋልን ምንም አያጠራጥርም። ግዜው ተቃርቧል!
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፰፥፪፡፬]
“እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ።”
Leave a Reply