Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2019
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ኢትዮጵያ በሕዝብ ተፈናቃዮች ቁጥር ፩ኛ ሆነች | ኢትዮጵያን ኢትዮጵያውያን ባልሆኑት የመተካት ትልቅ ሤራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2019

አዎ! እንደተለመደው ጅራፉን ቀድመው የሚያጮሁት ምዕራባውያኑ እና “ያል”ተባበሩት መንግሥታት፣ እንዲሁም የአውሮፓው ህብረት ወኪሎቻቸው ናቸው። በተለይ የእንግሊዝ ጋዜጦች ከዚህ በፊት ብዙ ዝናን ያተረፉበትንና ኢትዮጵያን የተመለከት መጥፎ ዜና፤ ድርቅ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ ጦርነት አሁን እንደገና አጉልተው ለማሰማት በመሞከር ላይ ናቸው።

ዘ ኢኮኖሚስት ትናትና ላወጣው ጽሑፍ የሚከተለውን ተንኮለኛ ርዕስ ስጥቶታል

After Drought, Famine and War, Ethnic Conflict Now Plagues Ethiopia The Country’s Shift Away From Autocracy is Proving Painful

ከድርቅ፣ ረሀብና ጦርነት በኋላ አሁን የዘር ግጭት ኢትዮጵያን ረብሿል የሀገሪቷ ከአምባገነንነት አገዛዝ መቀየር ህመምን አስከትሏል”

ዘ ጋርዲያን ዛሬ ባወጣው ጽሑፉ ደግሞ የሚከተለውን ርዕስ እናነባለን

Go and We Die, Stay and We Starve’: The Ethiopians Facing A Deadly Dilemma. In the rarely visited town of Gedeb, fears is rife over state plans to return 150,000 people to areas they fled because of ethnic violence

«ከሄድን እንሞታለን ፥ ከቆየን እንራባለን» በጎሳ ግጭት ሳቢያ ኢትዮጵያውያን ለሞት የሚዳርግ ከፍተኛ ችግር ገጥሟቸዋል

የተባበሩት መንግስታት ደግሞ የሚከተለውን መግለጫ ዛሬ አውጥቷል

UNHCR Says Some 196,300 Refugee Students Enrolled in Ethiopia

በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) 196 300 የጎረቤት ሃገራት ስደተኛ ተማሪዎች በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ተመዘገቡ”

ታዲያ ይህ የሕዝብ መተካት ዘመቻ በአገራችን እየተጧጧፈ እንደመጣ አይጠቁመንምን? አይናችን እያየ!

ባለፈው መስከረም ላይ ኢትዮጵያ ለስደተኞች የትምህርት፣ ስልጠና እና የስራ እድሎችን እንደምትሰጥ እንዲሁም አፍሪቃውያን ያለቪዛ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ማድረጓን እነ ዶ/ር አብዮት አስታውቀው ነበር። ሶርያውያን እና የመናውያን ወራሪ ስደተኞችም ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ ናቸው። በቅርቡ ደግሞ በሰሜን ሱዳን “ዳግማዊ መህዲ” የቱርክ ወኪል ሥልጣን ላይ ሲወጣ ሱዳኖችም ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንዲጎርፉ ይደረጋሉ።

ይህ ሁሉ አሳዛኝ ድራማ ምንን ያመለክተናል? እንግዲህ በአገራችን፡ በተለይ በዋቄዮ አላህ ልጆች ሆን ተብሎ የሚፈጠረው የውስጥ ግጭት ለስደተኞች መበራከት አስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህም ዛሬ ኢትዮጵያ በውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር በዓለም የመጀመሪያውን ቦታ ይዛለች፤ እነ ሶሪያን፣ ኢራቅን፣ አፍጋኒስታንን፣ ሶማሊያን እና የመንን በልጣ። በሌላ በኩል ግን ለጎረቤት ሃገራት ስደተኞች የሥራ እና ትምህርት ዕድል ትሰጣለች። ሁለቱ እንዴት ይጣጣማል?!

ወገኖቼ፤ በአገራችን ከፍተኛ ፀረኢትዮጵያ እና ፀረኢትዮጵያውያን ሤራ በመካሄድ ላይ ነው፤ ዋናው አላማቸው አጥባቂ ኢትዮጵያውያን በሆኑት የተዋሕዶ ልጆች ላይ ነው። የዘር መተካት ዘመቻ እየተካሄድ እንደሆነና ለዚህም በተለይ የዋቄዮ አላህ ጣዖት አምላኪዎች እንደ መሣሪያ ለመጠቀም መምረጣቸውን በደንብ መገንዘብ አለብን።

ወገን፡ ተነሱ እንነሳ!

__________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: