Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2019
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 8th, 2019

ልደታ ለማርያም | ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ)

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2019

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በአል በሰላም አደረሰን!

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግበማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡

ልደታበመባል በተለምዶ በማሳጠር የሚጠራው እና ወር በገባ በአንደኛው ቀን የሚከበረው የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና በሊባኖስ ተራራ በግንቦት አንድ ቀን የተወለደችበትን ቀን የሚያስታውስ ትልቅ በዓል ነው፡፡ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ ስላልነበራቸው እግዚአብሔርን በጾም እና በጸሎት በጠየቁት ወቅት የዓለሙ መድኅን የሆነውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደችውን ቅድስት ድንግል ማርያምን ስጣቸው፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉና ለክብር የማይሮጡ በመሆናቸው የሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊነት ሊታወቅ አልቻለም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2019

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ላይ ካሰማራቸው ሐዋርያት መካከል ሐዋርያው ማርቆስ አንዱ ነው

ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት

ሐዋርያው ማርቆስን በሚመለከት መሪራስ አማን በላይ “ሐዋርያው ማርቆስ ዜግነቱ ሮማያዊ ሲሆን፡ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ነው። በዚያን ጊዜ ግብጾች ቦታ አልነበራቸውም ሲሉ ተናግረዋል። ሐዋርያው ማርቆስ ቤተሰቦቹ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ነዋሪነታቸው ግብጽና ኢየሩሳሌም እንደነበረ በታሪክ ተጠቅሷል።

አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ፡ ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ አንበሳ ነው ሲሉ መጽሐፍ ጽፈዋል። ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ አንበሳ ነው የተባለው መጽሐፍ ገጽ 100 ላይ “ማርቆስ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉ ጽፈዋል። እኒህ አባት ሐዋርያው ማርቆስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐዋርያት ኢትዮጵያዊ ደም ያላቸው መሆናቸውን በማመለከት ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው መጽሐፍ ገጽ 42 ላይ፡ “ከኢትዮጵያውያን ዘር የሚወለደው ፊልጶስም ነው” ሲሉ ሁለቱ ሐዋርያት ከጌታችን ጋር ያደረጉትን የቃላት ልውውጥ በሚመለከት ጽፈዋል።

ከዚህ ላይ ማየት ያለብን እነዚህ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቀድሞ ጀምረው ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉና ለክብር የማይሮጡ በመሆናቸው ማንነታቸው ሊታወቅ አልቻለም። እንኳን ቀድሞ በቅርቡ የዳ/ዊ አጤ ቴዎድሮስን ታሪክ የፃፉት አንዱ ደራሲ መጽሐፉን የዘመኑ የታሪክ ሊቃውንቶችን ጥቅስ ለመውሰድ ሲሉ “የማይታወቀው ደራሲ” እንደጻፈው እየተባለ ነው የሚጠቀሰው። የጥንት ኢትዮጵያውያን “እወቁልን” የማይሉ በመሆናቸው ብዙ የታሪክ አባቶቻችን ስምና ታሪክ ተደብቆ ቀርቷል። በዚህ ባለንበት አገር አሉ ከሚባሉት ሊቆች መካከል ለአንዱ የሊቀ–ጠበብት ማዕረግ ዩኒቨርስቲው ሲሰጣቸው አስተዳዳሪው ለተሰብሳቢው እንግዳ እንዲህ ብለው ነበር፦

ኢትዮጵያውያን ይህን ሰርተናል የማይሉ በስራቸው እንጂ ለወረቀት የማይጓጉ በመሆናቸው ይህ ዶ/ር እገሌ እንደሌሎች ዶክተሮች ማመልከቻ ይዞ ወደ ጽሕፈት ቤቱ መጥቶ አስቸግሮኝ አያውቅም። የስራውን ጥራትና ብቃት ዩኒቨርስቲው በማየቱ የሌቀ–ጠበብት ማዕረግ ሰጥቶታል” ብለዋል።

ትቤ አክሱም ገጽ 67 “ቅዱስ ማርቆስም ያባቱን ሀገር አስቀድሞም ያውቀው ስለነበረ መጥቶ እንዳስተማረ” ሲሉ ጽፈዋል። ከዚህ ላይ የኢትዮጵያውያን ከቀድሞ ጀምሮ የመጣው ታሪክ የሚያመለክተው ለክርስትና ሃይማኖት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ነው። ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት። ላይ እንደተጠቀሰው ዛሬ ድረስ በህይወት ያሉ ደራሲያን ኮሎኔልነታቸውን፣ ጠበብትነታቸውን ወይም ሊቅነታቸውን ሳይጠቅሱ መጽሐፍ የጻፉ ደራሲያን ነበሩ። ምክኒያቱም ኢትዮጵያውያን አብዛኛው እወቁኝ የማይሉ ናቸው። በዚህ ምክንያት ከቀድሞ ጀምሮ ተያይዞ በመምጣቱ ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ሳይታወቅ ኖሮ ነበር።

መሪራስ አማን በላይ፡ “ጉግሣ” መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 3 መጋቢት 1993 .. ገጽ 17 ላይ “የማርቆስን አክስት ማለት የበርናባስንና የአርስጦሎስን እህት ጴጥሮስን አግብቶ ነበር። እንዲሁሙ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የቤተ እስራኤል የሌዊና የይሑዳ ነገድ የሆነ ወደ ቀሬና ቀራኒዮ ወደ ቤተ መቅደስ ሊሰግድ መጥቶ ስሙም ስምዖን ይባል ነበር። በበነጋታው ከአባቱና ከናቱ ዘመድ ከስምዖን ጋር ማርቆስ የጌታችንን የክርስቶስን ግርፋትና ሕማማቱን እየተከተለ ተምልክቷል። አጎቱንም የአባቱን ዘመድ ኢትዮጵያዊ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው የጌታን መስቀል እንዲሸከም አይሁዳ ሊያስገድዱት አይቷል ተመልክቷል” ሲሉ ጽፈዋል። ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ጥቁር መሆኑን በሌሎችም ታሪክ ታውቋል።

ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነና ታሪኩን ስላወቁ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ አጽሙ አጽሙ ቬነስ ግዛት / ከተማ ከሚቀር ግብጽ መግባት ይኖርበታል ብለው ከቬነስ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ጋር ያደረጉት ጥረት ቀላል አይደለም። ቀደም ሲል ግብጾች ሊያስመልሱ ያልቻሉትን አጤ ኃይለ ሥላሴ በጥረታቸው የቅዱስ ሐዋርያው ማርቆስ አጽም ወደ አፍሪቃዋ ግብጽ እንዲገባ ሆነ። ይህ ታሪክ በመሆኑ ሊገለጽ የሚገባው ሲሆን፡ ጃንሆይ መሠረት ያደረጉት ዋናው ነጥብ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በዘሩ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው።

የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩንን ዋኖቻችንን እናስብ፤ ከብቶች በሚሰማሩበት ሜዳ እንደ ወይፈን በገመድ አሥረው ለጐተቱት ለማርያም ልጅ ማርቆስ ሰላምታ ይገባል፤ በእሳት ነበልባል ሊያቃጥሉት በወደዱ ጊዜ ዝናብና ውርጭ ነዲዱን አጠፉት መብረቅም በድኑን ጋረዳት።

የድንግል ማርያም ልጅ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለው የቅዱስ ማርቆስ ጸሎቱና በረከቱ በሕዝበ ክርስቲያንና በሀገራችን በኢትዮጵያ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፡ አሜን!

እንኳን አደረሰን!!!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

የ፬ ልጆች እናቷ ክርስቲያን እህታችን ፓኪስታንን ለቅቃ ወደ ካናዳ አመራች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2019

እናትዬ እንኳን ከጅቦች መንጋጋ ነፃ ወጣሽ፤ ጀግና ክርስቲያን ማለት አንቺ ነሽ።

የጅጅጋ፣ የጅማ፣ የቡራዮ፣ የለገጣፎ፣ የከሜሴ፣ የሱልልታ እናቶችም እንዲሁ ከዋቄዮ አላህ ጅቦች መንጋጋ በቅርቡ ነፃ ይወጣሉ፣ እግዚአብሔር አምላክ በጠላቱ ላይ እሳት ያወርድበታል!!!

ታያላችሁ፤ በሃገራችን ክርስቲያኖች ያለማቋረጥ ሲታረዱና ዓብያተክርስቲያናቱ ሲቃጠሉ የዓለም መንግስታትና ሜዲያቸው ፀጥ ብለዋል፤ ምክኒያቱም ከራሳቸው የሆኑት ሥልጣን ላይ ናቸው ስለዚህ መዋረድ የለባቸውምና ነው። የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ግን ዝም አይልም!

ከስድስት ወር በፊት የቀረበ ቪዲዮ፦

የዚህች ምስኪን ክርስቲያን እህታችንን አስገራሚ ታሪክ ትምህርት ይሁነን።

አስያ ቢቢ ትባላለች፡ ከ 8 ዓመታት በፊት ከሙስሊም ጎረቤቶቿ ጋር የመጠጥ ውሃ ለመቅዳት ወደ አንድ ኩሬ ወረደች፤ እዚያም ክርስቲያኗ አስያ ቢቢ ለሙስሊሟ ውሃ ስታቀብላት፤ ሙስሊሟ “ክክርስቲያን እጅ ያገኘሁትን ውሃ አልጠጣም፡ ኩፋሯ በክርስቲያ እጅ አደፍርሰዋለች” በማለት ሙስሊም ጓደኞቿን ሰብስባ ትጮኽባታላች፤ ከዚያም ጉዳዩ ለፖሊስ ይቀርብና የአራት ልጆች እናቷ ክርስቲያኗ አስያ ቢቢ ትታሠራለች። ክርስቲያን በመሆኗ እና የእስልምናን አምላክ ባለመቀበሏ ለ8 ዓመታት ያህል ብርሃንን ሳታይ ታፍና በቆየችበት እስር ቤትም የሞት ፍርድ ይሰጣታል፤ አሁን ከ8 ዓመታት በኋላ፡ በአንዳንድ የክርስቲያኑ ዓለም የሰባዕዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦች ግፊት የፓኪስታን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ፍርዱ እንዲሻርላትና እንድትፈታም ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ታዲያ አሁን የዚህችን ጀግና ክርስቲያን መፈታት ዜና ፓኪስታናውያን መንገድ ላይ ወጥተው ደስታቸውን በመግለጽ ፋንታ፤ አሁን ሙስሊሞቹ “ክርስቲያኑ አስያ ቢቢ ትገደል፡ የለቀቋት ዳኞችም ይገደሉ!“ በማለት በፓኪስታን ከተሞች አደባባዮችና መንገዶች ላይ የተለመደውን ረብሻና ብጥብጥ በመፍጠር ላይ ናቸው።

ዓለም የእኛ፣ የእኛና የእኛ ብቻ ነች!” የሚሉት እነዚህ አረመኔዎች የእስልምና ውጤት ናቸው፤ የእስልምና አምላክ እና ነብይ ምሕረት የሚባል ነገር አያውቁምይሰቀል! ይገደል! ብቻ እንጂ።

ዓለማችንን ከእነዚህ አስቀያሚ የዲያብሎስ ልጆች ጋር መጋራታችን የሚያሳዝን ነው! ወስላታው የም ዕራቡ ዓለም እንደ እስያ ቢቢ ለመሳሰሉት ተበዳይ ክርስቲያኖች ጥገኝነት እንደመስጠት በብዙ ሚሊየን ለሚቆጠሩ በዳይ መሀመዳውያን በሩን ከፍተውላቸዋል። ግብዝ ዓለም!

________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በጅማ አካባቢ የተዋሕዶ ልጆች እየታረዱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2019

___________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: