Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2019
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 6th, 2019

ቡልጋሪያ | ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የካቶሊኩን ጳጳስ ፍራንሲስኮን አላስተናግድም አለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 6, 2019

በራሳቸው በካቶሊኮች ዘንድ የተጠላውና መናፍቅ የሆነው የቫቲካን ጳጳስ ፍራንሲስኮ ከቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ለመገናኘት እሁድ ዕለት ወደ ቡልጋሪያ በመጓዝ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ጋር የጋራ የጸሎት አገልግሎት የማክበር ተስፋ ነበረው። ነገር ግን የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ አባቶች ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ጸሎት ለማድረግ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጠዋል።

የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት በዛሬው ዕለት በሶፊያ ከተማ ከጳጳሱ “ለሰላም ፀሎት” ማድረጊያ ሥነ ሥርዓት ጋር እንዲቀላቀሉ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል፤ በተለይ በዚህ “የሰላም ጸሎት” ላይ የሙስሊም መሪዎች መካፈላቸውን የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶችን አላስደሰታቸውም።

የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት በፀረክርስቶሷ ኦቶማን ቱርክ እና በኮሙኒዝም ጭቆና ቀንበር ብዙ ፈተናን ያየች ቤተክርስቲያን ናት።

ከሦስት ዓመታት በፊትም ጳጳስ ፍራንሲስኮ በኦርቶዶክስ ጆርጂያ ተመሳሳይ ዕጣ ደርሶት ነበር።

የቡልጋሪያ አባቶች ውሳኔ ትክክለኛ ነው። ይህ ግራ የተጋባ ጳጳስ አንድ የዓለም ሃይማኖት (በቫቲካን መሪነት) ለመመሥረት በመጣደፍ ላይ ነው፤ ለዚህም ነው መሀመዳውያኑ በማስጠጋት ላይ ያለው፣ ለዚህም ነው በሚሊየን የሚቆጠሩ መሀመዳውያን “ስደተኞች” አውሮፓን እና አሜሪካን እንዲያጥልቀልቁ ድጋፉን የሚሰጠው። ወደ ቡልጋሪያም የሄደው ያው ቡልጋሪያ በሯን ለሙስሊም ስደተኞች እንድትከፍት ለመገፋፋት ነው።

ለሰላም ፀሎት” በሚል ሰበብ በአገራችንም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በአንድ ላይ ሲሰባሰቡ እያየን ነው፤ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፤ ከሰይጣን ጋር ሆኖ ለሰላም ፀሎት ማድረግ አይቻልም፤ ቅጥፈት ነው! እራስን ማታለል ነው!

ሰሞኑን አንዳንድ አስገራሚ ነገሮችን እያየን ነው፤ ለምሳሌ የበዓል ወቅትን ወይም ልዩ መርሃ ግብሮችን በመጠቀም እንደ እነ መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ የመሳሰሉትን ታዋቂ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችከሙስሊም ኡስታዞችና ሸሆች ጋር መድረክ ላይ ወይም ስቱዲዮ ውስጥ በአንድ ላይ እንዲገናኙና በአገራችን ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ መልዕክት እንዲያስተላልፉ እየተደረገ ነው፤ ከጀርባው ትልቅ ተንኮል አለ፤ “ሁሉም ሃይማኖቶች አንድ ናቸው፣ አንድ ነን፣ በሉሲፈር መሪነት ዓለም አቀፋዊ የሆነ አንድ ሃይማኖት መመሥረት አለብን” የሚል አጀንዳ ያለው ነው።

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፬]

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: