Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2019
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 4th, 2019

የምዕራብ ሉሲፈራውያን “ኢትዮጵያን”፣ ሰዶማውያን “ባንዲራዋን”፣ ሙስሊሞች ደግሞ “ክቡር መስቀሏን” ሊሠርቁ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 4, 2019

አዎ! እየተካሄደ ያለው ይህ ነው፤ ከታሪክ መማር ካልቻልክ ስተቶችን ከመደጋገም አትቆጠብምና ሞኞቹ ኢትዮጵያውያን በውጭ ጠላቶቻቸው በመታለል የራሳቸው ጠላቶች በመሆን ላይ ናቸው።

ቀደም ሲል፡ ሱዳኖች የተባሉት ኢትዮጵያውያን “የሱዳን አረቦች ነን ኢትዮጵያውያን አይደለንም” አሉ፤ ከዚያ የጂቡቲ ኢትዮጵያውያን “ጂቡቲያውያን ነን ኢትዮጵያውያን አይደለንም” አሉ፣ ቀጥለውም ሰሜን ኢትዮጵያውያን “እኛ ኤርትራውያን ነን ኢትዮጵያውያን አይደለንም” አሉ፣ ብዙም አልቆየም ደቡብ ኢትዮጵያውያን፤ “የለም እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ኦሮሞዎች ነን” አሉ፣ ዛሬ ደግሞ “ትግሬ እና አማራ” የተባሉት “አይ እኛ በቅድሚያ ትግሬዎች እና አማራዎች ነን” በማለት ላይ ናቸው።

እንግዲህ እነዚህ ኢትዮጵያውያን የጠላትን ተንኮል ባለመረዳትና ከጠላት ጋር፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ በማበር “ኢትዮጵያን” ከማንንነታቸው ላይ ለመፋቅ በፈቃዳቸው ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። እራስን ለማጥፋት!

ሰሞኑን “አማራ” በተባሉት ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት ሆን ተብሎ፣ ሰው ሠራሽ በሆነ መንገድ በመንደርተኛ ብሔር ግንባታ ላይ በተናጠል ትኩረት እንዲያደርጉ ለመገፋፋት ነው፤ ልክ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ ወዘተ እንደተባሉት፡ ከኢትዮጵያዊነታቸው በፊት መንደርተኛነታቸውን ያስቀድማሉ ማለት ነው። “ዕንቁላል ወይስ ዶሮ?” የሚለውን የተለመደ ዕንቆቅልህ ምን አውቅልህ ጨዋታ ይመስል”።

የዚህ ሁሉ ዲያብሎሳዊ አጀንዳ አላማም የእኔ የሚሉትን አዲስ ማንነትን እንዲይዙ እና “ኢትዮጵያን” እንዲረሱ፣ አማርኛ ቋንቋን ከብሔራዊ ቋንቋነት ለማስወገድ፣ የኢትዮጵያን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ለማስተው፤ በመጨረሻም፡ ዋናው ግባቸው ነው፤ የተዋሕዶ ክርስትናን ለማጥፋት ነው።

በቀጥተኛነታቸውና በግልጽነታቸው የማደንቃቸው ኢንጂነር ይልቃል እንኳን ባንድ ወቅት “አማራ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለቱ አስጠቅቶታል” ብለው ነበር።

አይ! ይህማ አይሆንም፤ “ኢትዮጵያዊነታችንንማ በፍጹም አንተውም” ልትሉ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አይምሰላችሁ፤ በዚህ ከቀጠለ፤ በዛሬው ውጥቅንቅጥ ሥርዓት እያደጉ ያሉት ሕፃናት በሚቀጥሉት ሃያ አመታት ውስጥ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው በመተው ዲያብሎስ የፈጠረላቸውን አዲስ ማንነት ይቀበላሉ። ለዚህም የእነ ዶ/ር አብዮት አህመድን ፀረኢትዮጵያ አጀንዳ አራማጆች እና እየተሠራ ያለውን ፀረኢትዮጵያ ሤራ ማየት የተሳናቸው እውሮች ከተጠያቂነት አያመልጡም። ኢትዮጵያን በመተው ባንዲራዋን እና መስቀሏን ያልተሸከም ሁሉ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደሚወድቅ፡ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኤርትራ ምስክሮች ናቸው።

__________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: