Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • May 2019
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for May 2nd, 2019

ልክ በሎጥ ዘመን እንደሆነው ዛሬም ክርስቲያኖች በሰዶማውያኑ ጋኔን ተከብበዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2019

ሰዶምና ገሞራ አመድ እስኪሆኑ ድረስ በአማላካችን ፍርድ የተቃጠሉት ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ነበር፤ አዎ! ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት። ግን የሰው ልጅ ዛሬም አልተማረም፤ አሁንም የሚታያው ያው “ተመሳሳይ ነገር ነው፤ ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም። በእኛ ዘመን ሰዶምን እና ገሞራን እንደገና ማየት መቻላችን ማመን ያቅታል።

በሰዶማውያኑ እና በሙስሊሞች መካከል የሚንቀሳቀስወ ጋኔን አንድ ዓይነት መሆኑን ይህ ማስረጃ ነው። ይህን ያህል ጠበኝነትና ግልፍተኝነት ከዲያብሎስ ብቻ ነው የሚመጣው። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ! የ “ለዘብተኛ/ሊበራል ዲሞክራሲ እና የእስላም ርዕዮተ ዓለማት ፍሬ ይህ ነው። ከዚህ የበለጠ ግልጽ ማስረጃ የለም።

ሁለቱ ገዳይ ቡድኖች ለክርስቶስ እና ተከታዮቹ ያላቸው ጥላቻ ብዙዎቻችን ከምንገምተው በላይ ነው፤ ቪዲዮው ላይ የሚታየው ድርጊት እንዲያውም ቀላሉ ነገር ነው፤ በየጎረቤቱ ተደብቀው የሚፈጽሙት ጥቃት እና ወንጀል እጅግ በጣም የሚሰቀጥጥ ነው፤ ቴክኖሎጂን እየተጠቀሙ ምንም ባላደረጓቸው ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ፣ ጨረር አፍላቂ መሳሪዎችን (ሌዘር፣ ማይክሮዌቭ ወዘተ) ይጠቀማሉ፤ አዎ! እስላም በብረት ጎራዴ፥ ሰዶማውያን ደግሞ በጨረር ጎራዴ።

ዓለምን ሲያውኩት ያጋንንት ሥራቸው እንዳይተርፈን ለእኛ የእነርሱ ግብራቸው፡ ገብርኤል በሰይፉ ቀጥቅጦ ይጣላቸው!!!

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፱]

ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት።

ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት። በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።

እነርሱም። ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ። ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ።

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፫]

የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፥ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ክፉ ነገርን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!

[፪ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፪]

ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

“ናግራን” ሳውዲ አረቢያ በአንበጣ መንጋ ተወረረች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2019

ሰማዕታተ ናግራን

ከኢትዮጵያ (ኤርትራ + ሱዳን) አካባቢ የተነሳው የአንበጣ መንጋ በሳውዲ እና የመን መዋሰኛ የምትገኘውን የናግራን ከተማ ወርሯል። በ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ (የአክሱም) መንግሥት

ቀይ ባሕርን ተሻግሮ እስከ ደቡብ ዓረብ (የመን) ድረስ ግዛቱን አስፍቶ እንደነበር የሚታወቅ ነው። ከ495-525 .. የነገሠው የሀገራችን ንጉሥ አጼ ካሌብ በየመን (ናግራን/Najran) አካባቢ የሚገኙ ክርስቲያኖች፡ ድሁ ንዋስ (ፊንሐስ) በተባለ አይሁዳዊ ከደረሰባቸው ጥቃት ለመከላከል መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት በ፷ መርከቦች አዝምቶ ከጥቃት ታድጓቸዋል።

ለሰማዕታቱም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያነት ታሪክ በዐረቢያ ምድር የመጀመሪያው ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ከ1400 ዓመታት በፊት በዚሁ በናግራን ታንጾ ነበር፤ ይህም የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር። ነገር ግን እርኩሱ መሀመድ (በገሃነም እሳት ይቃጠል) 622 .ም ጀምሮ በዲያብሎሳዊው ጂሃዱ እና “ሁለት ሃይማኖቶች በአረቢያ ጎን ለጎን መኖር የለባቸውም” በሚል መርሆው እዚያ የነበሩትን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን (ደካማ በነበረበት ዘመን መጠለያ ሰጥተውት የነበሩትን) በመጨፍጨፍ ቤተክርስቲያናቸውን አፈራርሶባቸዋል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዛሬ ሳውዲ አረቢያ ተብሎ በሚጠራው ሃገር በምትገኘዋ በናግራን ከተማ ክርስቲያኖች አይኖሩም።

የመጀመሪያ ማሰንቀቂያ የሆነው ይህ የአንበጣ መንጋ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ አረብ ኤሚራቶች፣ ኢራን እና ግብጽ ያመራል። እኛ ዝም ብንል የሰማዕታት ደም ዝም አይልም፤ ይጮኻል፣ ይጣራልፈስሶ አይቀርምሊቢያና የመን ውጥንቅጣቸው እየወጣ እንደሆነ እያየን ነው፣ ግብጽና ሳውዲም አንበጣ ብቻ ሳይሆን ገና እሳት ይወርድባቸዋል።

[ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፲፡፬፥፭]

አንበጣዎች

ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤ የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፥ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: