Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 26th, 2019

ድንቅ ተዓምር በጠፈር | ዝነኛው ቴሌስኮፕ በ፴፩ ሚሊየን የብርሃን ዓመት እርቀት ላይ ክቡር መስቀሉን አገኘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2019

የአሜሪካ የህዋ ምርምር ተቋም፡ ናሳ/ NASAንብረት የሆነው ሃብል ቴሌስኮፕ/ Hubble Telescope በ፴፩ ሚሊየን የብርሃን አመት እርቀት ላይ እኛ ከዚህ ሆነን ማየት የማንችለውን ነገር በጥለቂ ጋላክሲ ለማየት ችሏል። ይህ በጣም አስገራሚ የሆነ ነገር የተከሰተበት ቦታ በጣም ከመራቁ የተነሳ ርቀቱ በእኛ ኪሎሜትር አይለካሙ፤ በብርሃን ፍጥነት እንጅ፤ ስለዚህ የብርሃን ዓመት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። 1 ብርሃን ዓመት = 10 ትሪሊየን ኪሎሜትር – ወይንም 10 ሚሊየን ሚሊየን ኪሎሜትር።

ምድር ላይ፤ በቅርቡ ስፔን ላይ ከሃዘን ጋር እንዳየነው፤ መቶ ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የነበረውን ሕፃን ለሁለት ሳምንታት ያህል ቆፍረው ማውጣት አልቻሉም፤ ግን ወደ ሌላ ዓለማት ርቀው በመሄድ ብዙ ሲደክሙ ይታያሉ፤ ምን እንደሚፈልጉ እንኳን የሚያውቁት አይመስለኝም።

ተመልከቱ! አምላካችን ኢየሱስ ግን በሁሉም ቦታ መኖሩን ያሳያቸዋል፤ እኔ ነኝ ጸጋው፣ ምሕረቱ፣ ሰላሙ ፣ እውነቱ፣ ቸርነቱ፣ ፍቅሩ በማለት ምድር ላይ የሰጠንን ክቡር መስቀሉን ከሁሉም ዓለሞች ሆኖ ያሳያቸዋል። አሁንስ ምን ይሉ ይሆን? ይህ ተዓምር በተለይ በፋሲካ ዋዜማ መታየቱ አይስገርማቸውምን? ለማመን በግትርነት ሌላ ምልክት ማየቱን ይሹ ይሆን?

ያዘን እናት የንባ ባሕር

ቁማ ነበር እመስቀል ሥር

ተቸንክራ በፍቅር፡፡

ቅድስት እናት ለዘላለም

በልቤ ውስጥ እንዲታተም

የልጅሽ የየሱስ ሕማም፡፡

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: