ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) – የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት
ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤
፩. ፀሐይ ጨለመ፤
፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
፫. ከዋክብት ረገፉ፤
፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩–፶፬)፡፡
ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤
፩. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)››፤
፪. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››፤
፫. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፤
፬. እመቤታችንን ‹‹ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩንም ‹‹እናትህ እነኋት›› በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
፭. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ››
፮. ‹‹ተጠማሁ››፤
፯. ‹‹ዅሉ ተፈጸመ›› (ማቴ. ፳፯፥፵፭–፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫–፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲–፴)፡፡