Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ድንቅ ተዓምር | የኢትዮጵያ ታላቅ መስቀል በፈረንሳይ እሳት ተፈትኖ አለፈ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2019

የፓሪሱ ኖትረዳም ካቴድራል ከደረሰበት የእሳት ቃጠሎ ከተረፉትና ውድ ከሆኑት ጥቂት ቅርሶች መካከል ይህ የ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስጦታ የሆነው የኢትዮጵያ መስቀል አንዱ ነው።

ቀዳማዊ ኃይለ ላሴ ከ ስልሳ አምስት ዓመታት በፊት፡ ... 1954.ም፡ ወደ ፈረንሳይ በተጓዙ ጊዜ እግረመንገዳቸውን ሰሞኑን በእሳት የወደመውን የፓሪሱን ኖትረ ዳምካቴድራል እና ቤተመቅደስ ጎብኝተው በዛውም ለፈረንሳይ አንድ ታላቅ የኢትዮጵያ መስቀል በስጦታ መልክ አበርክተው ነበር።

መስቀሉ የአለም መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ ከቃጠሎው የተረፈው የኢትዮጵያ መስቀል አሁን ወደ ታዋቂው ሉቭር ቤተ መዘክር ተወስዷል።

ፈረንሳይ ይኼን ውድና ታላቅ መስቀል በኖትረዳም ቤተ መዘክር አስቀምጣ ለ ስልሳ አምስት ዓመታት ያህልከጎብኚዎች ከፍተኛ ገቢ ታገኝበት ነበር።

ባለፈው ሳምንት ላይ የኖትረዳም ካቴድራል ከነቤተመዘክሩ ሲቃጠል መስቀሉ ግን አንዳች ጉዳት ሳያደርስበት ተገኝቷል።

ወገኖቼ፤ ጊዜው እየተቃረበ ነው። የአለም አይኖች ሁሉ ድንቅ፣ ምስጢራዊ፣ የአለም እምብርት፣ የሕይወት ዛፍ እና የገነት መገኛ ወደሆነችው ኢትዮጵያ ይማትራሉ። አለም በአውሎ ነፋስ፣ በጎርፍ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በእሳት ስትናጥ ሁሉም መዳኛና መጠጊያ ወደሆነችው ወደ ኢትዮጵያ ፊቱን ያዞራልአሁን ለጊዜው በአገራችን ሁሉም ነገር ደፍርሷል፤ ካልደፈረሰ አይጠራምና፡ ግን በቅርብ አገራችን ትጸዳለች፤ ጠላቶቿ ሁሉ አንድ ባንድ ይንበረከካሉ። የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሩቅ አይደለም!

ነጠብጣቦቹን ስናገናኝ

ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን – ላሊበላ – ፓሪስ – ኖትረዳም (የእኛ ወይዘሮ )– መስቀል – ስቅለት

በላሊበላ ካባ ለብሰው የነበሩት ማክሮንን እና አህመድ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው!

መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!

_____________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: