Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 19th, 2019

ታዋቂው ካናዳዊ የሥነ-ልቦና ፕሮፌሰር ጆርዳን ፔተርሰን | “እውነተኛው ክርስትና ኦርቶዶክስ ነው”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2019

በመላው ዓለም የሚገኙ ብዛት ያላቸው ሰዎች ስለ ኦሮቶዶክስ ክርስትና ምን ታስባለህ? ባማለት ፕሮፌሰሩን ጠይቀዋቸዋል። ሲመልሱም

ኦሮቶዶክስ ክርስቲያኖች ይወዱኛል፤ ለምን እንደሆነ አላውቅም ግን፡ እንደሚመስለኝ፡ የሆነ ግንዛቤ አለኝ፦

ብዙ ደብዳቢዎች ከብዙ ሃይማኖት መሪዎች ይደርሱኛል፤ ከአይሁዶች፣ ከክርስቲያኖች፣ ከሙስሊሞች። አብዛኛዎቹ ደብዳቤዎች ግን ከኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው።

እንደ እኔ ከሆነና እንደሚመስለኝ፤ ኦርቶዶክሶች ክርስትናን ከፕሮቴስታንቶች እና ካቶሊኮች ለየት ባለ መልክ ነው የሚያዩት።

ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ፕሮቴስታንቶችን እና ካቶሊኮችን ማጣጣሌ አይደለም፤ የራሳቸው የሆነ ምክኒያት ሊኖራቸው ይችላልና።

ነገር ግን፡ በምዕራቡ ዓለም ሰዎች ክርስትናን የሚያዩት አለማዊ የግንዛቤ ንድፈሀሳብ የሚነጸባረቅበት የእምነት እሴት እንደሆነ አድርገው ነው።

በምዕራቡ ዓለም ክርስቲያን ለመሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለኃጢአተኞች ቤዛ አድርጐ መስጠቱን ብቻ መቀበል በቂ ነው። ለምን ይህ እንደሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን በዚህ ላይ ብቻ መወሰናቸው አደጋ ያስከትላል።

ኦርቶዶክሶች ግን በዚህ ላይ ብቻ አይወሰኑም፤ ኦርቶዶክሶች “መስቀሉን ተሸክመህ እየተሰነካከልህም ቢሆን ኮረብታውን ውጣ” ብለው ያምናሉ፤ ለእነርሱ መስቀሉ የእውነታ ማዕከል ነው፤ ሁሉም ነገር መስቀሉ ላይ ነው።

ይህን ፕሮቴስታንቶችና እና ካቶሊኮችም ያምኑበታል፡ ነገር ግን ዝቅተኛ ዋጋ ነው የሚሰጡት፤ ይህን ዋጋ አለመስጠታቸው ግን በተለይ በአሁኗ ዓለም በጣም አደገኛ ነው።

ኦርቶዶክሶች፦ “ወደሚቀጥለው ሕይወት ስትሸጋገር ስቃይን፣ ሞትን እና ዳግመኛ መወለድን በእውነታ ማዕከል በሆነው በመስቀሉ ላይ ታገኘዋለህ።”ብለው ያምናሉ።

ይህን መቀበልና ማቀፍ ግድ ነው፤ ይህ ከባድ ሥራ ነው፤ ምክኒያቱም ጉድለቶችህን፣ የእውነታን ጉድለቶች፣ የህልውናን አሳዛኝ ሁኔታ፣ ሞትህን፣ የሰው ልጅን ክፉነት ሁሉ መቀበል ግድ ነውና።

እነዚህ አስገራሚ የሆኑ እና በጣም የሚጠይቁ መስፈርቶች ናቸው። ማድረግ የምትችለውን ታደርጋለህ፤ መስቀልህን ማንሳት ብቻ ሳይሆን ኮረብታውን እየተሰነካከልክ በመውጣት ወደ እግዚአብሔር ከተማ፣ መልካም ወደሆነው ትጓዛለህ።

ኦርቶዶክሶች ይህን ጥሩ አድርገው አዘጋጅተውታል፤ መድረሻ ግባቸው ይህ ነው፤ የኑሮ ትርጉማቸው ይህ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ክርስቶስን መምሰል ነው፤ ክርስቶስ አርማቸው ነው፤ ክርስትና እንደሚያስተምረው፦ አምላክ ከ ቅድመፍጥረት የነበረውን የታሪክ ድፍርስ፣ የሁኔታዎች ምስቅልቅል ወደ መኖሪያ ሥርዓት ለመለወጥ ክርስቶስን አርማው አደረገው።

እውነተኛ ንግግር ነው፤“መስቀሉን በጀርባህ ተሸክመህ እየተሰነካከልህም ቢሆን ኮረብታውን ውጣ”፤ ይህ በጣም ወጥ የሆነ ጽንሰሐሳብ ነው።

ኦርቶዶክሶች ይህን ጽንሰሐሳብ ፊት ለፊት በማውጣት የእምነታቸው ዋና መሠረት እንዲሆን አድርገው በመጠበቃቸው በጣም ጥሩ ሥራ ሠርተዋል

ስለ ኦሮቶዶክስ ክርስትና ያለኝ ሃሳብ ይህ ነው!

ዋው!

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Psychology | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዶ/ር አብዮት ቸርች ጣራ ተደርምሶ ፲፫ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2019

በደቡብ አፍሪቃዋ ክዋዙሉ ናታል ለ ፈረንጆቹ የስቅለት ዕለት አንድ የጴንጤ ቸርች ውስጥ ከነበሩት ሰዎች መካከል አሥራ ሦስቱ ሲሞቱ ሌሎች ክፉኛ ቆስለዋል። የቸርቹን ጣራ ያልተጠበቀ ኃይለኛ ዝናብ ነበር የደረመሰው። ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

ዘመነ ዶ/ር አብዮት | የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደ ጴንጤ ቸርች ተለወጠ”

የሚለው ቪዲዮ ካሳየን ሁኔታ ጋር የሚያገናኘው ነገር ይኖራል፤ አውሮፕላኑ ከ ኪንሻሳ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረው አውሮፕላን ውስጥ የሆነ መንፈስ ይታያል ታዲያ ይህ መንፈስ በእዚህ የደቡብ አፍሪቃ ቸርች ላይ ከዝናብ ጋር ወርዶ ይሆን? KwaZulu-Natal – Kinishasa (KK)

_____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: