ተዓምር በፓሪስ | በተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስ ታየ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2019
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ብዙ ሰዎች እየመሰከሩ ነው። ድንቅ ነው። የዛሬዎቹ ከሃዲ ፈረንሳይ አባቶች ይህን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ክብር ሲሉ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በስንት ድካምና መስዋዕት ሠሩት። የአሁኑ ተልካሻ ትውልድ ግን ከአውሬነት ነፃ አውጥቶ እየባረከ ፀጋውን የሰጣቸውን ጌታችንን በመተው እንደ ይሁዳ የክህደት ኑሮውን መረጡ። በዚህም ይህን ድንቅ ቤተክርስቲያን ለፀሎት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እና ለነፍስ ማደሻ በመገልገል ፈንታ ጎብኝዎችን በመጋበዝ የገንዘብ ማምረቻ መሣሪያ አደረጉት።
አዎ! ጌታችን በዚህ እጅግ በጣም አዝኗል፤ ስለዚህ፡ ቤቱ ለእርሱ ሲባል የተሠራ ነውና፤ እርሱ የማይመለክበት ከሆነ “እንግዲያውስ” በማለት እንዲቃጠልና እንዲፈርስ ፈቀደ። ፈረንሳዮች ሙሉ በሙሉ እንዳይፈራርሱ ከፈለጉ በጣም ማልቀስና ወደ ጌታችን መመለስ ይገባቸዋል።
አባቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ለመጨረስ ሁለት መቶ አመት ፈጅቶባቸው ነበር፤ ለስምንት መቶ ዓመታት ያህል ብዚ ጦርነቶችን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ምንም ሳይነካ አሳልፏል፤ ዛሬ ግን፡ እውቀት ጨምሯል፣ ቴክኖሎጂው ሁሉ በጣም ተራቅቋል በሚባልበት ዘመን፤ ሕንፃው በሰዓታት ውስጥ ወደመ። በሰሜን ተራሮች ቃጠሎ አገራችን “ውሃ፣ ውሃ!” እንደሚል ሕፃን “ሄሊኮፕተር፣ ሄሊኮፕተር!” በማለት ለመነች፤ “የመጠቅችው” ፈረንሳይ ግን በታላቅ ንብረቷ ላይ የደረስውን እሳት ከበሰተላይ ለማጥፋት አንድም ሄሊኮፕተር መጠቀም አልቻለችም። ዋው! አይገርምምን?!
Leave a Reply