Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 17th, 2019

ተዓምር በፓሪስ | በተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስ ታየ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2019

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ብዙ ሰዎች እየመሰከሩ ነው። ድንቅ ነው። የዛሬዎቹ ከሃዲ ፈረንሳይ አባቶች ይህን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ክብር ሲሉ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በስንት ድካምና መስዋዕት ሠሩት። የአሁኑ ተልካሻ ትውልድ ግን ከአውሬነት ነፃ አውጥቶ እየባረከ ፀጋውን የሰጣቸውን ጌታችንን በመተው እንደ ይሁዳ የክህደት ኑሮውን መረጡ። በዚህም ይህን ድንቅ ቤተክርስቲያን ለፀሎት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እና ለነፍስ ማደሻ በመገልገል ፈንታ ጎብኝዎችን በመጋበዝ የገንዘብ ማምረቻ መሣሪያ አደረጉት።

አዎ! ጌታችን በዚህ እጅግ በጣም አዝኗል፤ ስለዚህ፡ ቤቱ ለእርሱ ሲባል የተሠራ ነውና፤ እርሱ የማይመለክበት ከሆነ “እንግዲያውስ” በማለት እንዲቃጠልና እንዲፈርስ ፈቀደ። ፈረንሳዮች ሙሉ በሙሉ እንዳይፈራርሱ ከፈለጉ በጣም ማልቀስና ወደ ጌታችን መመለስ ይገባቸዋል።

አባቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ለመጨረስ ሁለት መቶ አመት ፈጅቶባቸው ነበር፤ ለስምንት መቶ ዓመታት ያህል ብዚ ጦርነቶችን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ምንም ሳይነካ አሳልፏል፤ ዛሬ ግን፡ እውቀት ጨምሯል፣ ቴክኖሎጂው ሁሉ በጣም ተራቅቋል በሚባልበት ዘመን፤ ሕንፃው በሰዓታት ውስጥ ወደመ። በሰሜን ተራሮች ቃጠሎ አገራችን “ውሃ፣ ውሃ!” እንደሚል ሕፃን “ሄሊኮፕተር፣ ሄሊኮፕተር!” በማለት ለመነች፤ “የመጠቅችው” ፈረንሳይ ግን በታላቅ ንብረቷ ላይ የደረስውን እሳት ከበሰተላይ ለማጥፋት አንድም ሄሊኮፕተር መጠቀም አልቻለችም። ዋው! አይገርምምን?!

_________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እኅተ ማርያም | በመስቀል አደባባይ ለ666ቱ አውሬ የደም መስዋዕት ያደረገው መሪያችሁ ትክክለኛ ስሙ አብዮት አህመድ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2019

መስቀል አደባባይን ግራኙ መንግስቱ ኃይለ ማርያም የአብዮት ብሎ ሰየመው፤ የደም መስዋዕት አደረገበት፤ ግራኝ አብዮት አህመድ ተረከበው፤ የደም መስዋዕት አደረገ፤ ለግራኙ ዋቄዮ አላህ ሰጠው፤ የደም መስዋዕት ተቀበለበት፤ በደሙ ሰከረ። ግን፤ ሁሉም መስዋዕት በመጥረጊያ ወይም “በቆሻሻ ጠረጋ”ሳይሆን በክቡር መሰቀሉ በአንድ ዕለት ተጠራረገ።

አዎ! ግራኝ አብዮት አህመድ ሥልጣን ላይ በወጣ በወሩ የድጋፍ ሰልፍ ጥሪ ሲያደርግ፤ አንዳንዶቻችን “ገና ምንም ሳይሠራ ለምኑ ድጋፍ ነው ሕዝብ እንዲወጣለት የፈለገው?“ በማለት ጠይቀን ነበር። ለካስ ደም ለማፍሰሰና ለዋቄዮ አላህ መስዋዕት ማድረግ አቅዶ ነበር። ከዚህ በኋላ ነበር እነ መሀንዲስ ስመኘው፣ በጅጅጋ መነኮሳትና ቀሳውስት፣ በቡራዮ፣ ጌዲኦ፣ ለገጣፎ፣ አጣዬ ወዘተ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የተካሄደባቸው። ይህ እንዳቀደው የዓለም አቀፍ ማሕበረሰን ትኩረት አልሳበለትም፤ ስለዚህ ከመላው ዓለም የመጡ መንገደኞችን የተሸከመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን በይበልጥ አትኩሮትን ያገኝለት ዘንድ ለመስዋዕት ሥነ ስርዓቱ መረጠው – የዋቄዮ አላህ ዙፋን በሚገኝበት በሆራ ቢሸፍቱ ሸለቆ ውስጥ መቶ አምሳ ሰባት ሰዎች የደም መስዋዕት እንዲከፍሉ አደረገ። የሚገርም ነው፤ ባንዲራችን ላይ ያረፈውን ባለአምስት ማዕዘን ኮከብ ሙጭጭ አድርጎ መያዙ ለደም መስዋዕቱ ይረዳው ዘንድ ነው፡ ማለት ነው።

የሚገርም ነው፤ ዶ/ር አብዮት አህመድ ልጆች እንደሌሉት እኔም ጥርጣሬ ነበረኝ፤ እህታችን የተነገራት ነገር ትክክል ሳይሆን አይቀርም፤ ልጆቹ የተባሉት የእርሱ አይመስሉኝም። ልክ የባራክ ሁሴን ኦባማ “ዱርዬ” ሴት ልጆች የእርሱ እንዳልሆኑ። ዶ/ር አብዮት፡ ልጆች ከሌላቸው ከ ሦስቱ “M”ኦች፤ ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት አማኑኤል ማክሮን(በሰላሳ ዓመት የምትበልጠውን ሴት አግብቶ ይኖራል)፥ ከጀርመኗ ካንዝለር አንጌላ ሜርከል እና ከብሪታኒያዋ ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ ጋር በ 666ቱ አውሬ መንፈስ ስም አብሮ ተደምሯል፤ ስለዚህ ልክ እንደ እነሱ ሥልጣን ላይ እስቆየ ድረስ የደም መስዋዕት ማድረጉን እና ዓብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረሱን ይቀጥልበታል። ለዚህም ተጠያቂው እርሱ ብቻ ሳይሆን፤ ይህን ሁሉ ጉድ እያየ ለእርሱ ድጋፉን በመስጠት ላይ ያለው ግብዝ ሰው ሁሉ ነው። ዋ! ብለናል።

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »