ተዓምር በፓሪስ | መስቀሉ ብቻ ከቃጠሎ ተረፈ፤ ሰማዩ ላይ የላሊበላ መስቀል ታየ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2019
በኖትረ–ዳም ካቴድራል የተቀስቀሰው እሳት በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋል ሕንፃ ውስጥ እሳት አጥፊዎች ሲገቡ መስቀሉ ምንም ሳይሆን እና ሳይቃጠል ኃይለኛ ብርሃን አንጸባርቆ የታያቸው መስቀሉ ነበር። ይህ ትልቅ ምልክት ነው፣ ለመስቀሉ ጠላቶችም ማስጠንቀቂያ ነው። ዲያብሎስ ጠላት ይፈር፣ ቅጥል ይበል!
በጣም ድንቅ ነው! ይህ ሁሉ ነገር በሥላሴ ዕለት ነው የተፈጸመው፤ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ቅድስት ሥላሴን በጎበኝበት ዕለት።
በሌላ በኩል ደግሞ፤ ቢቢሲ በቀጥታ ሲያስተላለፍ ነበረው የቪዲዮ ምስል፡ ሰማዩ ላይ ነጭ ቀለም ያለውን መስቀሉን እሳቱ በፈጠረው ጥቁር ጭስ መካከል ጎልቶ ያሳየናል።
እንዴት ደስ ይላል! ተመስገን አምላካችን!
Leave a Reply