በጣም የምያሳዝን ነገር ነው፤ ይህ ፈረንሳይ ውስጥ በጎብኝዎች ብዛት የመጀመሪያውን ቦታ የያዘ ታሪካዊ ቦታ ነው። በስምንት መቶ ዓመት ታሪኩ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የእሳት አደጋ ሰለባ ሲሆን፤ እጅግ ያሳዝናል፤ የአንድ ሺህ ዓመት ታሪክ ያለው የፈረንሳውያን ብሔራዊ ማንነትና ኩራት በአንድ ሰዓት ዕልም ብሎ ጠፋ፡ ዋው!
ነገር ግን፤ በአገራችን ተንኮል ሲሠሩ በእነርሱ ላይ የፍርድ እሳት ይዘንብባቸዋል። የሰሜን ተራሮች ቃጠሎ ከሰማይ ይታያል። ባለፈው ወር ላይ ሰዶማዊው የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ማክሮን ከ ዶ/ር አህመድ ጋር ሆኖ ላሊበላን አላግባብ ረግጦ ነበር። “ላሊበላን እናድሰው” ብለው ነበር፤ ግን ጉዳዩ ተንኮል እንዳለበት የላሊበላን ድንቅ ዓብያተክርስቲያናት እንዲሠሩ አባቶችን እና መላዕክቱን ያዘዘው ኃያሉ እግዚአብሔር ያውቃል። እስኪ ይታይን፤ ወገኖቼ፤ በጣም ብርቅ የሆነውን እና በጎብኝዎች ዘንድ የመጀመሪያውን ቦታ የያዘውን ላሊበላ ንብረታችንን በእድሳት መልክ ሲተናኮሉ የራሳቸው አንደኛ ቱሪስት ሳቢ ካቴድራል ተቃጠለ። ሆኖም፡ በተለይ በእነርሱ ፋሲካ ቅዱስ ሣምንት ይህ አደጋ መከሰቱ እጅግ በጣም አሳዛኝና አጠራጣሪም ነው። የመሀመድ አርበኞች ይህን ካቴድራል እናፈርሰዋለን በማለት ደጋግመው ይዝቱ ነበር።
ያም ሆነ ይህ፡ በላሊበላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ያላግባብ ካባውን ለብሰው የነበሩት ፕሬዚደንት አማኑኤል ማክሮን እና ዶ/ር አብይ አህመድ ለራሳቸውም ለአገሮቻቸውም መጥፎ ዕድልን ይዘው መጥተዋል።
“ማክሮን በላሊበላ ካባ ለብሶ በተመለስ ማግስት ፓሪስ በተቃዋሚዎቹ ጋየች | የድል ሐውልት ላይ አውሬው ታየ”
ሰዶማዊው ማክሮን ላሊበላን አርክሶ ከተመለስ በኋላ ፲፪ የፈረንሳይ ዓብያተክርስቲያናት ላይ ክፉኛ ጥቃት ደርሶባቸዋል
በሚለው ቪዲዮ ላይ ይህን ጽፌን ነበር፦
ፕሬዚደንት ማክሮን ከአጋሩ ጠ/ሚንስትር ግራኝ አህመድ ጋር በመሆን ወደ ላሊበላ ሄደው ቅዱስ ዓብያተክርስቲያናቶቻንን አርክሰዋል። የሚገርመው ደግሞ፤ የራሱን አገር ዓብያተክርስቲያናት በአግባቡ መንከባከብና መጠበቅ ያልቻለው አማኑኤል ማክሮን የላሊበላ ዓብያተክርስቲያናትን “ለማደስ ቃል ገብቷል” መባሉ ነው።
በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ አማኑኤል ማክሮን እና አብይ አህመድ ላይ መዓት በመምጣት ላይ ነው። የለበሱት ካባ መዘዝ? እነዚህን ሁለት የኢትዮጵያ ጠላቶች ካባዎቹ አቦዝነዋቸው (deactivate) ይሆን?“
የሚገርም ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት እዚህ በእድሳት ላይ ከነበረው ካቴድራል ፊት ለፊት ቁጭ ብዬ አጠገቤ የነበርችው ሕፃን አሜሪካዊት እናቷን እንዲህ ብላ ስትጠይቃት መስማቴን አስታውሰዋለሁ፦
“ማሚ እነዚያ ሰዎች እዚያ ሕንፃ ላይ ምን እያደረጉ ነው?” እናትየዋም፦ “ቀለም እየቀቡት ነው፤ ዛሬ ቀብተው ከጨረሱ በኋላ ነገር ተመልሶ ጥቀርሻ ይሆናል” አለቻት፤ የአየር ብክለቱን ለመጠቆም።