Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 14th, 2019

ኢቫንካ ትራምፕ የኢትዮጵያ ጉብኝቷን በቡና ስነ ሥርዓት / 666 መስዋዕት ጀመረች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2019

ለአውሬው ፍየል መሆኑ ነው፤ ዋው! የቡናው ቤት ውስጥ ካልዲን እና ፍየሉን ለማስተዋወቅ ተሞክሯል። “ታሪኩ እንዲህ ይላል፦ አንድ ካልዲ የሚባል የፍየል እረኛ የሚጠብቃቸው ፍየሎች የሆነ ዛፍ ፍሬን በልተው ያልተገባ ባህርይ ማሳየት ጀመሩ”። የምል ጽሑፍ ግርግዳው ላይ ይነበባል።

አንዷ ፍየል ብቻ መስላኝ? ለማንኛውም በጉ ከፍየሎች የሚለይበት ዘመን ላይ ደርሰናልና ህዝበ ክርስቲያኑን አድነዝዞ ለእነ ዶ/ር አህመድ እንዲሰግድ ያደረገውን ቡናን አንጠጣ፤ ግድ የለም፤ ለፍየሎች እንተውላቸው።

ድርሳነ ጽዮን ማርያም” :- ተአምር 1 ላይ የተጻፈው በሙሉ ይህ ነው:-

ሰማያዊት የሆነች የእናታችን የጽዮን ተአምር ይህ ነው : ጸሎቷና በረከቷ ህዝበ ክርስቲያን ከምንሆን ከሁላችን ጋር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን::

ህዝበ ክርስቲያን ሆይ ልንገራቹ ሁላችሁም ስሙ የተጻፈ መጽሃፍ ሁሉ እኛ ልንመክርበት ተጽፏል እንዳለ ጳውሎስ ሮሜ 13:4 :ከአዳም ልጆች ወገን ሴሩህ የሚባል ሰው ነበር ለሴሩህ ስሙ ብኑ የሚባል ልጅ ተወልዶ በህጻንነቱ ሞተበት በብኑ ስም በተቀረጸው ጣኦት መመለክ ተጀምሯል በመቃብሩም ላይ ሰይጣን የሚወዳት ከሱስ የተነሳ ጾምን የምታሽር የከፋች ዕጽ በቀለች ይህውም በስንዴ መካከል እንክርዳድ የዘራ ጠላት ዲያብሎስ ካለችበት አምጥቶ ዘራት ማቴ ፲፫: ፳፰::

በብኑ ስም ቡን ተብላለች ቡና ማለት ነው: ማክሰኞ ከተፈጠሩት ዕፅዋት መልካምና ክፉ አሉ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያፈራል እንዳለ ማቴ ፯:፲፪

እስማኤላውያን የሚያመልኳቸው የጣኦታቸው መስዋዕት ሆነች የተንባላት አለቃ የሚሆን እስከ መሃመድም ትደርሳለች ተንባላትም ያለ እርሷ ሌላ አይሰውም ተንባላት ማለት የመሃመድ ተከታዮች ናቸው: ጣኦት የሚያመልኩ ባለዛሮችም ይህችኑ ይሰዋሉ የቡና ሱስ ያዘን ብለው ጾምን የሚሽሩ በበዓል የሚወቅጡ ራሳችንን አመመን በማለት በውስጣቸው ላደረ ለሱስ ጋኔን የሚገብሩ ብዙዎች ናቸው ወደ ቅዳሴም እንዳይሄዱ በጥዋት እሷን እየጠጡ ይህችም ዕጽ ክፉ ሁና ሰውን ስታሳስት ትኖራለች::

ተአምር ፪፦

ሌላም የሚያስረዳና ልቡናን የሚያጸና ስሙ ልንገራችሁ የተንባላት መምህር የነበረ ስሙ መሀመድ የሚባል አንድ ሰው ከመካዱ የተነሳ ከአጋንንት ጋር ይውላል ከዕለታት አንድ ቀን ሲሰግድ በልጅነቱ ያመው የነበረው የራስ ምታት በሽታ ይነሳበታል በዚህ በሽታ እየተሰቃየ ሳለ ከዕለታት በአንዱ ቀን ዲያቢሎስ በተንኮሉ ያስተው ዘንድ ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ መሀመድ ሆይ ምን ሆንክ ይለዋል የራስ ምታት በሽታ የሆነበት እርሱ ዲያቢሎስ ነው፡፡

መሀመድ መልሶ ከፍተኛ የራስ ምታት ነበረብኝ በዚህ ደዌ እጨነቃለው ይለዋል ዲያቢሎስም የራስ ምታት መድሀኒት ብነግርህ ታደርገዋለህን የልቦናዬን ፈቃድ ትፈጽመሀልን? ይለዋል መሀመድም ካዳንከኝ አዎ ያልከኝን ሁሉ አደርገዋለሁ ብሎ የመልስለታል፡፡

ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ

  • ዕጸ ጌት የተባለች ጫትን፣

  • ዕፀ ኩስራ የተባለችውን ቡናንና

  • ዕፀ ስጥራጢስ የተባለጭውን ጥንባሆን

እነዚህን ሶስቱን ዕፅዋት ከአሉበት አምጥቶ መድሀኒት ናቸው ብሎ ይሰጠዋል፡፡ይህንንም ቡና ከጠጣህ ፈጥነህ ትድናለህ ለልጅ ልጅ ዘመን በመካ መዲና መስዋዕት አድርገህ ሰዋ ብሎ ቆልቶ ያሰየዋል፡፡

መሀመድም ብረት ምጣድ አግሎ ያሳየዋል እንደመልኬ ከሰል አስመስልህ አጥቁረህ ትቆላለህ ይለዋል እንዳለው አድርጎ ከሰል አስመስሎ ይቆላል ሁል ጊዜም እንደዚሁ ካላከሰልክ መድሀኒት አይሆንህም ይለዋል ራስ ምታቱም ለጊዜው የተወው ይመስለዋል ኋላ ግን ሰዓት እየጠበቀ ይነሳበታል።

በመሓመድ ሥርዓትና ሕግ የሚጓዙ አወል ፤ ቶና ፤ በረካ የሚባሉ ሦስት ሰዎች ለንግድ የመጡ መስለው ከአምስት ተከታዬቻቸው ጋር እነዚህን ዕፅዋት ይዘው ይመጣሉ እነዚህም «ጫት፤ ቡና ፤ ጥንባሆ» ናቸው አህዛብ ለሰይጣን የሚያቀርቡዋቸው የጣኦት መስዋዕት ናቸው። የእግዚአብሔር መስዋእት ግን፤ 

  • ስንዴ
  • ዘቢብ
  • እጣን

ናቸው።

አርብ እና እሮብ ብዙ ሰዎችን እያዛጋ ከቅዳሴ የሚያስቀረው እኮ ቡና ነው። በፆም ሰዓት ብዙ ሰዎችን በራስ ምታት የሚቀውር ቡና ነው። ቡና ካልጠጡ ደስታቸውን የሚያጡ፣ የሚነጫነጩ፣ የሚሳደቡ፣ የሚደብራቸው ቤቱ ይቁጠራቸው። ቡና ቁጭ ተብሎ የሰው ሥጋ በሃሜት የሚበላበት ወሬ እንቶ ፈንቶ የሚሰለቅበት ነው። ሥራ ፈቶች እስከ 3ኛ የሚያንቃርሩት ቡና ቤተክርስትያን እስከምታወግዘው መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር የሰጠንን አእምሮ መጠቀም ብቻ በቂ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

___________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

“666”ቱ ባሏ የላካት የፕሬዚደንት ትራምፕ ልጅ ወደ አዲስ አበባ ሄደች | “ሴቶቻችንን ለማጎልበት” ከሚል ተልዕኮ ጋር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2019

አውሬው ከነጫማው ሃገረክርስቲያን ኢትዮጵያ ውስጥ እየገባ ነው፤ ከሁለት ዓመት በፊት “የጌታችን መስቀል ጫማ ላይ እንዲረገጥ ጫማዎችን እያመረተች ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው ፀረክርስቶሷ ቱርክ ናት” በሚል ርዕስ እታች የሚገኘውን ቪዲዮ አቅርቤ ነበር፦

አሁን ደግሞ ኢአማኒ ቻይና ከፕሬዚደንት ትራምፕ “ለዘብተኛ” ሴት ልጅ፤ ኢቫንካ ጋር በመተባበር የጫማ ፋብሪካዎችን በማስፋፋት ላይ ትገኛለች። ጉድ ነው፤ ኢትዮጵያውያንን ቻይኖች የማድረግ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ቪዲዮው በግልጽ ያሳያል። ኢትዮጵያውያን ማንንታቸውን እስከካዱላቸው ድረስ፣ ወደ ክርስቲያን ሃገር አይጠጉ እንጂ፤ ኢአማኒዎቹን ቻይናን፣ ምዕራቡን ወይም አረቡን ቢመስሉላቸው ግድ የላቸው፤ እንዲያውም ይህ ነው የሚፈለገው፤ ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዲተው። “እኔ አማራ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ…” የሚያስብሉንም “ኢትዮጵያዊ” ነኝ ማለቱን እንድናቆም ነው። ኢትዮጵያዊነታችንን እየተነጠቅን ነው፡ ወገን!

ሴትነታቸውን እየካዱ የመጡት ምዕራባውያን ሴቶች “የአፍሪቃን ሴቶች እናጎልብታለን” በሚል ተልካሻ መርሕ ሞኙ ሕዝባችንን ይደልሉታል። ሴቶች ከምዕራቡ ዓለም ይልቅ በአፍሪካ ከፍተኛ የሴትነት ሚና ይጫወታሉ፤ በተለይ ልጆችን ወልደው በማሳደግ፣ ቤተሰብን በመንከባከብ። አውሬው ግን ይህን አይወድም፡ ስለዚህ “ሴቶችን እናጎለብታለን” በማለት የአፍሪቃ ሴቶች እንዳይወልዱና እውነተኛውን ሴትነታዊ ማንነታቸውን ይክዱ ዘንድ ወሊድ መከላከያን እንዲጠቀሙ፣ እንዲያመነዝሩና ወንድን በመጥላት በግብረሰዶማዊ ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ይገፋፏቸዋል። ሁሉም ተግባራቸው ከ 666ቱ ነው።

በዓለማችን ላይ ከሚታዩት የክርስቶስ ተቃዋሚ ግለሰቦች መካከል ይመደባል ብዬ የማምነው ሰው የኢቫንካ ትራምፕ ባለቤት ያሬድ ኩሽነር ነው። የሚገርም ነው፡ የዚህ ቀፋፊ ሰው ቢሮ የሚገኘው በ ኒው ዮርክ ከተማ “666 Fifth Avenue/ 5ኛው ጎዳና” ላይ ነው።

______________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: