በሃይድ ፓርክ የ ‘መተንፈሻ መናፈሻ’ ይህን ድንቅ ትምህርት የሰጠን ጀግናው የሃይድ ፓርክ ክርስቲያን “ቦብ” ነው። በዚህ ትምህርቱ እስልምና የዓረብን ባሕል ማስፋፊያ መሣሪያ እንደሆነ፤ ለዚህም የግብጽ ኮፕቶች፣ ኑብያውያን እና ደቡብ ሱዳናውያን በምሳሌነት እንደሚቀርቡ ያስተምረናል።
የግብጽ ኮፕቶች እና ኑብያውያን ባሕላቸውንና ቋንቋቸውን ተግባራዊ እንዳያደርጉና የዓረብን ቋንቋ እና ባሕል እንዲከተከሉ ተገድደዋል። (በግብጽ አገር ኮፕትኛ ቋንቋን የተናገረ ምላሱ ይቆረጥ እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል፤ ያውም በገዛ አገራቸው።
እስኪ እንደምሳሌ ወስደን አለባበስን በሚመለከት እራሳችንን እንጠይቅ፦ ለሴት ሙስሊም ወገኖቻችን ዋናው ቁምነገር ሰውነታቸውና ጸጉራቸው እንዳይታይ በልብስ መከለል ከሆነ የሚሸፈኑበትን ሂጃብ የሀገራቸውን ነጠላ ወይም ኩታ ቀሚሳቸውንም የሐበሻ ቀሚስ ማድረግ ሲችሉ የኢትዮጵያ የሆነውን ልብስ ወርውረው በመጣል የሚጠቀሙት ከላይ እስከ ታች የዓረብን ልብስ ነው። ይህ ምንን ያሳያል? አዎ! ለማንነታቸው ያላቸው ግምትና ጥላቻ ከፍተኛ መሆኑ ነው። እነዚህ ወገኖች ወደዱም ጠሉም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለገዛ ሀገራቸው እሴቶች ጠላቶች ሆነዋል። እንግዲህ እስልምናን ሲቀበሉ ከልብሳቸው እስከ ቋንቋቸው ሁለነገራቸውን የዓረብ ለማድረግ መርጠዋል ማለት ነው።
የቦብ ሐተታ የሚያስተምረን፡ እስልምናን መቀበል ማለት የዓረብ ባሪያ ሎሌ ባንዳ መሆን ማለት እንደሆነ ነው፤ ይህም በመላው ዓለም በግልጽ የሚታይ ክስተት ነው፤ ሃይድ ፓርክን ጨምሮ።
ዓረቦች እንዲጠበቅላቸው የሚፈልጉት የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው ሁሉ እኛም ኢትዮጵያውያን ከነሱ የተሻለ እንዲጠበቅልን የምንፈልገው ማንነት አለን። የራስን ጥሎ የዓረብን መያዝ ማለት የውዴታ ባርነት ነው። የገዛ ማንነትን መካድ ነው። ችግሩ ወገኖቻችን ይሄንን አለመረዳታቸው ብቻ ሳይሆን ለመረዳት አለመሞከራቸውና አለመፈለጋቸውም ነው።
በተለይ፡ በአሁን ሰዓት በቅናትና ምቀኝነት መንፈስ በተዋሕዶ ክርስትና ላይ ለተነሱት የጎረቤት ሃገራት ጠላቶቻችን፣ ለምዕራባውያን የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እና ለዋቄዮ አላህ ልጆች ይህ ትልቅ ትምህርት ነው።