Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የግራኝ አህመድ ጂሃድ በ ከሚሴ እና አጣዬ | ሕዝብ እያለቀ ነው ፣ በ ዓብያተ ክርስቲያናት ላይ ጥቃት ደርሷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 8, 2019

ታሪክን ስለረሳን፤ የአባቶቻችንና እናቶቻችንን አስከፊ ዘመን በመርሳታችን፡ ታሪክ ተደግሞ እንዲታየን እየተደረገ ነው። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት የተካሄደው የግራኝ አህመድ ጽንፈኛ ዘመቻ አሁን አንድ ባንድ እየተደገመ ነው፤ ዓይናችን እያየ። ንገረው ንገረው እምቢ ካለ መከራ ያሳየው!

/ር ግራኝ አህመድ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን መጨፍጨፍ ያስችለው ዘንድ ሜንጫ እና ገጀራውን ለመረከብ ወደ ሩዋንዳ ተጉዟል – ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት የተፈጠረውን የእልቂቱን መንፈስ ወደ ኢትዮጵያ ይዞ ይመለሳል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ ለማይኖረው ዕልቂት ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ያለው ይህ የዶ/ርነት ማዕረግ የተሰጠው የሳጥናኤል ወኪል በሕዝባችን ላይ ጽንፈኛ የሆነ ተግባር ከመከሰቱ በፊት ሁሌ ሰበብ እየፈለገ ከኢትዮጵያ ሹልክ ብሎ ይወጣል። ሁኔታው ትንሽ መረጋጋቱን ሲያይ፡ ተመልሶ ይመጣና“ አላየሁም፣ አልሰማሁም፣ አላውቅኩም!” በማለት እያለቃቀስ ሞኞች ተከታዮቹን ያታልላል። ከፊሉ ሕዝባችን ይህን ያህል ይታለላል ብዬ አላስብም ነበር። አንጎሉን በምናምኑ ምን ያህል እንዳጠቡትና እንደተቆጣጠሩት ነው የሚያሳየን።  ሆኖም ግን ዓይንና ጆሮ እያላቸው ማየትና መስማት የተሳናቸው “ሞኞች” ከተጠያቂነት አያልፉም፤ የእያንዳንዱ ንፁኻን ደም በእጃቸው አለና። እነዚህ ሞኞች ልባቸውን ለአውሬው መቀለቡን እስካላቆሙ ድረስ አሳዛኙ ድራማ ይቀጥላል።

_________

Leave a comment